በአፋር በሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገደሉ

መጋቢት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር የሰብአዊ መብት ድርጅት ለኢሳት በላከው መረጃ አብሌክ አድአሊ እና ሲዲ ሃቡራ የሚባሉት ጎሳዎች መካከል ከትናንት በስቲያ በተነሳው ግጭት 15 ሰዎች ሲገደሉ፣ 7 ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል።

አቶ ጋአስ አህመድ እንደገለጸው ከሶስት ወራት በፊት ከመሬት ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ተባብሶ ባለፈው ሰኞ ደም አፋሳሽ ግጭት ተካሂዷል። በግጭቱም ከአንደኛው ጎሳ 9 ከሌላኛው ደግሞ 6 ሰዎች መሞታቸውን የገለጹት አቶ ጋአስ የግጭቱ መንስኤ ከመሬት ባለፈ የጠመንጃ መስፈታት አጀንዳም እንዳለው ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት አካባቢውን መቆጣጠራቸውን የገለጹት አቶ ገአስ፣ የአካባቢውን ህዝብ መሳሪያ ማስፈታታቸውን ገልጸዋል።

ችግሩን አስቀድሞ መፍታት ሲገባ እዚህ ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ መጠበቁ አሳዛኝ መሆኑም አክለው ተናግረዋል።