ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ አርብ ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ወሊሶ መዛመቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች በከተማዋ የተዘረጋን ዋና መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ሲያቀርቡ መዋላቸው ታውቋል። በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች በሚገኙ የገጠር ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አርብ የቀጠለ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በምዕራብ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እንዲሁም ...
Read More »በደብረብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ
ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ-ብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በትንሹ 14 ሰዎች መገዳላቸውን ፖሊስ አርብ አስታወቀ። አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከሌላ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው ሊደርስ መቻሉንና፣ ሌሎች ሶስት ሰዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፅኑ በመጎዳታቸው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ...
Read More »በኦሮምያ ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ ዋለ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 4 ወራት በተከታታይ ሲደረግ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል።ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ሰራዊት በሰፈነበት ምእራብ ሃረርጌ፣ሀብሩ ወረዳ ዴፎ ከተማ ህዝቡ ለተቃውሞ በመውጣት፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት ጥያቄዎችን ሲጠይቅ አርፍዷል።በወለጋ ሆድሮጉድሩ የሻምቡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በክልሉ የሚገኙ በርካታ ትምህርትቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣መንግስት ትምህርት ቤቶችን መክፈት ለተጨማሪ ...
Read More »የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች የሚያወግዝ ተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል፣ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ግልሰቦችን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችን ዛሬም በሁመራ ከተማ አዘጋጅቷል። ይኸው በክልሉ መንግስት የሚቀነባበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የአማራ ማንነቱ ይከበርለት በማለት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥያቄውን እንደገና ባነሱት የወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ነው። የወልቃይትን ህዝብ ተወካዮች ” ማንነታቸው ከአማራ ህዝብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ፣ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አካሄዱ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መብታቸው እንዲከበርላቸው ለአመታት ሲጠይቁ የቆዩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአርብ ቀን ጸሎት በሁዋላ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን በመልቀቅ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።ፍልውሃ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ “ጭቆናን እንታገላለን፣ ኮሚቴው ይፈታ ፣ ድራማው ይብቃ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ተለቀዋል።
Read More »የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የእሰረኞች ሰንድ እንዳይወጣ አገደ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፌደራል አቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠይቆባቸው ጉዳያቸውን ከከቃሊቲ እስር ቤት በመመላለስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት የቀድሞው አንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ማዕከል፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ማስረጃ ላይ የሰነድ አስተያየታቸውን ለማቅረብ ያዘጋጁትን ጽሁፍ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይወጣ እንደከለከላቸው ገለጹ፡፡ ከእስር ተፈቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኘው የቀድሞው ...
Read More »ቻይናዊያን በሕገወጥ የችርቻሮ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች መስራት አልቻልንም አሉ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዲናችን አዲስ አበባ በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች በቻይናዊያን የሕገወጥ ንግድ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ ተናገሩ። ባለፉት ሶስት ዓመታት የውጭ ዜጎች በሚበዙበት በቦሌ ሩዋንዳ ለምግብ ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶች በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በሕገወጥ የቻይኖች ዜጎች አካባቢያችን ተወሮ ሱቃቸውን ለመዝጋት እየተገደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቦሌ ሩዋንዳ በሚኒ ...
Read More »በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተታውሞ አድማሱን አስፍቶ ቀጥሏል
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሃሙስ በበርካታ አካባቢዎች መዛመቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የመንግስት ባለስልጣናት ተቃውሞን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃን እንደሚወስዱ ቢያሳስቡም ህዝባዊ ተቃውሞው በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል። በየአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በመቃወም ድርጊቱን ሲያወግዙ መዋላቸው ተገልጿል። ይሁንና፣ የጸጥታ ...
Read More »አስቸኳይ የምግብ እንክብካቤን የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር 6 ሚሊዮን መድረሱን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ አስቸኳይ የምግብ እንክብካቤን የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ። በድርቁ ሳቢያ እርዳታን ይፈልጉ የነበሩ የአምስት ሚሊዮን ህጻናት ቁጥርም ወደስድስት ሚሊዮን ያደገ ሲሆን ድርቁ በመባባስ ላይ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። አስቸኳይ የምግብ ድጋፍን ከሚፈልጉት ስድስት ሚሊዮን ህጻናት መካከልም ከ430ሺ በላይ የሚሆኑት ልዩ የነብስ-አድን የምግብ እንክብካቤን ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ መንግስት አስፈላጊውን የሃይል እርምጃ እንደሚወስድ ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ያለውን የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ለማስቆም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ሃሙስ በድጋሚ ገለጠ። የመንግስት ባለስልጣናት የተጀመረውን የሃይል እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቢልጹም፣ በክልሉ ተቃውሞው ዳግም በመዛመት ላይ መሆኑን የተለያዩ አካላት አስታውቀዋል። ተቃውሞው ዳግም ማገርሸቱን ተከትሎም የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከተቃውሞው ጀርባ የውጭና የውስጥ አካላት አሉ ሲሉ የገለጻቸውን አካላት በስም ...
Read More »