ቡርኪና ፋሶ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሾመች

ኀዳር (ስምንት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የብሌስ ካምፓወሬ መንግስት በ2 ቀናት አመጽ ከተገለበጠ በሁዋላ ስልጣን ለሳምንታት ተረክቦ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ስልጣኑን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ለተመረጡት ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኬል ካፋንዶ እንደሚያስረክብ

ታውቋል፤፡ሌ/ኮ አይሳክ ዚዳ ስልጣናቸውን በፍጥነት እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል። የ72 አመቱ ካፋንዶ ከሃይማኖት፣ ከጦር ሰራዊት፣ ከፖለቲካ፣ ከሲቪክ ማህበረሰቡና ከባህላዊ መሪዎች ተውጣጦ በተመሰረተው ጉባኤ ተመርጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከአንድ አመት በሁዋላ በሚደረገው ምርጫ አይወዳደሩም። ቡርኪናፋሶ በሁለት ቀናት ህዝባዊ አመጽ ለ27 አመታት የቆየውን የካምፓወሬን መንግስት መገልበጧ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንዳታገኝ አድርጓታል።