በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀየረ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 14/2010) በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ በአካባቢው አመጽ መቀስቀሱ  ተነገረ።

የሚዛን ቴፒ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት አመጽም ትምህርት ተቋርጧል።

በሚዛን ቴፒ ማጅ እና ጎጄብ መንገዶች ከመዘጋጋታቸው በተጨማሪ የንግድ መደብሮችም ተዘጋግተዋል።

የመከላከያ አባላትና የፌዲራል ፖሊስ አመጹን ለማርገብ በሕዝቡ ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸ ተነግሯል።

የሚዛን ቴፒ የሕዝብ ተቃውሞ ከጎጀብ ወንዝ በበቃ እንዲሁም ማሻ ይደርሳል።

የተቃውሟቸው መንስኤ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ የጠየቋቸው የልማጥ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው እንደሆነም ይነገራል።

በየአካባቢዎቹ በግለሰቦች ስም የተያዘ የሕዝብ ሃብት ለወጣቶች እንዲከፋፈልና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር የጠየቁ የሚዛን ቴፒ ነዋሪዎች በፌደራልና በመከላከያ ሃይሎች ድብደባና እንግልት ደርሶባቸዋል።

ከአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ የአካባቢው ሕብረተሰብ ከሃገሪቱ ልማት ያልተጠቀመ ነው ሲሉ ይገልጻሉ።

በሚዛን ቴፒ የተጠራቀመው የሕዝብ ብሶት ታዲያ ወደ ተቃውሞ መቀየሩን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባነሱት አመጽ ትምህርት ተቋርጧል።

በዚሁ በሚዛን ቴፒ ማጅና ጎጀብ መንገዶችና የንግድ መደብሮች ተዘግተዋል።

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪን ለመድፈር ሙከራ በመደረጉ የግቢው ተማሪዎች ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ጉዳዩ ወደ ሕዝቡ ደርሶ ከተማው ተረብሾ መዋሉንም ለማወቅ ተችሏል።

የሕዝቡን ብሶት ተከትሎ የተነሳውን አመጽ ለማርገብ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት ሕዝቡን ከበው እየደበደቡ መሆናቸውም ተነግሯል።