(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 9/2010) በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ። ከ50 በላይ ሰዎችም ቆስለዋል። በአውቶብስ መናሃሪያ አካባቢ በተፈጸመው በዚሁ የቦምብ ጥቃት ከፍተኛ ደም የፈሰሳቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታል ባለመወሰዳቸው ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሳምንት በሞያሌ ዳግም ባገረሸው የሶማሌና የኦሮሞ ተወላጆች ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን የዛሬው የቦምብ ጥቃት ዳግም ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር እንደሚያያዝ የኢሳት ...
Read More »በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ሶስት ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል
በሞያሌ ከተማ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት ሶስት ሲገደሉ ከ60 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) በሞያሌ ከተማ ሰላማዊ ዜጎች በሚበዙበት በከተማዋ መናሃሪያ አካባቢ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት እስካሁን ሶስት ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በጥቃቱ ከመቶ በላይ ሰላማዊ ዜጎች በደረሰባቸው ጉዳት ቆስለው ወደ ከተማዋ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መሃከል ህጻናት፣ሴቶችና አዛውንቶች ...
Read More »በቡሌ ሆራ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ
በቡሌ ሆራ የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሁለት ቀናት በፊት በጉጂ እና ጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ቆስለው በከተማው በሚገኝ ሆስፒታል የተጠለሉ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ያበሳጫቸው የሆስፒታሉ ሰራተኞች፣ በቁስለኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ ከኢትዮጵያ ባህል የወጣና ሰብአዊ መብትንም የሚጥስ በመሆኑ ገለልተኛ አካላት አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ...
Read More »በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ለሰዓታት ተስተጓጉለው ውለዋል።
በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ለሰዓታት ተስተጓጉለው ውለዋል። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) የቢቢሲው የአዲስ አበባ ወኪል ኢማኑኤል ኢንጉዛ ከሥፍራው እንደዘገበው የአየር መንገዱ የአየር ትራፊክ ሠራተኞች ዛሬ ማለዳ ላይ አድማ በመምታታቸው የኬንያው ኬ ኪው ወደ ናይሮቢ የሚያደርገውን ጉዞ ጨምሮ የበርካታ አየር መንገዶች በረራ ለሰዓታት ተስተጓጉሏል። የአየር ትራፊክ ሠራተኞቹ መሣሪያዎቻቸውን በማውረድ ማደማቸውን ያወሳው የቢቢሲው ዘጋቢ፣ የአመጻቸው ምክንያት ...
Read More »የዳባት ወረዳ ነዋሪዎች ወልቃይትና ሴቲት ሁመራ እንደሚመለስላቸው ጠየቁ
የዳባት ወረዳ ነዋሪዎች ወልቃይትና ሴቲት ሁመራ እንደሚመለስላቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ዳባት ከአመታት በፊት የነበራትን ሰባት ወረዳዎች በማጣት በሰሜን የነበሩትን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ክልል እና ወደ ሰሜን ጎንደር ተከፋፍሎ በመሰጠቱ፤ ዛሬ ያላት የህዝብ ብዛት ተመናምኗል፡፡ ይህም ለልማት የሚመደብላትን ገንዘብ አነስተኛ እንዲሆን አድርጓል፡፡ እነዚህ ችግሮች ባለመነሳታቸው ከተማዋ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣ ባለችበት መቆየቷ በየጊዜው በወረዳዋ ለሚከሰተው ችግር ...
Read More »40 ሚሊዮን ብር የወጣበት የጣናን ደለል ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ በዝገት ሲበላ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተባለ
40 ሚሊዮን ብር የወጣበት የጣናን ደለል ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ በዝገት ሲበላ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተባለ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢሳት ትናንት ሰኞ አንድ የመንግስት ባለስልጣንን ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የጣና ደለልን ለመጥረግ የተገዛው ማሽን ያለ ስራ መቀመጡን ገልጾ ነበር። ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ባለስልጣኑ የሰጡት መረጃ የተዛባ ነው። ማሽኑ ...
Read More »ራይላ ኦዲንጋ ኬንያን ወክለው በዊኒ ማንዴላ የቀብር ስነ ስርአት ላይ ተገኙ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010) የኬንያው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ኬንያን ወክለው በዊኒ ማንዴላ የቀብር ስነ ስርአት ላይ መገኘታቸው ተሰማ። ራይላ ኦዲንጋ በቀብር ስነስርአቱ ላይ የተገኙት በሃገሪቱ መንግስት ተወክለው መሆኑንም ቢሮአቸው አስታውቋል። የራይላ ኦዲንጋ ወደ ስፍራው መጓዛ በሀገሪቱ የተፈጠረው ሰላምን የማውረድ ሒደት ውጤታማ መሆኑን ማሳያ ነው ተብሏል። በመጨባበጥ የተጀመረው የኡሁሩ ኬንያታና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ቅርርብ በርካቶችን አስገርሞ ነበር። አሁን ...
Read More »ግብጽ የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት ያወጧቸውን መግለጫዎች ውድቅ አደረገች
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010) ግብጽ በአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የተፈጠረውን አለመግባባት በተመለከተ የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት ያወጧቸውን መግለጫዎች ውድቅ አደረገች። ግብጽ የተቋረጠው ውይይት በካይሮ እንዲቀጥል ብትፈልግም ጥሪውን አሁን ለመቀበል ዝግጁ እንዳልሆነች የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጿል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ በካርቱም የተካሄደው የኢትዮጵያ፣የሱዳንና የግብጽ ውይይት የተቋረጠው በግብጽ ችግር ምክንያት አይደለም። እናም ኢትዮጵያና ሱዳን ...
Read More »አቶ ታዬ ደንደአ፣ስዩም ተሾመና ኢያሱ አንጋሱ ከወህኒ ወጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010)ለሁለተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደአ ዛሬ ከወህኒ ቤት ወጡ። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ኢያሱ አንጋሱም ከወህኒ መፈታታቸው ታውቋል። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በጽሑፍ እንዲሁም በውውይትና በቃለ ምልልስ በንቃት የሚሳተፈው መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንደአ እና የኦሮሚያ ...
Read More »የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ይደረጋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 8/2010)የኢትዮጵያ የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆነው እንዲሰሩ ይደረጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናገሩ። ለቅሬታ ምንጭ የሆኑ ሕጎችም ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ቃል ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይህንን የተናገሩት ትላንት በሚሊኒየም አዳራሽ በተጠራ ሕዝባዊ መድረክ ላይ መሆኑም ታውቋል። ከጅጅጋና አምቦ ፣ በቤተ መንግስት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከመቀሌ በኋላ በተካሄደው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አምስተኛው የሚሊኔም አዳራሽ መርሃግብር ...
Read More »