የዋጋ ግሽበቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ

ሐምሌ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ የዋጋ መረጃው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም የሸቀጦች ዋጋ ካለፈው ጋር ሲነጻጸር መጨመሩን ይፋ አደረገ፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሰረት በግንቦት ወር 9 ነጥብ 4 በመቶ የነበረው የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የዋጋ ግሽበትን ወደአንድ አሃዝ አውርጃለሁ በማለት ባለፉት ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ ለፓርላማ አባሎች እንደተናገሩት የኤርትራ መንግስት አካባቢውን የማተራማስ አጀንዳውን ካላቆመ ፣ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ሻእቢያ ኢትዮጵያና ጅቡቲን ለማተራመስ እየሰራ ነው ሲሉ ከሰዋል። የኢትዮጵያን ህዝብ አስታውቀን እርምጃ እንወስዳለን ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ እስካሁንም ለደረሰብን ጥቃት ተመጣጣኝ እርምጃ ስንወስድ ቆይተናል ሲሉ አክለዋል። የአቶ ሃይለማርያም መግለጫ በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት7 ...

Read More »

በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ 82 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ ፑትላንድ ራስ ገዝ ዋና ከተማ ጋሮው በከባድ መኪና ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ የነበሩትን ሰማንያ ሁለት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና የተሽከርካሪውን ሹፌር አብሮ መያዙን የፑትላንድ ፀጥታ ሹም ኃላፊ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከአስር ሽህ በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች በመሳፈር ባሕር አቋርጠው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሰላምዋ እርቋት በጦርነት ምስቅልቅል ውስጥ ...

Read More »

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃወሙት

ሰኔ ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለማቀፍ ታላላቅ የመገኛኛ ብዙሃን አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር እና የመድረክ የፖለቲካ ማህበር አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና ´´አሜሪካ አምባገነኖችን የምትደግፍም ሃገር መሆኗን በምሳሌ አስደግፎ ማስረዳት ...

Read More »

አረብ አገር ትሄዳላችሁ ተብለው የተሰበሰቡ ወጣቶች በግድ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መጓዛቸው ተሰማ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 3 ቀናት ወደ አረብ አገር እንወስዳችሁዋለን በሚል የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ ለማጓጓዝ መሞከሩን ወጣቶች ተናግረዋል። ወጣቶች እንዳሉት ወደ አረብ አገራት ትሄዳላችሁ ተብለው ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም እያጓጓዙ ሲሆን፣ አንዳንዶች መንገድ ላይ ጠፍተዋል። ካለፈው አመት ጀምሮ ወታደሮችን ለማሰልጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ የነበረው የኢህአዴግ መንግስት ፣ ከወጣቱ ...

Read More »

ከፍተኛው ፍርድ ቤት እነ አቶ አቡበክር አህመድን ጥፋተኞች ናቸው ሲል ወሰነ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 18 የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በሙሉ ጥፋተኞች ሲባሉ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤት ለሃምሌ 27 ቀጠሮ ሰጠ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በ አቶ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሀመድ አባተ፣ አህመድ ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጠየቀ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ካውንስል፣ ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ በአስቸኳይ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል እንድትለቃቸው ጠይቋል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው የተመድ የሰብአዊ መብት ካውንስል በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በጭካኔ የተሞላ አካላዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙባቸው የሚያትቱ ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዳሉት ለኢህአዴግ መንግስት በላከው 8 ገጽ ደብዳቤ ላይ ማስፈሩን ጋዜጣው ዘግቧል። በሪፕሪቭ የህግ ክፍል ...

Read More »

በዘይሴ ቀበሌ አንድ ግለሰብ 4 የመንግስት ሹሞችን ገደለ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ዘይሴ በሚባል ቀበሌ፣ ከ4 ቀናት በፊት አንድ ግለሰብ ከመሬት ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የመሬት አስተዳደር ሃላፊውን ጨምሮ ሌሎች 3 የወረዳ ሹሞችን ገድሏል። ግለሰቡ በ2007 ምርጫ የተቃዋሚ አባሎችን ደግፈሃል በሚል የያዘውን መሬት እንዲለቅ የመሬት አስተዳዳር ሃላፊው በጠየቁት ጊዜ፣ ” ከአባቴ ያገኘሁትን የውርስ መሬት አልለቅም” በማለት መመለሱን ተከትሎ፣ የመሬት ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት የስለላ ስራ ለሚሰራለት ለአንድ ኩባንያ ብቻ 1 ሚሊዮን ዶላር ከፈለ

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጣሊያን ውስጥ የሚገኘውና ሃኪንግ ቲም ” hacking team” በመባል የሚታወቀው ለደህንነትና ለስለላ የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር ሶፍት ዌሮችን የሚሸጠው ድርጅት፣ የራሱ መረጃዎች በሌሎች ሃይሎች የተዘረፈ ሲሆን፣ እስካሁን ይፋ በሆኑት መረጃዎችን ቢንያም ተወልደ የተባለ ኢትዮጵያዊ በብሄራዊ ስለላ ድርጅት ስም 1 ሚሊዮን ዶላር በአንድ ጊዜ መክፈሉን የወጣው ሰነድ ያመለክታል። ገንዘቡ የተከፈለው በቀጥታ ከመንግስት የስለላ ተቋም ...

Read More »

የሸህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ ንብረት ከሆነው ከሚድሮክ ጎልድ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መንግስት ማጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሲያጋልጥ፤ ሚድሮክ ጎልድ በበኩሉ 10 ሳንቲም ዕዳ የለብኝም ሲል አስተባበለ።

ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ግን ማስተባበያውን አጣጥለውታል። የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት፣ የማዕድን ሚኒስቴር የሼክ መሐመድ አል አሙዲ የወርቅ ልማት ኩባንያ ከሆነው ሚድሮክ ጐልድ በሕግ የተወሰነውን ገቢ ባለመሰብሰቡ፣ አገሪቱ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ አጥታለች ማለቱ ይታወሳል። ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ በማዕድን አዋጁ 78/2002 መሠረት በከፍተኛ ...

Read More »