የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በውሃ ችግር ምክንያት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የኮምቦልቻ ግቢ ተማሪዎች ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓም በሰልፍ በመውጣት የውሃ ችግራቸው እንዲቃለል ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ የሚጠጣ ውሃ እንኳን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አልቻሉም። ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መልስ የሚሰጣቸው አካል አላገኙም። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተገኝተው ተማሪዎችን ለማረጋጋት ቢሞክሩም፣ ተማሪዎቹ ግን ከዚህ በላይ ማታገስ እንደማይችሉ፣ ችግሩ በአስቸኳይ ካለተፈታ በተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ለፕሬዚዳንቱ ገልጸውላቸዋል።