የአይካ ጨርቃጨርቅ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቱርክ ዜጎች በመሰረቱት አይካ ጨርቃጨርቅ ውስጥ የሚሰሩ ከ8 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጠይቀው የጠበቁትን ጭማሪ ባለማግኘታቸው አድማ መተዋል።

አድማው የተጀመረው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን ፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አድማው ቀጥሎአል።