መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዕውቁ ፎቶግራፍ አንሽ አቶ ሽመልስ ደስታ፤ የሊባኖስ መንግስት 50 ዓመታት በፊት ያበረከተላቸውን የክብር ኒሻን መልሶ እንዲረከባቸው ጠየቁ። አቶ ሽመልስ ደስታ በዓፄ ሀይለሥላሴ ጊዜ ከሊባኖስ ያገኙትን የክብር ሽልማታቸውን ለመመለስ የወሰኑት፤ ሊባኖስ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ነው። አቶ ሽመልስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1966 ዓመተ- ምህረት ከቀዳማዊ ሀይለሥላሴ ጋር ወደ ቤሩት ...
Read More »ኖርዌይ 450 ህጻናትን ልታስወጣ ተዘጋጅታለች ተባለ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘ ፎሬነር እንደዘገበው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔውን በተመለከተ ለፓርላማ አባላት ንግግር አድርገዋል። እንደርሳቸው አባባል ውሳኔው ስደተኝነትን የሚገታ እርምጃ ነው። እርሳቸው ይህን ቢሉም የአገሪቱ ፖለቲከኞችና ጸሀፊዎች ውሳኔውን እያወገዙ ነው። ፖለቲከኞች ውሳኔው ህጻናትን እንዳይጨምር እየጠየቁ ነው። ለመለስ መንግስት የሚሰጠውን እርዳታ የጨመረው የጠ/ሚኒሰትር ጂንስ ስቶልተርበርግ መንግስት ፣ በአለማቀፍ ደረጃ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለሚታወቅ መንግስት እርዳታ መጨመሩ ...
Read More »ሰበር ዜና :- የጋምቤላ መንግስት የምክር ቤት አባላት ለሁለት ተከፈሉ
መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላ መንግስት የምክር ቤት አባላት ለሁለት ተከፈሉ ፤ አንደኛው ወገን ህገ መንግስቱንና የፌደራሉን መንግስት አንቀበልም እንደ ጁባ ራሳችንን እናስተዳድር የሚል አቋም ይዟል የክልሉ መንግስት ጸጥታ የማስጠበቁን ስራ ለመከላከያ አስረክቧል በቅርቡ በተገደሉት 19ኙ ሰዎች ላይ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት ተረጋግጧል ፕሬዚዳንቱ ካልወረደ ግድያው እንደሚቀጥል የምክር ቤቱ አባላት አስጠንቅቀዋል
Read More »በጋምቤላ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት ላይ ናቸው
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊ የጸጥታና የደህንነት አማካሪ የሆኑት አለቃ ጸጋየ በርሄ፣ የልዩ ሀይል ዋና አዛዥ እና የጽረ ሽብር ግብረሀይል ከክልሉ ፕሬዚዳንት ከአቶ ኦሞድ ኦቦንግ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው። የመለስ መንግስት ባለስልጣኖች ወደ አካባቢው የተጓዙት በጋምቤላ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ ነው። በክልሉ ሰሞኑን 19 ሰዎች ከተገደሉና 8 ሰዎች ከቆሰሉ በሁዋላ ከፍተኛ የሆነ የፍርሀት ድባብ ነግሷል። በክልሉ ...
Read More »ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት ከመሰንዘር ይልቅ የውስጥ ችግሩን ብትፈታ ይሻላታል ተባለ
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጥቃት ከመሰንዘር ይልቅ የውስጥ ችግሩን ብትፈታ ይሻላታል ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የወሰደችው ወታደራዊ ጥቃት በአገር ውስጥ የሚታየውን ችግር ለመሸፋፈን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ የግል አስተያየታቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ዶ/ር ነጋሶ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ መደንገጣቸውን ተናግረው ፣ ኤርትራ ትረዳቸዋለች የሚባሉትን ...
Read More »በሙስሊም መካከል ልዩነት ለመፍጠር መንግስት እየሰራ ነው ተባለ
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሙስሊሞች ትናንት በአወሊያ መስኪድ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ተሰብስበው የኮሚቴውን ሳምንታዊ ሪፖርት አድምጠዋል፡፡ በቀጣይ ከአሕባሽ፣ ከመጅሊስና ከኢህአዴግ መንግሥት ሕገወጥ ተግባር ስለሚያደርጉትም ሠላማዋ ትግልም ተወያይተዋል፡፡ ሪፖርተራችን ያነጋገራቸው አንድ የኮሚቴው አባል ከለፈው ሣምንት ጀምሮ የመንግሥት የደህንነት ሰዎች በድብቅ ከሚያደርጉብን ክትትል እና አሰርጎ ማስገባት ...
Read More »በየወሩ 45 ሺህ ሴቶች ወደ ሳዓዲ ዐረቢያ ሊላኩ ነው
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በየወሩ 45 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳዓዲ ዐረቢያ ለመላክ መዘጋጀቷን ሳዓዲ ጋዜጣ ዘገበ። ጋዜጣው በሳዑዲት ዐረብ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንጮቹን ጠቅሶ ከጂዳ እንደዘገበው፤ 45 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በየወሩ ወደ ሳዑዲ የሚመጡት በቤት ሠራተኝነት ለማገልገል ነው። የሳዑዲ መንግስት ኬንያን ጨምሮ ከአራት አገሮች ለቤት ሠራተኝነት ወደዚያው የሚያቀኑ ሴቶችን በህግ እንዳይገቡ ካገደ በሁዋላ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ተፈላጊነታቸው በከፍተኛ ...
Read More »ሴቶች ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬታማ አይሆንም ተባለ
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። አቶ ኦባንግ ይህን የተናገሩት፤ ሰሞኑን ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 3 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሴቶች ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ነው። “የሴቶችን መብት በማስከበር ለሥልጣን ማጎናጸፍ” በሚል ርዕስ ...
Read More »የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመድረኩ አባላት እና የመድረኩ አስተዳዳሪዎች የድጋፍ ዝግጅት ያደረጉት ብቸኛው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ህብረተሰቡን ለማገልገል የሚያደርገውን ጥረት በማድነቅ ነው። በኢትዮጵያ የውይይት መድረክ ( ወይም ፓልቶክ) ከፍተኛ ተደማጭነትና ታዳሚ ያለው ኢካዲኤፍ ለኢሳት በተደጋጋሚ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል። መድረኩ በተከታታይ ዝግጅቶች ተመሳሳይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱንም ከአስተዳዳሪዎች ለመረዳት ተችሎአል። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መወያያ መድረክ ከዚህ በፊት በተለያዩ ...
Read More »ኤርትራ፤ ኢትዮጵያ ችግሯን በጦርነት እየሸፈነች ነው አለች
መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊ ት ወደ ኤርትራ ድንበር በመግባት በኤርትራ ወታደራዊ ተቋማትና ማሰልጠኛዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ማስታወቁን ተከትሎ ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት የጸብ አጫሪነት እርምጃ የድንበር ኮሚሽኑ የሰጠው ውሳኔ 10ኛ አመት እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ የአለማቀፍን ትኩረት ለማስቀየር ታልሞ የተደረገ መሆኑን ኤርትራ ገልጣለች። የድንበር ኮሚሽኑ ባድመ ለኤርትራ ይገባል በማለት ከ10 አመታት በፊት ቢወስንም ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለማስረከብ ...
Read More »