መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ በሆነ የጸጥታ ቁጥጥር በተካሄደው ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸው መልስ እስከሚያገኝ ድረስ ተቃውሞዋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጠዋል። አንዳንድ የተመረጡ የኮሚቴው አባላት መንግስት ወደ አወልያ እንዳይሄዱ ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ስለሰጣቸው በግቢው አለመታየታቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ የኮሚቴው አባላት ያልሆኑት ሌሎች ሙስሊሞች ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሙስሊሙን መሪዎች በደህንነት መኪኖች ሲከታተሉዋቸው መሰንበቱን ተከትሎ የጸጥታ መደፍረስ ሊከሰት ይችላል ...
Read More »የመለስ መንግስት ዜጎችን ለማፈናቀል ማቀዱን የሚያሳይ አዲስ ሰነድ ይፋ ሆነ
መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የህዝቅተኛ የኦሞ ሸለቆ አካባቢ ነዋሪዎችን ከቦታቸው በማንሳት በቦታው ላይ የሸንኮራ ገዳ ተክል ለመትከል መታቀዱን በድብቅ የወጣው ሪፖርት ያመለክታል። ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል በደረሰው መረጃ የሙርሲ፣ የቦዲና የኩዌጎ ነዋሪዎችን በቦዲ ለማስፈር ዘግጅቶች እየተካሄዱ ነው። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተካሄ መሆኑን ተገልጧል። አንድ የሙርሲ ተወላጅ ” መንግስት መሬቴን ስለወሰደው ሞትን እየተጠባበኩ ነው። ” ብሎአል። ሌላ ...
Read More »የአለም ደቻሳ ጉዳይ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው
መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በሊባኖሳዊው ጎረምሳ ከተደበደበች በሁዋላ እራሱን ያጠፋቸው አለም ደቻሳ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው በአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ሰዎች እንደገለጡት ድርጊቱ ኢትዮጵያኖች ያሉበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳይ ነው። አለም ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት መደብደቡዋ ፣ ጉዳዩን አሳዛኝ ማድረጉን የገለጡት ነዋሪዎች፣ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት በውጭ በሚገኙ ኢንባሲዎቹ አማካኝነት ካላረጋጋጠ ኢምባሲ መክፈት ለምን እንዳስፈለገም ጠይቀዋል። ...
Read More »ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት መሰንዘሩዋን አስታወቀች
መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ መንግሥትና ተላላኪዎቹን የጥፋት ተልዕኮ ማዕከላትን ዛሬ ማለዳ ላይ አውድሟል ብሎአል። የሚኒስቴሩ የኢንዶክትሬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ማዕከል ኃላፊ ኮሎኔል ገብረ ኪዳን ገብረ ማርያም ከኢትዮጵያ ድንበር በቅርብ ርቀት ባሉት ራሚድ፣ገላሃቤና ጌምቤ በተባሉ ሥፍራዎች ተሰባስቦ የነበረውን ኃይል ሙሉ በሙሉ አውድሟል ብሎአል። ሠራዊቱ የኤርትራ መንግሥትና ተላላኪዎቹን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ለማድረስ ከሚያደርገው ...
Read More »በጋምቤላ የተፈጸመው በመንግስት ሀይሎች ሳይሆን አይቀርም ተባለ
መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ባለፈው ሰኞ በተፈጸመው ጥቃት ከ30 በላይ በብዛት የጋምቤላ ኮሌጅ ተማሪዎች የሆኑትን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተጠልፎ፣ 19 ሰዎች ከተገደሉና 8 ሰዎች ደግሞ ከቆሰሉ በሁዋላ ድርጊቱን የፈጸሙትን ሰዎች ለማጣራት የኢሳት የጋምቤላ ዘጋቢ ላይ ታች ሲል ቆይቷል። ዘጋቢያችን ባደረሰን መረጃ ለጥቃቱ ምናልባትም የክልሉ ባለስልጣናት ወይም የፌደራል መንግስቱ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም። ትናንት የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ...
Read More »አንድ ኢትዮጵያዊ በኡጋንዳ ታርዶ ተገኘ
መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በንግድ አማካሪነት ይሰረ የነበረው እድሜው ከ55 እስከ 60 የሚገመተው አቶ ወልዩ ሀሰን ጣሄር ባለፈው ቅዳሜ አንገቱ በገጀራ ተቆርጦ ትናንት ተገኝቷል። አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን፣ ከግድያው ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ አንዲት ሴት መያዙዋን የዩጋንዳ የኢትዮጵያውያን ኮሚቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘለቀ ጀበሮ ለኢሳት ተናግረዋል። የድርጅታቸው ሾፌርና ዘበኛው መጥፋታቸውንም አቶ ዘለቀ አክለው ተናግረዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the ...
Read More »በየመን የታገቱ ከ3 ሺ በላይ ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ተደፈሩ
መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በሃርደሀ የመን የታገቱት ከ3 ሺ በላይ ሴቶች በተደጋጋሚ ጊዜ እንደተደፈሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አስታወቀ ኢትዮጵያውያኑ ሀርዳህ ከተማ ውስጥ ሻርቂያ በምትባል መንደር ለረጅም ጊዜ ታግተው ቆይተዋል። በርካቶቹ የውስጥ ሱሪ ብቻ ለብሰው መገኘታቸውን ኮሚሽኑ ገልጧል። ድርጊቱን ያጋለጡት ሁለት ሰዎች በአጥር ዘልለው ለማምለጥ በመቻላቸው ነው። ሀርዳህ ውስጥ የወንጀልምርመራ ሰራተኛ የሆኑት አሊ አብራሂም ” ለ15 ...
Read More »በዳውሮ ዞን ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት ተከስቷል
መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን በሚገኙ አራት ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት መከሰቱን የዞኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዋካ እና በተርጫ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጡት በዞኑ ተፈጠረው የውሀ እጥረት ህዝቡ አንድ ጀሪካን ውሀ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። ለዞኑ የውሀ ማስገቢያ ተብሎ የተላከው ገንዘብ በሙስና መበላቱንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to ...
Read More »በጋምቤላ በርካታ ሰዎች ክልሉን እየለቀቁ ነው
በጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጉዳት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ክልሉን እየለቀቁ ነው ከትናንት በስቲያ በጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ፣ የመሀል አገር ሰዎች ወይም በተለምዶ ደገኞች እየተባሉ የሚጠሩ ነዋሪዎች ተመሳሳይ ጥቃት ይፈጸም ይሆናል በሚል ስጋት አካባቢውን በአለው የትራንስፖርት አማራጭ ሁሉ እየለቀቁ ነው። በርካታ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ክልሎች በመኪና መጓዛቸውን በአይኑ መመልከቱን ወኪላችን ገልጦአል። በትናንትናው እለት በርካታ የፌደራልና ...
Read More »መንግስት ቀለደብን ሲሉ መምህራን ተናገሩ
መንግስት የደሞዝ ጭማሪ አደረኩ ብሎ ቀለደብን ሲሉ መምህራን ተናገሩ የኢትዮጵያ መምህራን የኑሮ ውድነቱ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ በመሆኑ መንግስትን የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። በደምቢያ፣ በደባርቅ እና በሌሎችም የሰሜን ጎንደር ትምህርት ቤቶች መምህራን የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ለጥያቄያቸው መልስ እንዲሰጣቸው ግፊት አድርገዋል። የመምህራኑ የስራ ማቆም አድማ ዛቻ ያሰጋው መንግስት በትምህርት ሚኒስትሩ በአቶ ደመቀ በኩል ባለፈው ሳምንት ፤ መንግስት አጥጋሚ ምላሽ እንደሚሰጥ ...
Read More »