የህግ የበላይነትን ማስከበር ያለበት ሃይል የኦሮሞ ህዝብን መግደሉ ተቀባይነት የለውም ተባለ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) የህግ የበላይነት ማስከበር ያለበት ሃይል የኦሮሞ ህዝብን መግደሉ ተቀባይነት እንደሌለውና ለህግ እንደሚቀርብ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ገለጹ። ጉዳቱን ያደረሰው ሃይል ማን እንደጠራውና በማን ትዕዛዝ ቦታው ላይ እንደተገኘ አላወቅንም ብለዋል። ሰሞኑን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ጨለንቆ ከተማ በሕወሃት የጦር አዛዦች የሚመራው ወታደራዊ ሃይል 18 ሰዎችን መግደሉንና በርካቶችን ማቁሰሉ ተዘግቧል። ይህንን ግድያ ተከትሎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ...

Read More »

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 3/2010) በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ ታወቀ። በወልዲያ፣ በጎንደር፣ በባህርዳርና በደብረታቦር ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የአጋዚ ሰራዊት በዩኒቨርስቲዎቹ ግቢ በመግባት ተማሪዎችን በመደብደብ ላይ መሆኑንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሻምቡ ግቢ ሁለት ተማሪዎች ተገድለዋል። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪው የአቋም መግለጫ በማውጣት ትምህርት ማቆሙን አስታውቋል። የህወሃት አገዛዝ ደጋፊ የሆኑ አክቲቪስቶች መንግስት ዩኒቨርስቲዎችን እንዲዘጋ ግፊት እያደረጉ መሆኑም ተሰምቷል። በአጠቃላይ ...

Read More »

ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 3/2010) በኢትዮጵያ የሕወሃት አገዛዝ ከስልጣን እንዲወርድ የሚካሄደው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ ተነገረ። በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች በመገደላቸው ተቃውሞው በተለያዩ ከተሞች እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል። የሕወሃት አጋዚ ወታደሮች ተቃውሞዎቹን ለመቆጣጠር እንደተሳናቸውም ምንጮቻችን ገልጸዋል። በቋንቋና ብሔር ላይ የተመሰረተው የሕወሃት ፌደራሊዝም ውጤቱ ግጭትና ትርምስ መሆኑን እያመላከተ ይገኛል። ግጭቶችና ጥቃቶች አንዴ በስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ሌላ ጊዜ ደግሞ በዩኒቨርስቲዎች የሚከሰቱት ብሔርን ከብሔር በመለየትና ቋንቋን ...

Read More »

በስደተኞች ጉዳይ የአውሮፓ መንግስታት ተባባሪዎች ናቸው በሚል ተከሰሱ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 3/2010) አምንስቲ ኢንተርናሽናል በሊቢያ በአፍሪካ ስደተኞች ላይ እየተካሄደ ላለው ሰቆቃ የአውሮፓ መንግስታት ተባባሪዎች ናቸው ሲል ከሰሰ። የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት የአውሮፓ መንግስታት በስደተኞቹ ላይ ለሚፈጸመው ሰቆቃ በተግባር ተሳታፊ ናቸው ብሏል። አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንዳወጣው ሪፖርት ከሆነ የአውሮፓ መንግስታት ስደተኞቹ ባህር አቋርጠው እንዳይመጡባቸው እዛው ሊቢያ ውስጥ ታግተው እንዲቆዩ ለአዘዋዋሪዎች፣ለታጣቂዎችና ለሊቢያ ተቋማት ገንዘብ ይሰጣሉ። በዚህም ምክንያት ይላል የድርጅቱ መግለጫ ...

Read More »

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የቀድሞ አመራሮቹን እያሳተፈ ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 3/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው ቀውስ ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ስብሰባ የተቀመጠው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የቀድሞ አመራሮቹን ማሳተፉ ታወቀ። በቅርቡ በሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ላይ የተጀመረውና በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ላይም የቀጠለው የቀድሞ አመራሮችን የማሳተፍ ርምጃ በመተካካት ስም ከሂደቱ የወጡትን ይበልጥ ተዋናይ እያደረጋቸው መምጣቱም ተመልክቷል። በስብሰባው ማጠቃለያ የካቢኔ ብወዛ እንደሚኖርም ይጠበቃል። የሕወሃት ደጋፊዎች በበኩላቸው አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ እንዲለቁ በመጠየቅ ...

Read More »

በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አደባባይ በመውጣት ድምጻቸውን አሰሙ

(ኢሳት ዜና –ታህሳስ 3/2010) በሊቢያ በጥቁር አፍሪካውያን በተለይም በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የባሪያ ንግድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት ሲሉ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አደባባይ በመውጣት ድምጻቸውን አሰሙ። በግሎባል አሊያንስና በሌሎች ሲቪክ ድርጅቶች አስተባባሪነት በተካሄደው በዚህ ሰልፍ ለኢትዮጵያውያኑ ስደትም ሆነ እንግልት ዋናው ተጠያቂ ህዝብን በመከፋፈል የሚታወቀው የህወሃት አገዛዝ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በዋሽንግተን ዲሲ፣በጀርመን ፍራንክፈርት፣በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያና በሌሎች ከተሞች በተካሄደው በዚህ ...

Read More »

በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ። በግቢው ውስጥ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱም ተሰምቷል።–የቅስቀሳ ወረቀት በመበተን ላይ መሆኑም ታውቋል። በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ግጭት ተቀስቅሷል። በወልዲያ ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት በትንሹ 4ተማሪዎች ተገድለዋል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ የህወሃት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ በመጠየቅ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ...

Read More »

በጨለንቆ በትንሹ ስድስት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) በሀረርጌ ጨለንቆ ዛሬ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በትንሹ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮምያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢም በተነሳ ግጭት ከ7 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ14 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የኢሳት ምንጮች ከስፍራው መረጃ አድርሰውናል። ለተቃውሞ መነሻ የሆነው ደግሞ ላለፉት ተከታታይ ወራት ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ሲፈጽም የቆየው የሶማሌ ልዩ ሃይል በአንድ የኦሮሞ ተወላጅ ላይ ግድያ በመፈጸሙ ነው። የልዩ ሃይሉ ...

Read More »

ሳውዲ ሲኒማ ቤቶች እንዲከፈቱ ፈቀደች

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) ሳውዲ አረቢያ ከ35 አመታት እገዳ በኋላ ሲኒማ ቤቶች በሀገሪቱ እንዲከፈቱ ፈቀደች። የሀገሪቱ ባህልና ማስታወቂያ ሚኒስቴር ሲኒማ ለመክፈት የሚያስችል ፍቃድ ዛሬ መስጠት ጀምሯል። ባለፈው ሰኔ አልጋ ወራሽነቱን የተቆናጠጡት መሐመድ ቢን ሳልማን በሳውዲ የተለያዩ ለውጦችን ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆኑ አሁን ሲኒማ እንዲታይ መፈቀዱ የዚሁ የለውጥ እንቅስቃሴ አካል ተደርጎ ተወስዷል። ራዕይ 2030 በመባል የሚታወቀውና በግዛቲቱ የተለያዩ ለውጦችን ለማድረግ በመንግስት የተያዘው ...

Read More »

የዋጋ ግሽበቱ ወደ 18 ነጥብ 1 በመቶ አሻቀበ

(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 2/2010) የምግብ ነክ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ወደ 18 ነጥብ 1 በመቶ ማሻቀቡን የማዕከላዊ ስታቲትክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የተጠናቀቀው ህዳር ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13 ነጥብ 6 በመቶ እንደነበርም የኤጀንሲው መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በቃላት መግለጽ የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል። የማዕከላዊ ስታቲትክስ ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ ደግሞ አሁን ላይ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ባለፈው ከነበረው እንኳን በ2 መቶ ...

Read More »