የአይካ ጨርቃጨርቅ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቱርክ ዜጎች በመሰረቱት አይካ ጨርቃጨርቅ ውስጥ የሚሰሩ ከ8 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጠይቀው የጠበቁትን ጭማሪ ባለማግኘታቸው አድማ መተዋል። አድማው የተጀመረው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን ፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አድማው ቀጥሎአል።

Read More »

በአብድራፊና በሶረቃ ከተማ የህዝብ ተመራጮች እየተያዙ ነው

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ህዝቡን አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች እየታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች አመራሮችም እየታደኑ ነው። የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአካባቢው ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አቶ አዋጁ አቦሃይ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2007 ዓም በ8 የፌደራል ፖሊሶች መሳሪያቸውን ተቀምተው ታስረዋል። ሶረቃ ውስጥ የሚኖሩ አቶ ደጀን የተባሉ ሰውም ...

Read More »

የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ሚዲያ አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊ አለመሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ያወጣው ረቂቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ውድድር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰዓት አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን አስታውቋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችን በረቂቅ የሰዓት ድልድሉ ላይ ጊዮን ሆቴል ጋብዞ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ኃላፊዎች ባቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ...

Read More »

ከአረብ ሃገር ተመላሾች መሬታችን በመነጠቃቸው ሰርተው ለመኖር አለመቻላቸውን ተናገሩ ፡፡

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ፣ ሰሜን ወሎና ባቲ አካባቢዎች የሚኖሩ ከስደት ተመላሽ ወጣቶች ባሰሙት ቅሬታ፤ ከአረብ ሃገር ወደ ሃገራችሁ ግቡ የሚለውን የገዢው መንግስት ቅስቀሳ በመስማት ስራቸውን ጥለው ወደ ሃገር ቤት ቢመጡም፣  ከስደት በፊት ጥረው ግረው ያለሙትን ቦታ በኢንቨስትመንት ስም ለባለሃብቶች ተሰጥቶ በማግኘታችው አብዛኛው ወጣቶች ተመልሰው ሲሄዱ ሌሎች ደግሞ ለችግር ተዳርገዋል። 1 መቶ 80 ቅሬታ አቅራቢ ወጣቶች  ...

Read More »

ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት አልጠበቀም በሚል የተቸ የጤና ባለሙያ እንዲታሰር ተባለ

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ በጩኮ 02 ቀበሌ በቡድን የተደራጁ ሰዎች የአንድን ነጋዴ ቤት  በመዝረፍ ግምቱ 9 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት ዘርፈውና ድብደባ ፈጽመው ከተሰወሩ በሁዋላ፣ ድርጊቱን የተቃወሙ  የአለታ ጩኮ ጤና አጠባበቅ ጣብያ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጤና እንዲያዝ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶበታል ። ዝርፍያው የተፈፀመው አቶ ተሾመ የተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ...

Read More »

475 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት የቀላል ባቡር መስመር ምርቃት እያነጋገረ ነው

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶስት ተከፍሎ ከሚካሄደው የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ መካከል ከቃሊቲ እስከ ለገሃር ያለው መስመር ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በጥድፊያ ባለፈው እሁድ እንዲመረቅ መደረጉና የሙከራ ስራው ለቀጣይ ሶስት ወራት እንደሚቀጥል መታወቁ እያነጋገረ ነው። የባቡሩ ግንባታ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎችና የመንገደኞች ተርሚናሎች እንዲሁም ከሀያት ወደ ጦር ሃይሎች እና ከፒያሳ የሚነሳው መስመር ግንባታው አልተጠናቀቀም። የባቡሩን መስመር ለማስመረቅ ጥድፊያ የተሞላበት ...

Read More »

በክልሎች የሚገኙ የአንድነት አመራሮች ጽ/ቤታቸውን በአቶ ትእግስቱ ለሚመራው ቡድን እንዳያስረክቡ ተጠየቁ

ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራውና  በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው የአንድነት አመራር ጥር 29 ቀን 2007 ዓም የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሰባ ለማካሄድ እንዲሁም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ቀበና በሚገኘው ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ቢሮው በፖሊስ በድንገት በመከበቡ ሳይሳካ ቀርቷል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አበበ አካሉ ለኢሳት እንደገለጹት ስብሰባውን ለማካሄድ ታስቦ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት የትግል ጥሪ አቀረቡ

ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢውን ፓርቲ በሃይል ለማንበርከክ በትግል ላይ የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት ጥሪያቸውን ያቀረቡት የመስክ ጉብኝት ለማድረግ ለተንቀሳቀሱት የኢሳት ጋዜጠኞች ነው። ሴት አርበኞቹ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አፈናና የመብት ጥሰት በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለማንበርከክ  ነፍጥ እንዲያነሱ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል። ለሁለት ወራት ያክል ከኢህአዴግ ታጣቂ የሰራዊት አባላት ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ስታደርግ ቆይታ ...

Read More »

በሰሜን አርማጭሆ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአማራ እና በትግራይ አዋሳኝ ቦታዎች ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ የአካባቢውን ህዝብ ለአመጽ ያነሳሳሉ ያላቸውን ሰዎች ለመያዝ መመኮሩ ብዙ ወጣቶች ቀያቸውን እየተዉ እንዲሸፍቱ አስገድዷቸዋል። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የአካባቢውን ወጣት እየሰበሰቡ የግንቦት7ትን መመሪያ እያስፈጸማችሁ ነው በማለት እያስፈራሩዋቸው ሲሆን ፣ ነዋሪዎቹ ግን ጥር 16 ባወጡት ...

Read More »

ምርጫ ቦርድ፣ ቦርዱን ያከብራሉ ያላቸውን በእነ ትግዕስቱ አወሉ ለሚመራው አንድነት እና በእነ  አቶ አበባው መሀሪ ለሚመራው መኢአድ ዕውቅና ሰጠ፡፡

ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና የቦርዱ ጸሀፊና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ በጋራ ዛሬ ጥር 21 ከቀኑ 10፡00 ሰኣት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ በእነአቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራው አንድነት፤ የፓርቲውን ደንብና የምርጫ አዋጁን የጣሱ ተግባራትን እንደሚያከናውን፣ ፓርቲው ያካሄደውን ጉባዔ ለሰባት ወራት ሳያሳውቀው መቆየቱን፣ የቀድሞ ፕሬዚደንት ከሃላፊነታቸው የተነሱት ሕጉን ጠብቆ ...

Read More »