ኢትዮጵያ በሆላንድ ኢምባሲ ልትከፍት ነው

ኢትዮጵያ በሆላንድ ኢምባሲ ልትከፍት ነው
(ኢሳት ዜና ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ/ም) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሆላንድ ዘ ሄግ ከተማ ላይ ኢምባሲ ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናት። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ በምባሳደርነት ተሹመው እንደሚመጡ ታውቋል።
አቶ አባይ ከህወሃት ሊ/መንበርነትና ከትግራይ ክልል ርዕሰ ብሄርነት ከተነሱ በሁዋላ በአምባሳደርነት እንደሚሾሙ የታወቀ ቢሆንም፣ የት አገር እንደተመደቡ አልታወቀም ነበር። የውጭ ጉዳይ ምንጮች እንደሚሉት ግን አቶ አባይ ሆላንድ በሚከፈተው አዲስ ኢምባሲ አምባሳደር ሆነው ይሾማሉ።
በቤልጂየም ብራሰልስ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሆላንድን፣ ቤልጂየምንና ሉክዘበርግን ሲወክል መቆየቱ ይታወቃል።