(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 25/2011)ዶክተር አብይ አሕመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ ተመረጡ። ለኢሕአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን እንደገና ተመርጠዋል። በዚሁም መሰረት አቶ አብይ አህመድም ሆነ አቶ ደመቀ መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱንና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን እንደያዙ እንደሚቀጥሉ ምርጫው አመልክቷል። በሐዋሳ እየተካሄደ ያለው የኢሕአዴግ ጉባኤ የግንባሩን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መርጧል። ለዚሁ የአመራርነት ስልጣን የተወዳደሩት ዶክተር አብይ አህመድ ከ177 መራጮች የ176ቱን ድምጽ በማግኘት ...
Read More »በአዲስ አበባ ሶስት የፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011)አዲስ አበባ ላይ ሶስት የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸው ተገለጸ። 5 ፖሊሶችም መቁሰላቸው ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩም የፖሊሶቹን መገደል አረጋግጠዋል። አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ሌሊት ላይ የተፈጸመውና ለፖሊሶቹ መገደል ምክንያት የሆነው ነገር የተፈጠረው በመጠጥ ሃይል የተገፋፋው የፖሊስ አባል ሁለት ባልደረቦቹን በመግደሉ እንደሆነ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ሌሎች ፖሊሶች ደግሞ አደጋውን እያደረሰ ያለውን ...
Read More »የሲአን አመራሮች ኢትዮጵያ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ አመራሮች በመንግስት የተደረገውን ጥሪ ተቀብለው ዛሬ ኢትዮጵያ መግባታቸው ታወቀ። በሲአን የውጭ ግንኑነት ሃላፊ በአቶ ደምቦባ ኪያናቴ የተመራው የልኡካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ሲገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተቀብለዋቸዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከዛሬ 40 አመት በፊት የመብት ጥያቄ አንስተው በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አንዱ እንደነበር ይታወቃል። ሴአን የሽግግር መንግስቱ አባልና በኋላም እንደ ...
Read More »የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ቁጥር ወደ አንድ መቶ ሺ ተጠጋ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ወደ አንድ መቶ ሺ መጠጋቱ ተገለጸ። ነዋሪዎቹን በማፈናቀልና በማጥቃት የክልሉ ፖሊስ ሃይል መሳተፉን የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ሲገልጹ የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት የክልሉ ፖሊስ በድርጊቱ አልተሳተፈም ሲሉ አስተባብለዋል። የመንግስት የአደጋ ጊዜ ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ እስካሁን የተፈናቀሉት ዜጎች ቁጥር 91 ሺ 348 መድረሱን አስታውቀዋል። በአጠቃላይ የ16ሺ ያህል ቤተሰብ አባላት የሆኑት እነዚህን ተፈናቃዮች ለመረዳት ...
Read More »የስኳር ልማት ፈንድ 65 ቢሊየን ብር የት እንደገባ አይታወቅም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011)ከኢትዮጵያ የተለያዩ ስኳር ፋብሪካዎች ለስኳር ልማት ፈንድ ተብሎ የተሰበሰበው 65 ቢሊየን ብር ያህል ገንዘብ የትና ለምን አላማ እንደዋለ እንደማይታወቅ አንድ የመስኩ ባለሙያ ገለጹ። ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የፋክተሪና ሎጅስቲክ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አማረ ለገሰ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ገንዘቡ ለ22 አመታት ያህል የተሰበሰበ ነው ስኳር ከፋብሪካ በሚወጣበት ዋጋና ለነጋዴዎች በሚደርሰው ሒሳብ በትንሹ በኩንታል የአንድ ሺህ ብር ...
Read More »የኦነግ ታጣቂዎች ትጥቅ አልፈቱም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 24/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ታጣቂዎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ትጥቅ አለመፍታታቸውን አንድ ከፍተኛ የኦነግ አመራር ገለጹ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ኦነግ በገባው ቃል መሰረት ታጣቂዎቹን ወደ ካምፕ እንዲያስገባም ጥሪ አቅርቧል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገጠር አደረጃጀት ሃላፊና የኦዴፓ ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲሱ አረጋ “በኦነግ ስም ታጥቀው በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱትን በትዕግስትና በብስለት እያየን ነው” በማለት ከሰሞኑ ያስተላለፉትን መልዕክት ተከትሎ የኦነግ ከፍተኛ ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ በካማሺና ሌሎችም ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በእየለቱ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የተፈናቃዮች ቁጥር ከ150 ሺ በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። መንግስት ያቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር መንግስት በቂ የመከላከል እርምጃ እንዳልወሰደ እና ግጭቱ መጨመሩን ሲገልጹ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለስልጣን ...
Read More »በሰሜን ሸዋ የመብራት መጥፋት በነዋሪዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው።
በሰሜን ሸዋ የመብራት መጥፋት በነዋሪዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። ( ኢሳት ዜና መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ/ም ) በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች በተከታታይ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የኤሌትሪክ መቆራረጥ በመፈጠሩ በነዋሪዎቹ እና በባለሃብቶች ሥራ ላይ ከፍጠኛ ጫና መፍጠሩን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በተለይም በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በመብራት መጥፋት ምክንያት የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለኅብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረዋል። ግምቱ ከ7.2 ሚሊዮን በላይ ...
Read More »ዲቪ ሎተሪ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) የ2020 የዲቪ ሎተሪ ዛሬ ተጀመረ። ከአፍሪካ ሃገራት ለናይጄሪያ እንዲሁም ከሩቅ ምስራቅ ለቻይናውያን እድል የነፈገው የዚህ አመት ዲቪ ሎተሪ ለአንድ ወር ያህል የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል። ባለፉት 20 ያህል አመታት ከ1 ሚሊየን በላይ የውጭ ሃገራት ዜጎች በዲቪ ሎተሪ አሜሪካ መግባታቸውም ታውቋል። በአመት እስከ 55ሺ ለሚሆኑ ሰዎች በሚሰጠው እድል እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1995 ጀምሮ በዲቪ ሎተሪ አሜሪካ በመግባት ከአለም ሃገራት ...
Read More »ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ምትክ አዲስ ስራ አስኪያጅ ተሾመ። የኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ለግድቡ ግንባታ በዋና ስራ አስኪያጅነት የሾሙት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮን መሆኑ ታውቋል። ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳንና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ በምክትል ስራ አስኪያጅነት መሾማቸውም ይፋ ሆኗል። አዲሶቹ ተሿሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ታውቋል። በምክትል ስራ አስኪያጅነት የተሾሙት ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን ...
Read More »