አቶ አህመድ አብተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011)የፖሊሲ ምርመራና ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አህመድ አብተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾመ። የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ፊርማ የተሾሙት አቶ አህመድ አብተው ዶክተር ይናገር ደሴን ይተካሉ ተብሏል። አዲስ ፎርቹን የባንኩን ምንጮች ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ አቶ አህመድ አብተው ከመስከረም 9/2011 ጀምሮ የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን የቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት ...

Read More »

ግሎባል አልያንስ ከቤንሻንጉል ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ማሰባብሰብ ዘመቻ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ግሎባል አልያንስ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለተፈናቀሉ ከ70ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የገንዘብ ማሰባብሰብ ዘመቻ በይፋ መክፈቱን አስታወቀ። አለም ዓቀፍ መብት ለኢትዮጵያውያን ግሎባል አሊያንስ በጎ ፈንድ ሚ አማካኝነት ለከፈተው ዘመቻ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል። በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ወጣቶች ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመነጋገር ለቤንሻንጉል ጉምዝ ተፈናቃዮች የተለያዩ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገለጿል። ...

Read More »

የወልቃይትን ህዝብ የማፈናቀልና የማሳደድ ተግባር ይቁም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011)የወልቃይትን ህዝብ የማፈናቀልና የማሳደድ ተግባር እንዲቆም ልሳነ ግፉአን ጠየቀ። ለወልቃይት ጠለምትና ጠገዴ የአማራ ተወላጆች መብት የሚቆረቆረው ልሳነ ግፉአን በህወሃት አገዛዝ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ላይ የሚደረሰውን የመብት ጥሰት በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል። ሰሞኑን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከተለያዩ የወልቃይት አካባቢዎች መፈናቀላቸውን ተከትሎ ልሳነ ግፉአን የአማራ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል። የተፈናቀሉት ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግም ልሳነ ግፉአን ጠይቋል። ...

Read More »

አቶ ጌታቸው አሰፋ በኢሕአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ አልተገኙም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ለሕወሃት ስራ አስፈጻሚነት የተመረጡ የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ በኢሕአዴግ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንዳልተገኙ ተነገረ። በፌደራል መንግስት የእስር ማዘዣ እንደወጣባቸው ሲነገርባቸው የቆዩት አቶ ጌታቸው አሰፋ በሕወሃት ስራአስፈጻሚ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎቹን እያነጋገረ ይገኛል። አቶ ጌታቸው አሰፋ ላለፉት 18 አመታት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ ለተፈጸሙ መንግስታዊ ግድያዎችና በዜጎች ላይ ለደረሱ ሰቆቃዎች ተጠያቂ ናቸው። ከስልጣን ከወረደ ...

Read More »

ፌደራሊዝም የተሻለ የፖለቲካ አስተዳደር ስርአት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 23/2011) ክልላዊ አስተዳደርን ከብሔር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድ ከቻልን እንደ ኢትዮጵያ ላለች ሃገር ፌደራሊዝም የተሻለ የፖለቲካ አስተዳደር ስርአት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። በሃዋሳ ዛሬ በተከፈተው የኢሕአዴግ 11ኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሁሉም ክልላዊ አስተዳደሮች ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተዳድሩ መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተረከብናትን ኢትዮጵያን አለመውደድ መብታችን ነው አስውበን ማስረከብ ግን ግዴታችን ነው ሲሉም ዶክተር አብይ አህመድ ...

Read More »

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለ3 ቀናት የሚቆየውን ኢህአዴግ ጉባኤ በአዋሳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ፓርቲያቸው የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚያደርግንና ወዴት አቅጣጫ ሊወስደው እንዳሰ በተናግረዋል። “ አገራችን የቀደመውን ጠብቀውና አዲስም አክለውበት ለመጪው በሚያስተላልፉ ተተኪ ወጣቶች እየተመራች፣ እየተገነባች የ21ኛው ...

Read More »

በከፋዞን ከ800 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በከፋዞን ከ800 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) በደቡብ ክልል በከፋ ዞን ይኖሩ የነበሩ ከ882 ያላነሱ የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። በ1946 ዓም ከሰላሌና ሜታሮ ቤት የተወሰዱ 20 ሺ የሚጠጉ የኦሮሞ ተወላጆች በከፋ ዞን እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ከ1983 ዓም ጀምሮ ቋንቋቸውን እንዳይጠቀሙ በመታገዳቸው ጥያቄ ማቅርባቸውን ተናግረዋል:፡ የአካባቢው ባለስልጣናት ...

Read More »

በቦረና አካባቢ ኦነግ ህዝቡን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው

በቦረና አካባቢ ኦነግ ህዝቡን የጦር መሳሪያ እያስታጠቀ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው ( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በቡሌ ሆራና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ታጣቂዎች፣ “ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች ተመልሰው ስልጣን የሚይዙ በመሆናቸው ትጥቃችን አንፈታም” በማለት ህዝቡን ሰብስበው በማናገርና ወጣቶችን እየመለመሉ በማስታጠቅላይ ናቸው። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሰዎች እንደተናገሩት፣ የታጣቂዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ህዝቡ ...

Read More »

በኢሕአፓ ስም አዲስ አበባ የገቡት ሰዎች ድርጅቱን አይወክሉም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011)በኢሕአፓ ስም በአዲስ አበባ አቀባበል የተደረገላቸው ሰዎች ድርጅቱን የሚወክሉ አይደሉም፥አባላችን አለመሆናቸውም ይታወቅልን ሲል ህጋዊ ነኝ ያለው ፓርቲ ያወጣው መግለጫ አመለከተ። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)’’አንድና አንድ ብቻ ነው”በሚል የወጣው የድርጅቱ መግለጫ እንዳመለከተው በአቶ መርሻ ዮሴፍ ስም አዲስ አበባ የገባው ቡድን እራሱን በአንጃነት የፈረጀ ነው። እናም አርማውም፥ስሙም በሕግ የተመዘገበ ኢሕአፓ የተባለ ፓርቲ እያለ፥ አባላት ያልሆኑ ሰዎችን የድርጅቱ አመራሮች ናቸው ...

Read More »

አዴፓ ሊቀመንበሩንና ምክትል ሊቀመንበሩን መረጠ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 22/2011) አዴፓ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። የቀድሞው ብአዴን አዲሱ አዴፓ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌንና አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መምረጡም ተመልክቷል። ደኢሕዴንም ወይዘሮ ሙፍርያት ካሚልንና አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በድጋሚ መርጧል። ደኢሕዴንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ፍጹም አረጋን ጨምሮ 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መምረጡም ታውቋል። የቀድሞው ...

Read More »