ሚያዝያ፩(አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከሁለት አመታት በፊት ጀምሮ የተነሳውን የማንነት ጥያቄ መርታችሁዋል በሚል የተያዙት ከ150 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍርድ ሳይሰጣቸው በአርባ ምንጭ እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ናቸው። ፍትህ አጥተው ከታሰሩት መካከል አንድ ሰው በህክምና እጦት ህይወቱ ማለፉን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በአካባቢው የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል። ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ...
Read More »የመንግስት አመራሮችና ጋዜጠኞች ከውጭ እና ከውስጥ የሚለቀቀውን ፕሮፖጋንዳ እንዲያከሽፉ አደራ ተጣለባቸው
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ኢህአዴግ የኒዮ ሊበራል አፈቀላጤ የሚላቸውን እነ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማንራይት ዎች እና ሲፒጄ የሚያወጡትን መግለጫ ነቅቶ በመጠበቅ አፍራሽ ጎናቸውን እንዲያጋልጡ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት፤ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አዘጋጆችና አመራሮች ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ከምዕራባዊያን ሀገራት የሚፈልቁ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳዎችን በማጋለጥ ጋዜጠኞች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ...
Read More »በአፋር በሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገደሉ
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር የሰብአዊ መብት ድርጅት ለኢሳት በላከው መረጃ አብሌክ አድአሊ እና ሲዲ ሃቡራ የሚባሉት ጎሳዎች መካከል ከትናንት በስቲያ በተነሳው ግጭት 15 ሰዎች ሲገደሉ፣ 7 ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል። አቶ ጋአስ አህመድ እንደገለጸው ከሶስት ወራት በፊት ከመሬት ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ተባብሶ ባለፈው ሰኞ ደም አፋሳሽ ግጭት ተካሂዷል። በግጭቱም ከአንደኛው ጎሳ 9 ከሌላኛው ደግሞ 6 ...
Read More »ተመላሽ ወታደሮች ስርአቱን እንዲታደጉ የብአዴን አመራሮች ተማጽኖ አቀረቡ
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኖቹ በባህርዳር ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የተመላሽ ሰራዊት አባላትን ሰብስበው ስርአቱ አደጋ ውስጥ በመግባቱ እንዲታደጉት ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ከምርጫው ጋር ተያይዞ ልማቱን ለማስቀጠል አደጋ ውስጥ ገብተናል ያሉት ባለስልጣናቱ፣ የተቀናሽ ሰራዊት አባላት በምርጫው ንቁ ተሳተፎ በማድረግ ስርአቱን እንዲታደጉ ተማጽነዋል። የሰራዊቱ አባላት “የቦታ ባለቤት እናደርጋችሁዋለን” ተብሎ ቃል የተገባላቸው ሲሆን፣ የፊታችን ቅዳሜ የመሬት ጥያቄያቸው መልስ እንደሚያገኝ ተገልጾላቸዋል። ...
Read More »አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለምርጫ ቅስቀሳ በሄዱበት ከፍተኛ ጫና እንደደረሳበቸው አስታወቁ
መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ9 ፓርቲዎች ትብብር ስር የሚንቀሳቀሰው የከምባታ ህዝቦች ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ወደ ትውልድ ቀያቸው አንገቻ ወረዳ ቢያቀኑም፣ የወረዳው አመራሮች ከፍተኛ ችግር እንደፈጠሩባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ወደ ወረዳው በመሄድ የምርጫ ፖስተሮችን ሲለጥፉ እንደተቀደደባቸው፣ የተከራዩትን ቤት እንዲለቁ መገደዳቸውን የገለጹት አቶ ኤርጫፎ ይባስ ብሎ ከተማው ውስጥ ሆቴል ለመያዝ ሲጠይቁ፣ ባለሆቴሎቹ “አታከራዩ” ተብለናል በሚል ...
Read More »የየመን አማጽያን ኤደንን ለመያዝ መቃረባቸው ተሰማ
የየመንን ዋና ከተማ ሰንአን በመቆጣጠር ሁለተኛዋን ታላቋን ከተማ ኤደንን ለመቆጣጠር ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመፋለም ላይ የሚገኙት የሃውቲ ሚሊሺያዎች፣ ከሳውድ አረቢያ የሚደርስባቸውን የአየር ጥቃት ተቋቁመው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር መቃረባቸውን መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። አማጽያኑ በሚደርስባቸው የአየር ጥቃት ሳይበገሩ፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ታማኝ ወታደሮች በመፋለም ላይ ናቸው።አሜሪካ ለሳውድ አረቢያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ መሆኗን ገልጻለች። ኢራን በበኩሉዋ ተዋጊ መርከቦቿን ወደ አካባቢው ልካለች። ...
Read More »ገዢው ፓርቲ የጦርነት ያክል ዘምቶብናል ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናገሩ
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው። አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ በማውጣት አባሎችን ማስፈራራታቸውን ፣ ግንጭ ...
Read More »በአለማቀፍ ድርጅቶች እርዳታ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመለሱ
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል። ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው። በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል አንድ እርጉዝ ሴት እና 37 ...
Read More »በሻውራ ከተማ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተከስቷል
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሻውራ ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ውሃ በማጣታቸው መቸገራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ለመግዛት ተገደናል የሚሉት ነዋሪዎች ምክንያቱም ሙስና ነው ይላሉ። የወረዳው መስተዳደር 300 ሺ ብር የተገዛውን ጄኔረተር 800 ሺ ብር እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ጄኔረተሩ በተሰራ ማግስት መበላሸቱን ...
Read More »የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር ከደቡብ ሱዳን መንግስት ድጋፍ እንዳገኘ ተደርጎ የሚቀርበውን ዘገባ አጣጣለው
መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን የግንባሩን ሊቀመንበር ተዋት ፖል ቻይን ጠቅሶ እንደዘገበው ፣ የደቡብ ሱዳን አማጽያን፣ የሳልቫኪር መንግስት ለኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና፣ የገንዘብ እንዲሁም የሎጅስቲክ ድጋፍ ያገኛል በሚል ያቀረበው ወቀሳ ተቀባይነት የሌለው ነው። አማጽያኑ የፖል ቻይ ጦር ወደ ጋምቤላ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም አስቧል በማለት ክስ አሰምተው ነበር። ፖል ቻይ በደቡብ ሱዳን ፖለቲካ ውስጥ ...
Read More »