ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ፣ በደቡብ እና በአማራ ክልሎች በተካሄደ የመረጃ አመራር ስልጠና ላይ አሰተያየት የሰጡ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞች ‹‹ቡጨ›› በማለት የሚጠሩት ቡጨቃ ፤ቆረጣ ወይም ሃብትን መካፈል የሚባለው አሰራር እንዳማረራቸው ገልጸዋል። ባለስልጣኖቹ “መንግስት ከከፈላቸው አበል ውጭ በድጋሜ አበል ካልተከፈላቸው ፕሮግራሞቻችን በደንብ አይሸፈኑም፤ ምንም አይነት ሂሳብ ካላገኙ ወይም የምግብ ፤ የነዳጅ እና ሌሎች ወጭዎች በጥሬ ብር ካልተሸፈነላቸው ...
Read More »ቡርኪና ፋሶ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሾመች
ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሌስ ካምፓወሬ መንግስት በ2 ቀናት አመጽ ከተገለበጠ በሁዋላ ስልጣን ለሳምንታት ተረክቦ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ስልጣኑን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ለተመረጡት ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኬል ካፋንዶ እንደሚያስረክብ ታውቋል፤፡ሌ/ኮ አይሳክ ዚዳ ስልጣናቸውን በፍጥነት እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል። የ72 አመቱ ካፋንዶ ከሃይማኖት፣ ከጦር ሰራዊት፣ ከፖለቲካ፣ ከሲቪክ ማህበረሰቡና ከባህላዊ መሪዎች ተውጣጦ በተመሰረተው ጉባኤ ተመርጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ከአንድ አመት በሁዋላ ...
Read More »ኢህአዴግ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አለመሳካቱን አመነ
ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘንድሮ የሚጠናቀቀው የኢህአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን የተለጠጠ ዕቅድ በግብርና ዘርፍ መዳከም ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን ኢህአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ አመነ፡፡ ኢህአዴግ «አዲስ ራዕይ» በተሰኘው በርዕዮተ ዓለም ልሳኑ የመስከረም- ጥቅምት 2007 ዓ.ም ዕትም ላይ የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአራት ዓመታት አፈጻጸም አስመልክቶ ባሰፈረው ሐተታ እንደጠቆመው ለጥጦ የያዘውን ዕቅድ ማሳካት እንዳልቻለ በማስቀመጥ አባላትና ደጋፊዎቹን ...
Read More »ከጉራፈርዳ የተፈናቀሉ አብዛኞቹ አርሶ አደሮች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆኑም
ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ በሆነው በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ህይወትና ንብረት ከወደመ በሁዋላ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ባለፉት ሁለት ቀናት የአካባቢውን አመራሮች በመሻርና በመሾም መረጋጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ ተፈናቃይ አርሶደሮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማግባባት ቢሞክሩም፣ አብዛኞቹ አርሶአደሮች ግን ለህይወታችን ዋስትና የሚሰጠን ስለማይኖር ወደ አካባቢው ለመመለስ ፈቃደኞች አይደለንም ብለዋል። በተለይም በከፍተኛ ሁኔታ ...
Read More »በጅማ በአሰቃቂ ሁኔታ እናትና ልጅን የገደለው ወታደር በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አልታወቀም
ኀዳር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተሰድቤአለሁ በሚል ምክንያት አንድ አዛውንትን እስከ ልጃቸው በሌሊት የገደለው ወታደር ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ ወደ መካለከያ ካምፕ ቢያመራም ህግ ፊት ይቀርብ አይቀርብ የታወቀ ነገር የለም። ወጣት ዮናስ በ16 ጥይቶች ተባስስቶ መገደሉን ከቅርብ ሰዎች የተገኘው መረጃ የሚያመልክት ሲሆን ወ/ሮ መንበረም ከ10 ያላነሰ ቦታ ላይ ተደብድበው ተገድለዋል። የከተማው ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ባሰማበት ወቅት ፖሊስ ...
Read More »በጅማ አንድ እናት እስከነልጃቸው በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊሶች ተገደሉ
ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በአካባቢው የሰፈሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ የሚወስዱት እርምጃ እየተባባሰ መጥቶ ረቡዕ ሌሊት ለሃሙስ አጥቢያ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የፌደራል ፖሊሶች ወደ አንድ ወጣት መኖሪያ ቤት ሰብረው በመግባት እርሱንና እናቱን በአምስት አምስት ጥይኦች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ወደ ካምፓቸው አምርተዋል። የከተማው ህዝብ ተቃውሞውን ለማሰማት ሃሙስ ጠዋት ወደ አደባባይ ቢወጣም ...
Read More »ከቦሌ ለሚ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታስረው ለስቃይ እየተዳረጉ ነው
ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ለሚ በሚባለው አካባቢ የማሪያም ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መደረጉን የተቃወሙ ነዋሪዎች ከፖሊሶች በደረሰባቸው ጥቃት በርካታ ሰዎች የተጎዱ ቢሆንም፣ ፖሊስ ሃይሉን አሰባስቦ በመምጣት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል። አብዛኞቹ ወጣቶች በኮብል ስቶን ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ፖሊስ ወደ ድርጅቶቹ በመሄድ ወጣቶችን በጅምላ ማሰሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወንድሞቹ የታሰሩት አንድ ነዋሪ ለኢሳት ሲናገር ...
Read More »በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ የአሜሪካ ኮንግረስ የውይይት መድረክ አዘጋጀ
ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብቶች የተባለው ድርጅት ለኢሳት በላከው መግለጫ የቶም ላንሶቶስ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ ታዋቂ ሰዎች ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟል። ተናጋሪዎቹ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ በመገምገም የአሜሪካ መንግስት የዲፕሎማቲክና የገንዘብ ድጋፉን ተጠቅሞ በኢትዮጵያ የሚታየው የተበላሸ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል ግፊት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል መግለጫው አመልክቷል። ዝግጀቱ ...
Read More »ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የ20 ሺህ ብር ዋስትና ገንዘብ ባለማስያዙ በእስር ላይ ነው
ኀዳር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ የዕንቁ መፅሔት አዘጋጅ በነበረው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ላይ የተሳሳተ መረጃን በመስጠት፣ ማነሳሳትና ግዙፍ በሆነ ማሰናዳት ወንጀል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል አራዳ ምድብ ችሎት ህዳር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ክስ የመሠረተበት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የተጠየቀውን የ20ሺህ ብር ዋስትና ማቅረብ ባለመቻሉ በቂሊንጦ በእስር ላይ መሆኑ ታውቆአል፡፡ የጋዜጠኛውን ዋስትና በመዋጮ ...
Read More »የቤተክርስቲያንን መፍረስ የተቃወሙት ተደበደቡ
ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 11 በለሚ አካባቢ የምትገኘው ማሪያም ቤተከርስቲያን በህገወጥ መንገድ ተሰርታለች በሚል ፖሊሶች ለማፍረስ ሲሄዱ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። ድርጊቱን የተቃወሙ ምእመናን “ቤተክርስቲያኑዋን ማፍረስ አትችሉም” ማለት ሲጀምሩ ፖሊሶች መደብደብ የጀመሩ ሲሆን፣ ህዝቡም በአጸፋው በፖሊሶችና በወረዳው አስተዳዳሪ ላይ ድንጋይ በመወርወር የተወሰኑ ፖሊሶችን አቁስሏል። የወረዳው አስተዳዳሪም ጉዳት ደርሶባቸው አምልጠዋል። ወደ ...
Read More »