(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 26/2010) የደቡብ ሱዳን መንግስት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪርን የስልጣን ዘመን በ3 አመታት ለማራዘም እቅድ ማጣቱ ተሰማ። የሳልቫኪርን ስልጣን እስከ 2021 እንዲቆይ ያደርገዋል የተባለው ይህ እቅድ ከወዲሁ ከተቃዋሚዎች ዘንድ ህገ መንግስታዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል። አንደ ሀገር ራሷን ከቻለች ትንሽ እድሜን ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን በተቃራኒ አንጃዎች የተነሳ የርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች ቆይታለች። ይህንን የእርስ በርስ ግጭት ለማስቆምም በተደጋጋሚ የሚደረጉ ስምምነቶች ከዳር ...
Read More »በለውጡ ሂደት እጁን መሰብሰብ ያለበት ሃይል እጁን እንዲሰበስብ ይደረጋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ– ሰኔ 26/2010)በለውጡ ሂደት እጁን መሰብሰብ ያለበት ሃይል እጁን እንዲሰበስብ ይደረጋል ሲሉ በአውስትራሊያ የኢትዮያ አምባሰደር ገለጹ። የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም ኤስ ቢ ኤስ ለተሰኘ ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ እንደገለጹት፡ የትግራይ ህዝብ እየተናገረ ነው። ለውጥ ያስፈልጋል። ህወሀት ውስጥም ለውጥ መደረግ አለበት ብለዋል። ህወህት እየታየ ያለውን ለውጥ ተገንዝቦ በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ...
Read More »ባለስልጣናት የፋሺዝም ተግባር አሳይተዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ– ሰኔ 26/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ እንዲሁም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በባህርዳር የፋሺዝም ተግባር አሳይተዋል ሲሉ የቀድሞው የኢንሳ ዳይሬክተር ገለጹ። የሕወሃቱ ነባር ታጋይ እና የቀድሞው የኢንሳ ዳይሬክተር ሜ/ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ በዚህ አካሄድ ከማንም ጋር የመኖራችን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ብለዋል። ትናንት ከትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ብአዴን እና ኦህዴድ ...
Read More »በቤንሻንጉል 54 የክልሉ ባለስልጣናት ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 26/2010) በቤንሻንጉል ክልል ከተከሰተውና 14 ያህል ሰዎች ከተገደሉበት ግጭት ጋር በተያያዘ 54 የክልሉ ባለስልጣናት መታሰራቸው ታወቀ። የፖሊስ ኮሚሽነሩ ከሥልጣናቸው እና ከስራቸው ሲታገዱ አስራ አንድ ፖሊሶች ታስረዋል። የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት እንዳስታወቁት የክልሉ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊዎችም ከስልጣን ተባረዋል ። የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሁሴን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶች እንደተዘጉ ይገኛሉ ፣ሆኖም ...
Read More »በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 26/2010)በኢትዮጵያ እና በሱዳን አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ግጭት መፈጠሩ ተሰማ። የግጭቱ መንስኤ የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያን የእርሻ መሬት እንዳያርሱ በመከልከላቸዉ ነዉ ተብሏል ፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል፡፡ ከሱዳን ጦር ጋር አብረው ወጊያውን የቀሰቀሱት የሕወሐት ሰዎች መሆናቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። ለግጭቱ መንስኤ የሆነውን የእርሻ መሬት ለረጅም ዓመታት እየተጠቀሙበት የሚገኙት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ናቸዉ፡፡ ...
Read More »ሱዳኖች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመግባት ጥቃት ፈጸሙ
ሱዳኖች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመግባት ጥቃት ፈጸሙ (ኢሳት ዜና ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) በቋራ ወረዳ በነፍስ ገበያ አካባቢ ከሱዳን ወታደሮች ጋር እየተካሄደው ባለው ውጊያ እስካሁን 7 የሱዳን ወታደሮች ተገድለው 2 ሙሉ የጦር መሳሪያዎችን የታጠቁ መኪኖች ተማርከዋል። ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከሶስት ቀናት በፊት በተጀመረው ጦርነት የተወሰኑ አርሶአደሮች መጎዳታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሱዳን በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጥቃት ስትፈጽም ይህ ...
Read More »ህወሃት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጀ ነው
ህወሃት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጀ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት እየተወሰዳቸው ያሉትን የለውጥ እርምጃዎች የሚቃወሙ የተቃውሞ ሰልፎች ለመጪው እሁድ እየተዘጋጁ ነው። ሰልፉን እኛን አይመለከተንም እያሉ ያሉ የራያ ተወላጆች ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። የራያ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ይዘው ከተገኙ ወይም ዶ/ር አብይ አህመድን ምስል የያዘውን ቲሸርት ...
Read More »በኤረር አካባቢ በሃዊያ ሶማሊዎችና በኦሮሞዎች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ እየተካሄደ ነው
በኤረር አካባቢ በሃዊያ ሶማሊዎችና በኦሮሞዎች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ እየተካሄደ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሃረር ወደ ባቢሌ- ጂግጂጋ በሚወስደው መንገድ መሃል ኤረር በምትባል የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከአጼ ሃይለስላሴ ጀምረው የሰፈሩ የሃዊያ ሶማሌዎችን ከኦሮሞዎች ጋር ለማጋጨት በሚደረገው ሙከራ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው። ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ አልፎ አልፎ በሚካሄደው ግጭት የሰዎች ህይወት ሲጠፋ ቆይቷል። ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ ...
Read More »አልጄሪያ ከ13 ሺ በላይ ስደተኞችን በኒጀር በረሃ መጣሏ ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 25/2010) አልጄሪያ ባለፉት 14 ወራት ከ13 ሺ በላይ ስደተኞችን በኒጀር በረሃ ላይ እንዲጣሉ ማድረጓን አዲስ የወጣ አንድ ሪፖርት አመለከተ። የአሶሼትድ ፕሬስ ሪፖርተርን ዋቢ አድርጎ የወጣው ሪፖርት በአብዛኛው በበረሃው እንዲጣሉ የተደረጉት ስደተኞች አልጄሪያን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት ጥረት የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት ሜዲትራኒያንን አቋርጠው አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞች ላይ ጫና ማድረጉን ተከትሎ በአካባቢው እየደረሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ መባባሱን ነው ...
Read More »ዶክተር ካሳ ከበደ ኢትዮጵያ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 25/2010) በቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት ዶክተር ካሳ ከበደ በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያ ገቡ። የኢሕአዴግ መንግስት በ1997 በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን ግድያ በመቃወም ስራና ስልጣናቸውን ትተው ኤርትራ የገቡት ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሉ ጎንፋም በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ከረጅም አመታት ስደት በኋላ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ታውቋል። ቅዳሜ ማለዳ አዲስ አበባ የደረሱት ዶክተር ...
Read More »