ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትናንቱ የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፖሊሶች ከፍተኛ ብትር ያረፈበትና የአካል ጉዳት የደረሰበት ጋዜጠኛ ስለሽ ታሞ በተኛበት ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ትናንት እንደሱ የከፋ በትር ላረፈባቸው የትግል አጋሮቹ እና ለለውጥ ሀይሎች በሙሉ፦<< አይዟችሁ!እንበርታ! መብታችንን ለማስከበር ከምናደርገው ትግል በፍጹም ወደ ሁዋላ እንዳንል፤ 2007 የለውጥ ዓመታችን ነው”ሲል መልእክት አስተላልፏል። በሰልፉ ላይ እንዴት እና በምን ...
Read More »ራዲዮ ፋና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ካወያየ በሁዋላ ፕሮግራሙን አልለቅም አለ። ውይይቱ ኢሳት ዝግጅት ክፍል ገብቷል።
ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ ራዲዮ ፋና “ሞጋች” በተሰኘ ፕሮግራሙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ለውይይት በመጋበዝ በተለይም አመጽ ቀስቃሾች መሆናቸውን በሚያሳጣ መልኩ ፕሮግራሞችን ሲለቅ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት የአንድነት አመራሮችን- ከድርጅቱ ካፈነገጡት ከነትእግስቱ አወል ቡድን ጋር በማከራከር ለህብረተሰቡ አንድነቶች የተከፋፈሉ ናቸው የሚል መል እክት በስፋት ያስተላለፈው ራዲዮ ፋና፤ ሀሙስ እና አርብ እለት በተመሳሳይ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ...
Read More »የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር -አንድነት አባላት ላይ የተወሰደውን የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ አወገዘ።
ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ፤ገዥው ፓርቲ በአንድነት የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ ለመቃወም ሰልፍ በወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና በፓርቲው ጽህፈትቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ በነበሩ አዛውንቶቸ ላይ ሳይቀር ድብደባ በመፈጸም ፤ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል ብሏል። ትብብሩ ጠርቶት በነበረው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ያስታወሰው መግለጫው፤<<የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ ...
Read More »የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው የዱባይ ማራቶን ኢትዮጰያውያን በወንድም በሴትም አንጸባራቂ ድል ተቀዳጁ።
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአበበ ቢቂላ፣ የማሞ ወልዴና የዋሚ ቢራቱ ልጆች በአረቢያን ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ጀግንነታቸውን አስመሰከሩ። ወበቃማውን የዱባይ አየርና አናት የምትበሳውን ጸሀይ በመቋቋም በደማቅ ቀለም ልዩ ታሪክ ጻፉ። የዝናም ውሀ በተጠማው የዱባይ ምድር አረንጓዴ ጎርፍ ፈሰሰ። ዛሬ ማርፈጃውን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው የዱባይ ማራቶን በወንዶች 1ኛ ኢትዮጰያ 2ኛ ኢትዮጰያ………………….12ኛ ኢትዮጵያ በመሆን አጠናቀዋል። የዱባይ ዜና አገልግሎት <<ኢትዮጰያውያኑ ዓለምን ...
Read More »ለመጪው ምርጫ በአድማ ብተና ስም እየተሰጠ ያለውን ስልጠና የተቃወሙ 97 የፌዴራል ፖሊስ አባላት እርምጃ ሲወሰድባቸው፤ 119 ፖሊሶች በግዳጅ እረፍት እንዲወጡ ተደረገ።
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የተባረሩት አብዮታዊ ዲሞክራሲን መቀበል ያልቻሉ ናቸው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊነሱ ይችላሉ የተባሉ ህዝባዊ አመጾችን ለማክሸፍ ያስችላል የተባለ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ከየክልሎቹ የመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በፌድራል ፖሊስ አድማ ብተና አደረጃጀት በየክልሉ የሚካሄደውን ይህን ስልጠና፦ << የፖሊስን ተልእኮና ዓላማ ...
Read More »የመኢአድ ምክትል ፕሬዝደንት አዘዞ ጦር ካምፕ መወሰዳቸው ተነገረ።
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ። መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ...
Read More »የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር- የመንግስት ሚዲያዎችን ተቸ
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቲቪ(ኢቢሲ) ፣ራዲዮ ፋና እና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ጠንካራ ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ተቸ። የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተፎካሪ ፓርቲዎች በተሰጣቸው አጀንዳ ዙሪያ ብልጫ ያለው ስራ አልሰሩም ሲል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር -የኢትዩጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬትን ወቀሰ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ -ለኢቢሲ ባስተላለፈው የደብዳቤ ትእዛዝ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ...
Read More »በመላ ሀገሪቱ ዜጎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እየተገደዱ ነው።
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህርዳር፣የአዲስ አበባ፣ የአምቦ፣ የጅማ፣የድብረማርቆስ እና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት ወኪሎች እንደተናገሩት በየቤቱ እየዞሩ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ በሚቀሰቅሱ ካድሬዎች ከመረበሻቸውም በላይ የምርጫ ካርድ ካላወጡ ስለሚጠብቃቸው ቅጣት ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ሲጀመር ምርጫ መኖሩ በየቀኑ በራዲዮና በቴሌቪዥን እየተለፈፈ ባለበት ሁኔታ በር እያንኳኩ ምርጫ ካርድ ውሰዱ ብሎ መቀስቀሱ አስፈላጊ አልነበረም ያሉት የባህርዳር ነዋሪዎች፤ ቅስቀሳው ግዴታ ...
Read More »በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር በተቃዎሟቸው ኢትዮጰያውያን ላይ የመሰረቱትን ክስ የስዊድን ፖሊስ ውድቅ አደረገው።
ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል። <<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤ ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር ነበር- ተቃውሟቸውን ጫማና እንቁላል በመወርወር የገለጹት። ኢትዮጰያውያኑ -አምባሳደሯን መኪና ላይ ...
Read More »ሰሞኑን የሐመር አርብቶ አደሮች ራሳቸውን ከፖሊስ ጥቃት ለመከላከል በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ፤ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ የፖሊስ ሀይሎችን ሙትና ቁስለኛ ማረጋቸው ተመለከተ።
ጥር ፲፬(አስራ አራት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶች ልብሳቸውን በመቀየር በእግራቸው ወደ ጅንካ ከተማ እየሸሹ ነው። የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃን በመጥቀስ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንደተመለከተው፤ ሐመሮች በወሰዱት የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የዞኑን የፖሊስ አዛዥ ሻምበል ለማ አሸናፊን ጨምሮ ሰባት ፖሊሶች ሲገደሉ፤ ስድስት ፖሊሶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነዋል። ከፖሊሶቹ በተጨማሪ ሁለት ሲቪሎችም መገደላቸውና ሶስት ሰዎች መቁሰላቸው የፖሊስ ሪፖርት ...
Read More »