በኤረር አካባቢ በሃዊያ ሶማሊዎችና በኦሮሞዎች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ እየተካሄደ ነው

በኤረር አካባቢ በሃዊያ ሶማሊዎችና በኦሮሞዎች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ እየተካሄደ ነው
(ኢሳት ዜና ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሃረር ወደ ባቢሌ- ጂግጂጋ በሚወስደው መንገድ መሃል ኤረር በምትባል የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከአጼ ሃይለስላሴ ጀምረው የሰፈሩ የሃዊያ ሶማሌዎችን ከኦሮሞዎች ጋር ለማጋጨት በሚደረገው ሙከራ የዜጎች ህይወት እየጠፋ ነው። ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ አልፎ አልፎ በሚካሄደው ግጭት የሰዎች ህይወት ሲጠፋ ቆይቷል። ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 23 ቀን 2010 ዓም በተካሄደው ግጭት 8 የኦሮሞ ተወላጆችና 2 የሃዊያ ተወላጆች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ግጭቱ ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር በሆኑ ማግስት የተጀመረ ሲሆን፣ በጊዜ ክትትል ካልተደረገበት ወደ አስከፊ ግጭት ሊያመራ ይችላል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።