በሐገሪቱ የተስፋፋው ስራ ዓጥነት ለታቃዋሚ  ለአሸባሪ እና ለሁከት ሃይሎች ግብአት  ሆኗል ሲሉ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ተናገሩ

ኀዳር (አንድ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ እንደተናገሩት በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ፤ ሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ስራ አጥ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እየተቀላቀሉ ነው።

የወረዳው ወጣቶችን ያወያዩት ሃላፊው ወጣት አርሶ አደሩ ተምሮ ስራ ካላገኘ ፤ ወይ የሚያርሰው መሬት ከሌለው ከትግል ውጭ ሌላ ምን መፍትሄ አለው ሲሉ  ጥያቄ አንስተው ብቸኛው መፍትሄ ስራ አጥነትን መቅረፍ መሆኑን አመልክተዋል፡፡