የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ (ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) ወኪላችን እንደዘገበው የሁለተኛ፣ የሶስተኛ እና በከፊል የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ኢንጂነሪንግ ፋክሉቲ ግቢ ለቀው ወጥተዋል። ሰሞኑን የተፈጠረውን አለመግባባት ሁሪያ በትላንትናው ዕለት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ጋር የተደረገው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ተማሪዎች ግቢውን እንዲለቁ በማስታወቂያ አዘዋል፡፡ማስታወቂያውን ተከትሎ ተማሪዎች ግቢውን በመልቀቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ...
Read More »ከአቢሲኒያ ባንክ የተዘረፈው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ
(ኢሳት ዲሲ–ነሀሴ 6/2010) በአቢሲኒያ ባንክ ከ5ሚሊዮን ብር በላይ ተዘርፎ በኋላ ላይ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ ቴሌ መድሃኒያለም ቅርንጫፍ 5 ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ ብር ተዘርፎ በፖሊስ እና በአካባቢው ማህበረሰብ ትብብር ዘራፊዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል። የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደገለጹት ዘረፋው የተፈፀመው የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኛ ከነበሩት ...
Read More »የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ላከ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010)ኢሕአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበሉን በመቃወም የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ላከ። መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ኮሚቴው በላከው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው በበቂ ማስረጃ ባልተደገፈ መልኩ የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢህአዴግ በኩል የተወሰነውን ውሳኔ እንዲያጤኑት ጠይቋል። የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት በህወሃት በኩል እየተደረገ ያለውን ሴራ ...
Read More »ኦህዴድ ከ2ሺ የሚበልጡ አባላቱን አባረረ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ባካሄደው 8ኛ ጉባኤው ከ2ሺ የሚበልጡ አባላቱን አባረረ። ከ500 የሚበልጡ የድርጅቱ አባላትን ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ማድረጉ ተሰምቷል። ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደገለጹት ኦሕዴድ ምንጠራ ያካሄደባቸው እነዚህ ግለሰቦች ነዋሪዎችን በአስተዳደር የበደሉ የሌላ አካባቢ ተወላጆች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች ደሞ ከቀያቸው ያባረሩና ያቆሳቆሉ ናቸው። ትላንት ማክሰኞ የሶስት ቀናት ድርጅታዊ ጉባኤውን ያጠናቀቀው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦሕዴድ/ በክልሉና በአጎራባች ...
Read More »ከሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች አምስቱ ታፍነው ተወሰዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) ለአቤቱታ አዲስ አበባ ከሚገኙት የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች መካከል አምስቱ ታፍነው መወሰዳቸው ተገለጸ። ላለፉት ሁለት ወራት አዲስ አበባ ሆነው በሶማሌ ክልል ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አፈናና ግድያ እንዲቆም ለመጠየቅ እያደረጉ ያሉት ጥረት በህወሃት ደህንነቶችና የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ባሰማራቸው አፋኝ ሃይሎች ምክንያት ሊሳካ እንዳልቻለ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በህወሃት ደህንነቶች ወከባ እየተፈጸመባቸው ያሉት ...
Read More »በወልቂጤ በተነሳው ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ንብረትም መውደሙን ነዋሪዎች ገለጹ
በወልቂጤ በተነሳው ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ንብረትም መውደሙን ነዋሪዎች ገለጹ (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው እሁድ የእግር ኳስ ጨዋታን ሰበብ በማድረግ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ ዛሬ ግጭቱ ተባብሶ የሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት ማክሰኞ ደግሞ ካምፕ 99 በሚባለው አካባቢ ከህገወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘ የከተማው ሹሞች ቤቶችን ሂደው በሚያፈርሱበት ሰዓት የቀቤና ተወላጆች፣ ...
Read More »የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ ዛሬ ባደረገው አስቸካይ ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከስልጣናቸው ማንሳቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ሐረሪ ብሔራዊ ሊግ አመራሮች ለ 27 አመታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጭቆና እንዲቆም በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ ቁጥራቸው ከ 600 በላይ የሚሆኑ የብሔረሰብ አባላት ባደረጉት አስቸካይ ስብሰባ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ እንደማይወክላቸው በሙሉ ድምጽ ...
Read More »በሀዋሳ እና ወልቂጤ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 6/2010) በደቡብ ክልል ሀዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በሃዋሳ እና ወልቂጤ ከተሞች ግጭቶች ተከስተዉ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል። በሁለቱም ከተሞች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎም ሰዎች መገደላቸው እየተነገረ ነው። በሃዋሳ የሚከበረው የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጨንበላላ በአል ሲከበር በከተማዋ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ተገኝቶ ነበር። ይሕንኑ የዘመን መለወጫ በአልን ምክንያት በማድረግ የተሰበሰበው ሕዝብ ...
Read More »በይርጋጨፌ ትናንት በነበረው ግጭት ቤቶች ተቃጠሉ
በይርጋጨፌ ትናንት በነበረው ግጭት ቤቶች ተቃጠሉ (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) በጉጂና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ አንዳንድ የደኢህአዴን አመራሮች ያሰማሯቸው የአካባቢው ባለስልጣናት “እኛ ተረጋግተን ሳንኖር እናንተ በእኛ ቦታ መኖር አትችሉም” በሚል የአካባቢውን ወወጣቶች አደራጅተው በጉራጌ፣ በአማራና በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት የተለያዩ ሰዎች ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ዛሬ፣ ብዙዎቹ የንግድ ድርጅቶቻቸውን ...
Read More »በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከሆሊስቲክ ፈተና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩትን አድማ ተከትሎ ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከሆሊስቲክ ፈተና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩትን አድማ ተከትሎ ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጸሙ (ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በምህንድስና ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች የጀመሩት አድማ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ተማሪዎች ግቢ በመግባት ድብደባ ፈጽመዋል። አንዳንድ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ህክምና ጣቢያዎች ተወስደዋል።የፖሊስና መከላከያ ሃይሎች ተማሪዎችን ከግቢ ለማስወጣት በአጥር ዘለው ሲገቡ የአይን ...
Read More »