(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 20/2011) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ተጠሪዎች፣ የአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ሹመት እንደሚሰጥ አስታወቀ። ሹመቱ ከፖለቲካ ታማኝነት ይልቅ እውቀት፣ ልምድና እንዲሁም በህብተረሰቡ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት ያላቸው ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች እንደሚገኙበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ አቶ መለስ ዓለም በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት አዳዲሶቹ አምባሳደሮች በተልዕኳቸው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። በውጭ ...
Read More »የሰራዊቱ አባላት ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 20/2011)ከወር በፊት ያለ ፈቃድ ወደ ቤተመንግስት የተንቀሳቀሱ ወታደሮችን ያስተባበሩ የሰራዊቱ አባላት ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከወታደራዊ ዲሲፒሊን በማፈንገጥና ሕግን በመጣስ የተንቀሳቀሱትን ወገኖች በሕግ ተጠያቂ ማድረግ ነገ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጸም ይከላከላል ሲሉ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ገልጸዋል። በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የፍትህ ጉዳዮች ከፍተኛ ሃላፊ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ኪዱ አለሙ ለመከላከያ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት መረጃ የመሰብሰቡ ስራ ተጠናቆ ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ...
Read More »በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 20/2011)በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ያለው ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ገለጹ። ዘርን መሰረት ያደረገ በሚመስለው ግጭጥ አሁንም በተማሪዎች መካከል መከፋፈልና ድንበርን አስቀምጡ የማስፈራራቱ ሒደት መቀጠሉንም ተማሪዎቹ ይናገራሉ። እንደተማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ በዩኒቨርስቲው ተመድበው ከነበሩት አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ መጡበት ተመልሰዋል።–አሁን ያሉትም ቢሆኑ መሄጃ ትራንስፖርት እየተጠባበቁ መሆኑን ይናገራሉ። በግቢው ውስጥ ያሉት ተማሪዎችም ቢሆኑ በዩኒቨርስቲው ይውላሉ እንጂ አዳራቸው ግን ሌላ ቦታ ነው። ይህ ...
Read More »በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ቡድን ሕዝባዊ ውይይት ሊያካሂድ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 19/2011)በአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በአምስት የሰሜን አሜሪካ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት እንደሚያካሄድ የዝግጅቱ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ገለጹ። አስተባባሪዎቹ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ሕዝባዊ ውይይቱ የሚካሄደው ስለተጀምሩ ሃገራዊ ለውጦችና ስለ ኢንቨስትመንት ከኢትዮጵያያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ነው። በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሕዝባዊ ውይይት የሚያደርግባቸው አምስቱ የአሜሪካ ከተሞች ...
Read More »አብዴፓ 12 አመራሮችን ከሃላፊነት እንዲነሱ ወሰነ
(ኢሳት ዲሲ– ህዳር 19/2011)የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አብዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የክልሉን ፕሬዝዳንት ጨምሮ 12 አመራሮችን ከሃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ አስተላለፈ። የክልሉ ፕሬዝዳንት ውሳኔውን አልቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል። ትላንት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ እንዲሰናበቱ ውሳኔ የሰጠባቸው አመራሮች ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በአዲስ አበባ የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ክልሉ በወጣት አመራሮች መተካት አለበት የሚል አቋም ላይ ደርሰው ...
Read More »ኦዴግና ኦዴፓ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 19/2011)በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው ኦዴግ በጠቅላይ አብይ አህመድ ከሚመራው ኦዴፓ ጋር ለመዋሀድ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንትና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ስምምነቱን ፈርመዋል። ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመከፋፈል ይልቅ ተሰባስቦ መስራቱ የበልጥ ትርጉም ይኖርዋል በማለት መግለጫ የሰጡት አቶ ለማ መገርሳ እለቱን ታሪካዊ ሲሉ ገልጸውታል። በሃይማኖት በሰፈርና በጎሳ የተከፋፈሉ ...
Read More »በአንድ ብሔር ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፖለቲካዊ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 17/2011) በትግራይ ክልል የ8 ከተሞች ነዋሪዎች ባንድ ብሔር ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፖለቲካዊ ጥቃትን እንቃወማለን ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በፌዴራል መንግስት የትግራይን ህዝብ ለማንበርክ የሚደረግ ሴራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢትዮጵያ ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም በነበረ ጊዜ በትግራይ ክልል አንድም ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ አለመካሄዱ ይታወሳል። በትግራይ በሚገኙ 8 ከተሞች የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ መንግስት በቅርቡ የወጣውን የአቋም ...
Read More »የሜቴክ ዳይሬክተር የስራ መልቀቂያ አቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 17/2011) አወዛጋቢው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተሾሙት ዶክተር በቀለ ቡላዶ የስራ መልቀቂያ አቀረቡ። ምክትል ዳይሬክተሩ ብርጋዴር ጄኔራል አህመድ ሃምዛ በምትካቸው መሾማቸውም ተመልክቷል። ሜቴክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው ገንዘብ16 ቢሊየን ብር መድረሱም ተገልጿል። የባንኮችን ሕጋዊ አሰራር በመጣስ አለም አቀፍ ግዢዎችን ያለጨረታ እንዲያከናውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተባባሪ ሆኖ መቆየቱንና ብሔራዊ ባንክም በዝምታ መመልከቱን መረዳት ...
Read More »የክልል ጥያቄዎች እየተበራከቱ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 17/2011)በደቡብ ኢትዮጵያ ተጨማሪ የክልል ጥያቄዎች በመቅረብ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። ጥያቄዎቹ እየቀረቡ ያሉት የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ወደ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያመራ የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው ተብሏል። 56 ብሔረሰቦች የሚገኙበትና በ9 ዞኖች በተዋቀረው የደቡብ ክልል ከሲዳማ ዞኖች በተዋቀረው የደቡብ ክልል ከሲዳማ ዞን በተጨማሪ ከወላይታ፣ከከፋ፣ከከምባታ እንዲሁም ከጉራጌ የክልል ጥያቄ እንደቀረበለት ታውቋል። በደቡብ ክልል ምክርቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ሔለን ደበበ ...
Read More »የሶማሌ ክልል በጀት በከፍተኛ መጠን ሲዘረፍ ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 17/2011) የሶማሌ ክልል በጀት በህወሃት ባለስልጣናትና ባለሃብቶች በከፍተኛ መጠን ሲዘረፍ ነበር ተባለ። በኮንትራት ተቋራጭነት ስም የህወሃት ባለስልጣናት በቢሊየን የሚቆጠር የክልሉን በጀት ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች መውሰዳቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሰሞኑን በተለያዩ ዞኖች ባደረጉት የስራ ጉብኝት ወቅት ክልሉ ከፍተኛ የበጀትና የመሬት ዘረፋ እንደተፈጸመበት ማረጋገጣቸውን ነው የፕሬዝዳንቱ የህግ አማካሪ ለኢሳት የገለጹት። ሜቴክ የ1ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ተዋውሎ ገንዘቡን በሙሉ ...
Read More »