ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ጊዮርጊስ አደባባይ እራሱን በቤንዚን ያቃጠለው ጎልማሳ ሁኔታና ምክንያት ይጣራ ሲሉ የጠየቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች በፖሊስ ተበትነዋል፡፡ የተወሰኑ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችም ተጎጂው በትላንትናው እለት ለህክምና ተኝቶበታል በተባለው የካቲት 12 ሆስፒታል ተሰብስበው ለመግባት ያደረጉት ሙከራም በፖሊስ ተበትኗል ። ዘጋቢያችን በዛሬው እለት ለማጣራት እንደሞከረው እራሱን ያቃጠለው ...
Read More »የዓለም አቀፉ የፕሬስ ቀን በውዝግብ ታጅቦ ከነገ ጀምሮ ይከበራል
ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዓለም አቀፉ የፕሬስ ቀን ከነገ ሚያዝያ 18-21/2004 ድረስ በአዋሳ ከተማ ለጋዜጠኞች በሚሰጥ ወርክሾፕ ይከበራል፡፡ በዓሉን ዩኔስኮ ስፖንሰር ያደረገው ሲሆን አዘጋጆቹም በዋንኛነት የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት የአቶ አማረ አረጋዊ ድርጅት የሆነው ሆርን ኦፍ አፍሪካ የፕሬስ ኢንሰቲትዩት እና የኢህአዴግ ተለጣፊ መሆኑ የሚነገርለት የኢትዮጽያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት ናቸው፡፡ በኢትዮጽያ ቴሌቪዥን ባልደረባ አቶ መሰረት አታላይ የሚመራው ...
Read More »በስዊዘርላንድ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ
ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው እለት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ በስዊዘርላንድ እና ኣካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱሰልፉ የተዘጋጀው ኢህአዴግ :- · ዋልድባ ገዳምን ጨምሮ በሁሉም የእምነት ተቋማት ላይ እያካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ፣ · የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም ፣ · የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ...
Read More »“አገራችንን እናድን” ሲል ግንቦት 7 ጥሪ አቀረበ
ሚያዚያ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“አገራችንን ለማዳን የቀረን ጊዜ ትንሽ፤ በጣም ትንሽ ነው። ስለዚህም በዚህ ወቅት ልቦቻችንና ክንዶቻችንን አስተባብረን በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ እናንሳ” ሲል ግንቦት 7 ጥሪ አቀረበ “አገራችንን ለማዳን እንፍጠን! ጊዜ የለንም” በሚል ርዕስ የንቅናቄው ልሳን ባሰፈረው ርዕሰ-አንቀጽ፤በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፋርዳ እና ሌሎች የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በአስር ሺዎች ...
Read More »በአዲስ አበባ አንድ ወጣት እራሱን ማቃጠሉ ተሰማ
ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ጎልማሳ ኢትዮጵያዊ ዛሬ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ በመሐል አዲስ አበባ ጊዮርጊስ ዳግማዊ ምኒልክ ሃውልት ፊት- ለፊት በሚገኘው የአውቶብስ መቆሚያ ጎዳና ፤ አዲስ ምሩቅ ተማሪዎች የሥራ ማስታወቂያ የሚመለከቱበት ቦታ ላይ ራሱን በላስቲክ የውሃ መያዣ በያዘው ቤንዚን አቃጠለ፡፡ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች በውሃ እና ለፍራፍሬ ንግድ ከለላ የተደረገ ህንፃ ሲሰራ እንደ ከለላ የሚጠቀሙበት ሸራ ...
Read More »የግልገል ጊቤ አደጋ የሙስና ውጤት መሆኑን ጥናቶች አመለከቱ
ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግልገል ጊቤ አንድ በደለል የመሞላት ዜና ይፋ ከመደረጉ በፊት፣ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ደርጅቶች የተጠኑ ጥናቶች ማመላከታቸውን መረጃዎች አሳይተዋል። በግድቡ ዙሪያ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግድቡ ስራ ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ መብራት ሀይል በደለል ዙሪያ ያካሄደው ጥናት ግድቡ ለመጪዎቹ 50 አመታት አገልግሎት እንደሚሰጥ ይሁን እንጅ የአካባቢ እንክብካቤ ከተደረገ ለ70 አመታትም አገልግሎት ...
Read More »ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመሐል ዳኛ እንዳሻው አዳነ፣ ቀኝ ዳኛ ሙሉጌታ ኪዳኔ እና በቅርቡ በዳኛ አራጋው በሪሁን የተተኩት የግራ ዳኛ ሁሴን ይመር ባስቻሉት ችሎት ላይ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የቆሙበትን ችሎት ለመታዘብ የመጡ በርካታ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ጋዜጠኞች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች እና የፍትህ ጋዜጣ አንባቢያን የተገኙ ሲሆን የችሎቱ አዳራሽ በርካታ ሰው ከሚያስተናግደው 15 ...
Read More »በሶማሊያ በቦምብ ፍንዳታ 2 የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ
ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሶማሊያ በቦምብ ፍንዳታ 2 የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ፤በአፀፋዉ ሰላማዊ ዜጎችን ገደሉ በሶማሊያ በለደ-ወይኒ ከተማ በመንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ሁለት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሲገደሉ በሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በስፍራዉ የነበሩ የዓይን ምስክሮች መግለፃቸዉን ሬዲዮ ጋራዌ የመረጃ ምንጭ አስታዉቋል። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 በአካባቢዉ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸዉና ከሟቾቹ መካከል ...
Read More »ኤርትራ የፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ዜና ረፍት አስተባበለች
ሚያዚያ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኤርትራው መሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አርፈዋል የሚለውን ወሬ የሚያስወራው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት መሆኑን አገሪቱ መንግስት አስታውቋል ፕሬዚዳንቱ አሁንም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ በምስል የተደገፈ መረጃ በኤርትራ ቴሌቪዝን ተሰራጭቷል። የአሜሪካ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም። የዝምባቡዌ መሪ የሆኑት ሮበርት ሙጋቤ እንዳረፉ ተደርጎ ሲወራ የነበረው ወሬ የሲአይ ኤ ፈጠራ ነው በማለት ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ እስከ አሁን ፈቃድ አላገኘም
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወጣቶችና በምሁራን የተገነባው አዲሱ ሰማያዊ ፓርቲ እስከ ዛሬ ፈቃድ ሊያገኝ አልቻለም። ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የፓርቲው መስራቾች በቦርዱ የታዘዙትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሙዋሉም፣ የቦርዱ አባላት ግን ፈቃዱን ሊሰጡዋቸው አልቻሉም። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድርጅቱ ሰራተኛ ለኢሳት እንዳሉት፣ ፓርቲው በመላ አገሪቱ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፊርማዎችን አሰባስቦ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ቢረጋገጥም፣ የቦርድ አባላት ግን ...
Read More »