(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በአካባቢው አመጽ መቀስቀሱ ተነገረ። የሚዛን ቴፒ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት አመጽም ትምህርት ተቋርጧል። በሚዛን ቴፒ ማጅ እና ጎጄብ መንገዶች ከመዘጋጋታቸው በተጨማሪ የንግድ መደብሮችም ተዘጋግተዋል። የመከላከያ አባላትና የፌዲራል ፖሊስ አመጹን ለማርገብ በሕዝቡ ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸ ተነግሯል። የሚዛን ቴፒ የሕዝብ ተቃውሞ ከጎጀብ ወንዝ በበቃ እንዲሁም ማሻ ይደርሳል። የተቃውሟቸው መንስኤ ደግሞ በተደጋጋሚ ...
Read More »የህወሃት ጄኔራሎች የኢትዮ-ሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ ነው
የህወሃት ጄኔራሎች የኢትዮ-ሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎችን እያስፈራሩ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) አቶ አብዲ ኢሌ በኢትዮ-ሶማሊ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ለከት የለሽ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም፣ የፕሬዚዳንቱን ከስልጣን መነሳት ለመጠየቅ ከክልሉና ከውጭ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን፣ አቤቱታቸውን ለፌደራል ባለስልጣናት ለማቅረብ አዲስ አበባ መገኘታቸውን ተከትሎ የህወሃት ጄኔራሎችና ነባር የድርጅቱ አመራሮች ወደ አገር ሽማግሌዎች ቤት በመሄድ ዛቻና ማስፈራሪያ እያስተላለፉ መሆኑን ምንጮች ...
Read More »በረከት ስምዖን ህወሃትን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ
በረከት ስምዖን ህወሃትን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ነው ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ መመረጡን ያልተቀበሉት አቶ በረከት ስምዖን፣ ከህወሃት ጋር በመሆን የእነ ዶ/ር አብይንና ለማን ቡድን ለመምታት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። በኢሃዴግ ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት እየተመናመነ የመጣው አቶ በረከት፣ በድርጅት አባልነት ከተመዘገቡበት ብአዴን ይልቅ ከህወሃት ጋር ጥምረት በመፍጠር እርሳቸውና በህወሃት ዙሪያ የሚገኙ ጓደኞቻቸው የሚቆጣጠሩትን ...
Read More »ኢትዮጵያ በሆላንድ ኢምባሲ ልትከፍት ነው
ኢትዮጵያ በሆላንድ ኢምባሲ ልትከፍት ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሆላንድ ዘ ሄግ ከተማ ላይ ኢምባሲ ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናት። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ በምባሳደርነት ተሹመው እንደሚመጡ ታውቋል። አቶ አባይ ከህወሃት ሊ/መንበርነትና ከትግራይ ክልል ርዕሰ ብሄርነት ከተነሱ በሁዋላ በአምባሳደርነት እንደሚሾሙ የታወቀ ቢሆንም፣ የት አገር እንደተመደቡ አልታወቀም ነበር። የውጭ ጉዳይ ምንጮች ...
Read More »በሽንሌ ዞን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ አለመላኩን የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ
በሽንሌ ዞን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ አለመላኩን የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በኢትዮ-ሶማሊ ክልል በሽንሌ ዞን ፣ በሃርዋ ፣ ገሚ፣ አይሎሶና ሌሎችም ቦታዎች አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ የተጎዱ ዜጎች እስካሁን ድጋፍ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለችግር ተዳርገዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤቶች መፍረሳቸውን፣ አንድ ሺ የሚሆኑ የእርሻ ማሳዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአካባቢው ተወላጆች ...
Read More »በአርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ቅጣጥ ከተጣለባቸው የወልዋሎ ተጫዋቾእች መካከል የአምስቱ ቅጣት እንዲነሳ ተደረገ።
በአርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው ቅጣጥ ከተጣለባቸው የወልዋሎ ተጫዋቾእች መካከል የአምስቱ ቅጣት እንዲነሳ ተደረገ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ-ከመከላከያ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ የመሀል ዳኛ ኢያሱ ፈንቴ የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም የወልዋሎ ተጫዋቾችና የቡድን መሪው ዳኛውን መሀል አስገብተው የፈጸሙት ድብደባ ብዙዎችን ማሳዘኑና ማነጋገሩ ይታወሳል። ድርጊቱን ተከትሎ “ዳኞች ዋስትና ካልተሰጠን ዳግም አናጫውትም”፡በማለታቸው ፕሪሚየር ሊጉ ለተወሰነ ጊዜ ...
Read More »የዋልያ ቢራ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
የዋልያ ቢራ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) በሆላንዱ ታዋቂ የቢራ ፋብሪካ ሃይነከን የተገነባው ቂሊንጦ በሚገኘው የቢራ ፋብሪካ ውስጥ በመጫንና በማውረድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ500 የማያንሱ ሰራተኞች መብታችን አልተከበረልንም በሚል የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። አድማው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በፋብሪካው የተመረቱ የቢራ ምርቶች ሳይሰራጩ ቀርተዋል። ሰራተኞቹን በኮንትራት የሚያሰራቸው ኤዶምያስ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ ...
Read More »ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች
ኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅሟ በመዳከሙ የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ አቆመች (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት የተነሳ የተበደረችውን ብድር በወቅቱ ለመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ በአጭር የክፍያ ጊዜና በከፍተኛ የወለድ መጠን የሚሰጡ ብድሮችን መበደር ማቆሟን የገንዘብ ሚኒስትሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል። አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ታገኛለች ተብሎ ቢታቀድም እቅዱ ሊሳካ አለመቻሉን ...
Read More »የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የኮምቦልቻ ግቢ ተማሪዎች ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓም በሰልፍ በመውጣት የውሃ ችግራቸው እንዲቃለል ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ የሚጠጣ ውሃ እንኳን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አልቻሉም። ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መልስ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኝተው ተማሪዎችን ለማረጋጋት ...
Read More »የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡
የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የማስፈጸም ችግሩ በአንድ ሴክተር መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሴክተሮቻችን የሚታይ ችግር ነው የሚሉት የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን አብዛኛውን ነገር እያሰረ ያለው የማስፈጸሙ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከኢንቨስትመንት አኳያ ባለሃብት መማምጣት ላይ ችግር እንደሌለ ሚገልጹት ከፍተኛ አመራር ዋናው ችግር የመጡትን ባለሃብቶች በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ ...
Read More »