(ኢሳት ዜና–ሕዳር 20/2010)በምስራቅ ሀረርጌ በተለያዩ ከተሞች በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ። በአዳማ ናዝሬት ዛሬ በተቀሰቀሰው ግጭት 2 ነዋሪዎች በአጋዚ ሰራዊት መገደላቸው ታወቋል። በምስራቅ ሀረርጌ ጨለንቆ፣ ጉርሱም፣ በደኖና ባቢሌ ህዝባዊ አመጽ ተነስቶ ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት መፈጠሩንም የደረሰን ዜና ያመለክታል። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው። በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉም ታውቋል። የህወሃት ደህንነቶች በኦነግ ስም ወጣቶችን እየመለመሉ በማሰር ላይ ...
Read More »የሶማሌ ተወላጆችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሶማሌ ክልል ፍቃደኛ አይደለም ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 20/2010)በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጆችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሶማሌ ክልል ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተገለጸ። በቁጥጥር ስር ለማዋል ተባባሪ ያልሆኑ የሶማሌ ክልል አመራሮች ርምጃ እንዲወሰድባቸው ተወስኗል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ለወራት በዘለቀውና አሁንም መብረድ ባልቻለው ግጭት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ የሶማሌ ክልል አመራሮች ርምጃ እንዲወሰድባቸው መወሰኑን የዘገበው በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው። ውሳኔውን ያሳለፈው ...
Read More »ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ሌሎች የሳውዲ ባለሃብቶችና ልኡላን በዚህ ወር መጨረሻ ሊፈቱ ይችላሉ ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 20/2010)ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሳውዲ ባለሃብቶችና የልኡላን ቤተሰቦች በዚህ ወር መጨረሻ ሊፈቱ እንደሚችሉ አንድ የሳውዲ ባለስልጣን ገለጹ። ከታሰሩት ውስጥ 95 በመቶው በድርድር ለመውጣት ፈቃደኛ መሆናቸውንም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። በድርድሩ መሰረትም የተወሰነውን የሃብታቸውን መጠን ወደ ሳውዲ መንግስት ግምጃ ቤት ማስገባት እንደሚጠበቅባቸውም ተመልክቷል። እጅግ ውድና ዘመናዊ በሆነው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ውስጥ የታሰሩት ባለሃብቶች በቁጥር 201 ...
Read More »በሊቢያ አፍሪካውያን ስደተኞች እንደሚሸጡ፣እንደሚለወጡና እንደሚገደሉ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 20/2010)በሊቢያ በአንድ ሳምንት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች እንደሚሸጡ፣እንደሚለወጡና እንደሚገደሉ ታወቀ። በመንግስታቱ ድርጅት የፈረንሳይ አምባሳደር እንዲህ አይነቱን ህገወጥ ድርጊት ድርጅቱ ማስቆም አለበት በህገወጥ ድርጊቱ ተሳታፊዎች ላይም ማዕቀብ መጣል አለበት ብለዋል። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ጥርስ አልባው የአፍሪካ ህብረት ግን በአቢጃን ኮትድቯር ከአውሮፓ ህብረት ጋር የጋራ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ነው። በሊቢያ እየተካሄደ ያለው የባሪያ ንግድ ከሁለት ሳምንት በፊት በሲ ኤን ...
Read More »የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ርምጃ የወሰደው በክልሉ አመራሮች ላይ ብቻ ነው ታባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 20/201)የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ማዕከላዊ ኮሚቴ በመቀሌ ሲያካሂድ በቆየው ስብሰባ ከፍተኛ ግምገማ ያደረገውና ርምጃ የወሰደው በዋናነት በትግራይ ክልል በሃላፊነት ላይ በሚገኙ አመራሮች ላይ መሆኑን ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። አቶ አባይ ወልዱ ከፓርቲው ሊቀመንበርነትና ስራ አስፈጻሚነት የተነሱት የትግራይና የአማራ ክልልን ወሰን ውዝግብ በቶሎ ባለመቅጨት ትግሬዎችን ለጥቃት አጋልጠሃል በሚል እንደሆነም ተመልክቷል። ከወሰን ውዝግቡ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ...
Read More »በቦረና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 19/2010) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወገን ቀርቶ በጠላት ላይ የማይደረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል ሲል የቦረና አስተዳደር ቅሬታውን አቀረበ። ድርጊቱን የፈጸሙ የመከላከያ አባላት ተላልፈው እንዲሰጡና ለህግ እንዲቀርቡም ጠይቋል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቦረና ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በሕዳር 14/2010 ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ለመከላከያ ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጻፈው ደብዳቤ የመከላከያ ሰራዊት ያደረሰውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በዝርዝር አስፍሯል። ደብዳቤው በቦረና ዞን ድሬ ...
Read More »የሕወሃትን አገዛዝ የሚያወግዙ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እንደቀጠሉ ነው
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 19/2010) የሕወሃትን አገዛዝ የሚያወግዙ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተነገረ። የሃሮማያና የጅማ ዩኒቨርስቲ ተመሪዎች በተቃውሞ ላይ ናቸው። 35ሺ የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ሲወጡ የጅማዎቹ ደግሞ ከግቢያቸው እንዳይወጡ ታግተዋል። በጋሞጎፋ ዞን ሳውላ፣አወዳይ እንዲሁም በወለጋ ሕዝባዊ ተቃውሞው እንደገና ተቀጣጥሏል። በኢትዮጵያ የሕወሃትን የ26 አመታት አገዛዝ ለማክተም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ይገኛል። በጋሞጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በግብር የተንገሸገሸው ነዋሪ የገቢዎችና ...
Read More »የኬንያ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ፈጸሙ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 19/2010) የኬንያ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ቃለ መሃላ ፈጸሙ። ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ግን ኬንያታ የተመረጡት ዝቅተኛ ቁጥር ባላቸው ድምጽ ሰጪዎች በመሆኑ በሚቀጥለው ወር ራሳቸው የፕሬዝዳንትነት ቃለመሃላ እንደሚፈጽሙ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል። ከሁለት አጨቃጫቂ ምርጫዎች በኋላ የኬንያ ፕሬዝዳንትነትን መንበር ለሁለተኛ ጊዜ የተቆጣጠሩት ኡሁሩ ኬንያታ ቃለ መሃላቸውን ሲፈጽሙ ተቃዋሚዎች በስነስርአቱ ላይ አለመታደማቸው ታውቋል። ኬንያታ በንግግራቸው ሁሉን አቀፍ ስሜት ለመፍጠር በተቃዋሚዎች ...
Read More »የኢሳት 7ኛ አመት በኮሎምቦስ ኦሃዩ ተከበረ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 19/2010)የኢሳት 7ኛ አመት በኮሎምቦስ ኦሃዩ በድምቀት ተከበረ። በበአሉ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልና የኢሳት ድርሻ በሚል ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ቅዳሜ ህዳር 25/2017 በኦሃዩ በተከበረው የኢሳት 7ኛ አመት ላይ ከኦሃዩና አካባቢዋ፣ከሴንሴናቲ፣ከዴይተን፣ክሊቭላንድና ኢንዲያና ግዛት የመጡ የኢሳት ደጋፊዎች ተሳትፈዋል። በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ኮመዲያን ክበበው ገዳና የኢሳት ባልደረባው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ሲሆኑ ኮመዲያን ክበበው ገዳ ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር። ...
Read More »ሰላም ባስ ገራዥ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር19/2010)በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ገራዥ ላት ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። አቃቢ ህግ ግለሰቦቹ ድርጊቱን የፈጸሙት በአርበኞች ግንቦት ሰባት ትዕዛዝ ነው ሲልም አመልክቷል። አርብ ሕዳር 15/2010 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች አንተነህ ፋንታሁን፣ኤርሚያስ አለባቸው፣አንድነት ፋንታሁን፣ፍስሃ እያዩና ብርሃኑ ሞገስ የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ተመልክቷል። እኒዚህ በክሱ ላይ የተዘረዘሩት ...
Read More »