ኢሳት ዜና (ሰኔ 28 2007 አም) የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታ ሲከታተል የቆየው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የካሳ ክፍያ በመፈጸም አቶ አንዳርጋቸውን በአስችኳይ እንዲፈታ ማሳሰቡን አለማቀፍ ሚዲያዎች ዘገቡ። ባለስምንት ገጽ ውሳኔውን በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በኩል ለኢትዮጵያ ያቀረበው ድርጅቱ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእስር ቤት ቆየታቸው ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰባዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው መግለጹን ዘ-ፋይናንሺያል ኤክስፕረስ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። በድርጅቱ የስቃይ ሰለባ ...
Read More »ኢሳት ቴሌቪዥን ስርጭቱን በአዲስ ሳተላይት እንደገና ጀመረ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ወር በላይ ተቋርጦ የነበረው የኢሳት ቴሌቪዥን አገልግሎት በአዲስ ሳተለይት ስራ ጀምሯል። ከኢህአዴግ መንግስት በሚደርስበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ ስርጭቱ በተደጋጋሚ ሲቋረጥ የቆየው ኢሳት ቴሌቪዥን ኤ ኤም 44 በሚባል ሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭቱን ከትናንት ሰኔ 25፣ 2007 ዓም ጀምሮ እንደገና ጀምሯል። በአለማቀፍ የፕሬስ ድርጅቶች ሳይቀር ሃሳብን በማፈን የሚወነጀለው የኢህአዴግ መንግስት የኢሳትን ስርጭቶች በቀጥታ ...
Read More »የጦር መሳሪያቸውን ያስመዘገቡ ሰዎች አስገዳጅ መመሪያ ተላለፈባቸው
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የኢህአዴግ መንግስት የግል የጦር መሳሪያ የያዙ ዜጎች ህጋዊ ፈቃድ ከመንግስት በመውሰድ፣ የጦር መሳሪያቸውን እንደንብረት እንዲይዙ አዲስ መመሪያ በማውጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች መሳሪያዎቻቸውን እያስመዘገቡ ፈቃድ ውሰደዋል። ይሁን እንጅ ገንዘብ እየከፈሉ ፈቃድ የወሰዱ ባለንብረቶች፣ በራሳቸው ገንዘብ የገዙትን መሳሪያ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌላ ሰው ማውረስ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። መሳሪያውን የሸጠ፣ ያወረሰ ወይም የጠፋበት ሰው ...
Read More »መንግስት በተለያዩ የሙያ ትምህርቶች አሰለጥናችሁዋላሁ በማለት የወሰዳቸው ተማሪዎች አብዛኞቹ ተበተኑ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ አመት በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ አሰማራችሁዋለሁ በሚል መንግስት ካሰበሰባቸው ከ2 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው በተለያዩ የመከላከያ ተቋማት ቢመደቡም፣ ቃል የተገባላቸው እና በተግባር የሚያዩት ነገር ባለመጣጣሙ ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸውን ሰልጣኖች ተናግረዋል። አሚባራ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ጫካ መንጥረው ህንጻ በመስራት ስልጠና የጀመሩ ወጣቶች እንደሚሉት፣ ...
Read More »ወጣት ሳሙኤል አወቀን ገድሏል የተባለው ሰው ቃል የግድያውን ድራማ ያመለክታል ተባለ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም አደራጅ የሆነውን የወጣት ሳሙኤል አወቀን ገዳይ በ19 አመታት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል። ይሁን እንጅ ገዳይ ተብሎ የቀረበው አቶ ተቀበል ገዱ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል እና ፖሊስ በወቅቱ የሰጠው መግለጫ ሊጣጣሙ አልቻሉም። ገዳይ ተብሎ የቀረበው ሰው ለፍርድ ቤቱ ግድያውን የፈጸመው መጠጥ ቤት አብረው ...
Read More »ሜሮን አለማየሁ ተፈረደባት!
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› ወንጀል የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈርዶባታል፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት ክስ ፣ በዋስ ...
Read More »የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ወጣ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ስምንተኛ ክፍል ያልደረሰ/ች ሠራተኛ ወደውጭ ሀገር መላክ የሚከለክል ሲሆን በሥራው የሚሰማሩ ኤጀንሲዎች ወደ 2 ሚሊየን ብር ወይም 100 ሺ ዶላር ለዋስትና ማስከበሪያ ካላስያዙ ወደስራ እንዳይገቡ ክልከላ አስቀመጠ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅቁጥር 632/2001 ሙሉ በሙሉ የሚሰርዘው ይህ ረቂቅ አዋጅ በቀድሞ አዋጅ ፈቃድ የተሰጣቸው ኤጀንሲዎች ...
Read More »በምስራቅ ጎጃም ዞን ከምርጫ ጋር በተያያዘ አርሶ አድሮች እየታሰሩ ነው
ኢሳት ዜና (ሰኔ 26 2007) በቅርቡ በምስራቅ ጎጃም ዞን በወጣት እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በመታሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ ። በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከ 15 አምት በፊት ያልከፈላቹት የማዳበሪያ እዳ አለባችሁ እየተባሉ በጅምላ መታሰራቸውን የተናገሩት እማኞች ገበሬዎቹ በሞት የተላዩዋቸውን ዘመዶች እዳ ጭምር እንዲከፍሉ መገደዳቸውም ታውቋል። የዞኑ ባለስልጣናት የማዳበሪያ እዳን ምክንያት ...
Read More »ከምርጫ 2007 በሁዋላ በስፖርታዊ ውድድሮች የተለያዩ የተቃውሞ ክስተቶች እየታዩ ነው ተባለ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በድንገት በተጠራው ስብሰባ ኮሚሽነር ያየህ አዲስ ፣ የብሄራዊ ሊጉ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ከተሞች ከምርጫ 2007 በኋላ የሚታዩ የስፖርታዊ “ጨዋነት ጉድለቶች” አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የምርጫ ውጤት ይፋ የሆነበት በመሆኑ በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግም ተናግረዋል። ኮሚሽነር ያየህ ” ዛሬ በስፖርት ሜዳ የሚታየው ተቃውሞ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፓርላማ የምርጫ ቦርድ ቁልፍ ሰው የነበሩትን ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔርን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮምሽን ኮምሽነር አድርጎ ሾመ፡፡
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ቢሆኑም ከህወሃት/ኢህአዴግ ቀጥተኛ መመሪያ በመቀበልና በማስፈጸም ረገድ ቁልፍ ሰው መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች እንዲዳከሙና ትንንሽ ልዩነቶቻቸውን በማጦዝ ፓርቲዎች እንዲናጉና እንዲፈርሱ ከኢህአዴግ ጋር እየተናበቡ የሚሰሩ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያቀርቡትንም አቤቱታ በማድበስበስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃና፤ ዶ/ር አዲሱ የሚሰጡዋቸውን ...
Read More »