መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል። ይህ ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች በከተማው የተለያዩ ቦታዎች በብዛት እንደሚገኙ ይታወቃል። ...
Read More »የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የኢህአዴግን ርዕዮተ-ዓለም በግዳጅ ለሀገር በቀል የሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች በመስጠት ላይ መሆኑ ተሰማ፡
መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኤጀንሲው በአዳማ ስብስባ እንደሚያካሂድና አንድ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ መሪ እንዲገኝ በስልክ በተነገራቸው መሠረት በአዳማ መገኘታቸውን የተናገሩት አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ ምግባረሰናይ ድርጅቶችን አላሰራ ባሉት ሕጎችና አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል የሚል ሃሳብ ይዘው በቦታው ቢገኙም የገጠማቸው ግን ፈጽሞ ያላሰቡት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ ስለሕገመንግስቱ ማለትም የፌዴራል ስርዓት ጠቀሜታ፣ ...
Read More »በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የማውጣት እንቅስቃሴ አልተጀመረም
መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት ተጋፍጠው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ከ2 ሺ ያላነሱ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያንንን ለመመለስ እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም ሲሉ የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኢምባሲው ባቀረበው ጥሪ መሰረት ምዝገባ አካሄዱ ቢሆንም ፣ መቼና እንዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። አንዳንድ አገራት የባህር ...
Read More »የገዢው መንግስት በባህር ዳር ከተማ ያደረጋቸው የምረጡኝ ስብሰባዎች ውጤት አልባ መሆናቸው ተነገረ፡፡
መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና ሙሉዓለም አዳራሽ የተደረገው ስብሰባ የተፈለገውን ግብ ሳይመታ መጠናቀቁን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የብአዴን አባላትን በጥሪ ወረቀት የከተማ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመዞር በስብሰባው እንዲገኙ በመመዝገብና የተለመደውን ማስፈራሪያ በመጠቀም እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በመስጠት የገዢውን መንግስት ...
Read More »ኢ/ር ይልቃል ከአገር አንዳይወጡ የተከለከሉበትን ምክንያት የሚነግራቸው ማጣታቸው ተዘገበ
መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ በደህንነት ሰዎች እንዲሰረዝ ከተደረገ በሁዋላ፣ እስካሁን ድረስ ምክንያቱን የሚነግራቸው አካል መጥፋቱን ሊ/መንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የኢሜግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መስሪያ ቤት ‹‹ፓስፖርቱ እኛ ጋር አልደረሰም፡፡ ቆይተው ደውለው ይጠይቁ›› ብለው ስልክ እንደሰጧቸው የገለጹት ኢ/ር ይልቃል፣ ይህም ሆን ተብሎ ጉዞውን ለማጓተት የተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ...
Read More »በአማራ ክልል ባለሀብቱ እና ነጋዴው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የሚጠበቅበትን ያህል አስተዋጽኦ አላበረከተም ተባለ፡፡
መጋቢት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛውን ድርሻ የሸፈኑት የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውም ተገልጿል። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአባይ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፀሀፊና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሰሞኑን ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፣ በአራት አመቱ ውስጥ በክልሉ የተሰበሰበው ገንዘብ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር አካባቢ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ ከ384 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግስት ...
Read More »በቦሌ አየር ማረፊያ በሚስጢር የተመዘገቡ በርካታ ድርጅቶች በህገወጥ መንገድ እየነገዱ ነው
መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጠው በቦሌ አየር ማረፊያ በሚስጢር ስም የተመዘገቡና ባለቤታቸው ተለይቶ ያልተመዘገቡ ድርጅቶች ካለፉት 10 አመታት ጀምሮ የኮንትራት ጊዜያቸውን ሳያድሱ እና የቤት ኪራይ ክፍያቸውን ለመንግስት ገቢ ሳያደርጉ በመነገድ ላይ ናቸው። በእነዚህ ድርጅቶች ጀርባ የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበትም ምንጮች ጠቁመዋል። የኤርፖርቶች ድርጅት ፣ተከራዮችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚል ምክንያት ...
Read More »የምዕራብ አየር ምድብ የሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪዎች በእኩልነት ያላማከለ የማዕረግ እድገት መስጠቱ በአየር ምድቡ ውስጥ ቅሬታ ፈጠረ
መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ አመጥተዋል እንዲሁም የመቆያ ጊዜያቸውን ሸፍነዋል ለተባሉ የአንድ አካባቢ ተወላጅ ከፍተኛ መኮንኖች፣መሰረታዊ መኮንኖችና ለባለ ሌላ ማዕረግተኞች የማእረግ እድገት ተሰጥቷል። መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በምድቡ ወታደራዊ መዝናኛ ክበብ በተዘጋጀው የማዕረግ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት የምድቡ ታማኝ ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን ፣ ስነስርዓቱ ለሁሉም የሚዲያ ሰዎች ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። ለተሸላሚዎቹ ማዕረግ የሰጡት የምድቡ ...
Read More »ባለፉት 4 አመታት ለአባይ ግድብ የታሰበውን ያክል ገንዘብ መሰብሰብ ሳይቻል ቀረ
መጋቢት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ኃይሎች ያሳተፈ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ባለመቻሉ ለአባይ ግድብ ፕሮጀክት ሕዝቡ በቂ ድጋፍ እንዳያደርግ ተጽኖ አድርጎበታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። የግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 4ኛ ዓመት በዓል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግድቡ ባለበት ጉባ ከተማ በመከበር ላይ ሲሆን ባለፉት 4 ዓመታት ሕዝብን በማንቀሳቀስ ለግድቡ ግንባታ የተሰባሰበው መዋጮ ወይንም የቦንድ ሽያጭ 6 ...
Read More »በደቡብ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙት ከፍተኛ ባለስልጣኖች አልተጠየቁም
መጋቢት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ በነበሩ በአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም ትእዛዝ ያስተላለፉት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፍርድ ቤት ባልቀረበቡበት ሁኔታ፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ ሹማምንት ባለስልጣናት ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል። አቃቢ ህግ ከ55 በላይ የአማራ ተወላጆች እና ...
Read More »