ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ

ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ በሚቀጥሉበትጊዜያት ስለሚመራበት የፖለቲካ አቅጣጫ ተናገሩ
( ኢሳት ዜና መስከረም 23 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለ3 ቀናት የሚቆየውን ኢህአዴግ ጉባኤ በአዋሳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ፓርቲያቸው የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በምን መልኩ ተግባራዊ እንደሚያደርግንና ወዴት አቅጣጫ ሊወስደው እንዳሰ በተናግረዋል።
“ አገራችን የቀደመውን ጠብቀውና አዲስም አክለውበት ለመጪው በሚያስተላልፉ ተተኪ ወጣቶች እየተመራች፣ እየተገነባች የ21ኛው ክፍለ ዘመን አብሪ ኮከብ ለመሆን ብቅ ባለችበት የለውጥ ዘመን ላይ ትገኛለች።” የሚሉት ዶ/ር አብይ፣ “የበለጸገች የጋራ ቤታችንን ለልጆቻችን ማድረስ የምንሻ ከሆነ ዝርፊያውንና የመጠላለፍ ፖለቲካውን ትተን ተግተንና ታጥቀን በጋራ መስራት የኖርብናል። እኩልነትና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየት የምንሻ ከሆነ ዘር እና ሃይማኖትንን መሰረት አድርገን አናጥቃ።” ብለዋል።
“ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን እኔ ሰራሁዋት ሊል አይቻለውም፤ ኢትዮጵያ በሁላችንም ደም እና ላብ የተሰራች በመሆኗ፣ ባለቤቶቿ ሁላችንም ነን። ትናንት የሁላችንም አባት እናቶች ለዚህ አገር ደማቸውን ገብረዋል። እንኳን ዛሬ በህይወት ቆመን ይቅርና ሁላችንም ካለፍን በሁዋላ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና ትቀጥላለች።” ሲሉ ኢትዮጵያ ሳትፈርስ እንደምትቀጥል ራዕያቸውን አስቀምጠዋል።
ዶ/ር አብይ ሲቀጥሉም “ የሃሳብ ብዝሃነትን መቀበል የብሄርብሄረሰብ ብዝህነትን የመቀበል ያህል ለአገራችን ሰላምና ብልጽግና አስፈላጊ” በመሆኑ፣ “ በተፎካካሪዎቻችን ሃሳብ ላንስማማ “ ብንችልእንኳን፤ የሚያሻግረን አዋጭ አማራጭ ግን ሃሳብ እንዳይፈስና ድምጻቸውን ማገድ ሳይሆን፣ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ታግሎ ሃሳባቸውን በላቀ ሃሳብ አሸንፎ መውጣት ብቻ ነው።” ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከእንግዲህ በሚያራምዱት ሃሳብ እንደማይዋከቡና ሃሳባቸውም እንደማይታፈን ተናግረዋል። “የአገር መጻኢእጣ ፋንታ በታሪክ ብቻ አይወሰንም። የተደረገውን በመደጋገምና አዲስ ነገርም በመጣ ቁጥር እንዳልተገራ ፈረስ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ለውጡን የምንገዳደር ከሆነ አገራችን የምትመኘውን ፈጣንና ሁለንተናዊ ለውጥ ማረጋገጥ አንችልም።” ሲሉም ለውጡን ለማይቀበሉ የድርጅታቸው አባላት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አሁን ያለውን ፌደራሊዝም በተመለከተ ሲናገሩ ደግሞ “እንደ ኢትዮጰያ ላለ ፈርጀብዙ ብዘሃነትን የተላበሰች አገር ፌደራሊዝም የተሻለ የአሰተዳደር ስርዓት ነው። የፌደራል መንግስት አወቃቀር ደግሞ የአሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆንይ ኖርበታል። ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ማስተናገድ ከቻልን እንደኛ አገር ላለነባራዊ ሁኔታፌደራሊዝም ተመራጭ የአስታዳደር ስርዓት መሆኑ አያጠያይቅም።” ያሉት ዶ/ር አብይ፣ ክልላዊ አስተዳድሮች ሁሉንም ብሄሮች በእኩልነት የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት እንደሌለባቸውና ይህ ሲሆን ዜጎች በየትኛውም የአገራቸው ክፍልያ ለስጋት ተንቀሳቀስው መስራትና ሃብት ማፍራት የሚያስችላቸውን መተማመን የሚያገኙ በመሆናቸው አብሮነታችን ይበልጥ እየጠነከረ የምናስባትን ጠንካራ አገር መስራት እንችላለን።” ብለዋል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትርክት ውስጥ የብሄር ማንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነት እስካሁን ድረስ ሚዛን ጠብቀው መሄድ ባለመቻላቸውም፣ ሁለቱንም ማንነቶች እንደሚተካኩ ሳይሆን እንደሚተባበሩ ማንነቶች ማየት እንደሚገባ ዶ/ር አብይ ተናግረዋል።
በአገራችን ውስጥ ከፍተኛ የሞራል እና የግብረገብነት ዝቅጠት መኖሩን የገለጹት ዶ/ር አብይ፣
“መሪዎች፣አስተማሪዎች፣ የእምነትአባቶች፣ የአገርሽማግሌዎች፣ ወላጆች፣ ታዋቂሰዎች፣ ፖለቲከኞችና የጎሳ መሪዎች ሁሉ በንጹህ ህሊና፣ በስነምግብር፣ በሞራል ልእልና፣በሃገርና በወገን ፍቅር፣በቃልና በግብር ምሳሌዎች” ሆነው ህዝብን ከጥፋት መታደግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።