አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበርና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ፤ ትናነት ወደሶማሊያ ማቅናታቸው ታወቀ። አቶ ሀይለማሪያም በኢህአዴግ ሊ/መንበርንት ከተመረጡ የመጀመሪያቸው በሆነው የውጭ አገር ጉብኝታቸው ወደሞቃዲሾ ያመሩት፤ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በዓለ-ሲመት ላይ ለመገኘት መሆኑ ታውቋል። የሶማሊያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፤ ባለፈው ጳሁሜ 5 ቀን ሀሰን ሼክ መሀመድን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ የሚታወቅ ሲሆን፤ በአዲሱ ፕሬዚዳንት ቃለመሀላ ስነስርት ላይ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ፤ ሌሎች የጎረቤት አገሮች ...
Read More »እስክንድር ነጋ የታሰረበት ፩ኛ አመት ታሰቦ ዋለ
(Sept. 17) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች የህሊና እስረኞች የታሰሩበትን አንደኛ አመት የሚያስብ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 4 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ። በዚህ የዋሽንግተን ዲሲ አምነስቲ አለማቀፍ ቅርንጫፍ ደጋፊዎችና ፍሪ እስክንድር ነጋ ባዘጋጁት ዝግጅት ላይ፤ የእስክንድር ነጋን ቤተሰቦች ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት አካሂደዋል። የዝግጅቱ አስተባባሪ፤ ወ/ት አዜብ የዝግጅቱን ዓላማ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩ አያሌ የህሊና እስረኞችን ...
Read More »በሶማሊ ክልል በሚሊሺያዎች እና በህዝቡ መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ሰዎችና ቁጥራቸው ያልታወቁ ፖሊሶች ተገደሉ
መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ መንግስት እየተደገፈ የተለያዩ የስብአዊ መብቶችን በመጣስ የሚታወቀው የሶማሊያ ሚሊሺያ ታጣቂ ሀይል ሰሞኑን ከሀሺ ወረዳ ህዝብ ጋር በፈጠረው ግጭት 11 ሰዎችን ሲገድል፣ ከሚሊሺያዎች ወገን ደግሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ይሁን እንጅ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ታጣቂዎች ተገድለዋል። በኦጋዴን አካባቢ ብቻ ሳይሆን ወደ አፋር አካባቢዎች በመንቀሰቃስ በመንቀሳቀስ የተለያዩ ግጭ ቶችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚፈጽመው ይህ ...
Read More »ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ አዲስ ተሿሚዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በስልጣናቸው ይቀጥላሉ ሢሉ አቶ በረከት ስምዖን ተናገሩ
መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ይህን ያሉት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ቅዳሜ ዕለት ሊቀ-መንበሩን እና ምክትል ሊቀ-መንበሩን መምረጡን ተከትሎ ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሀላፊው ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በሂልተን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ቀደም ሲል የህወሀቱን አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የሚመረጠው ሰው ሹመቱ የሚቆየው እስከ ቀጣዩ ምርጫ እንደሆነ እና ...
Read More »የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተለያዩ ወረቀቶችን በአዲስ አበባ መበተኑን አስታወቀ
መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሁፎችን እና መግለጫዎችን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መበተኑ ታውቋል። ድርጅቱ ” የአንባገነኑ ስርአት በየቤተ እምነቱ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የአማኞቹን ሰላም እየነሳ እንደሚገኝ፣ ዘረኛው ስርአት ሀገሪቷን በዘር ከፋፍሎ አንዱን ብሄር ከሌላኛው ጋር በማጋጨት የህዝቡን የመኖር ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ ማድረሱን ፣ በአገዛዙ ቅጥረኞች የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ክልል ማባረሩን፣የኦሮሞን፣የአፋርን፣ የጋንቤላን፣ የሱማሌን ...
Read More »የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ሊያፈርስ የሄደውን የፖሊስ ሀይል ተባብረው በመመከት ወደ መጣበት መለሱት
መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ፤”መብታችንን አናስነካም!”ባሉ ነዋሪዎች ድል አድራጊነት ተጠናቋል። የአስተዳደሩ ግብረ ኃይል ባለፈው ሐሙስ በዶዘር በመታገዝ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ፤ በአካባቢው ነዋሪዎች ብርቱ ተቃውሞ ተቋርጧል፡፡ እንደ ሪፖርተር ዘገበ፤ በወቅቱ በነዋሪዎቹና በፖሊስ መካከል የጥይት ተኩስና የድንጋይ ውርወራ ተካሂዶ ነበር፡፡ ባንዲራ በማውለብለብ ባካሄዱት ተቃውሞ መኖሪያ ቤታቸውን ከመፍረስ የታገዱት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መንግሥት እንዲያነጋግራቸው ...
Read More »አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ከግድያ አመለጡ
መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሦስት አጥፍቶ ጠፊዎች ባለፈው ረቡዕ በሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሁሴን ሼክ መሀመድ ለጥቂት ተረፉ። ጥቃቱ የተፈፀመው አዲሱ ፕሬዚዳንት ከኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዑካን ጋር ስብሰባ እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ነው። በጥቃቱ ሦስቱን አጥፍቶ ጠፊዎች እና አንድ የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስጠባቂ ወታደርን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ዓለማቀፍ መገናኛ ...
Read More »አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን የያዘውና180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ም/ቤት ጉባዔ በሞት በተለዩት የግንባሩ ለቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ የብአዴኑን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል አድርጎ መምረጡን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ ጉባዔው በዛሬው ውሎው በገጉት ሲጠበቅ የነበረውን የግንባሩን ሊመንበር ምርጫ ያከናወነ ሲሆን አዲሱ ተመራጭ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »የፋና ራዲዮ ዘገባ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን አስቆጣ
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ኢንዶውመንት ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የሚታወቀውና ራሱን “የግል ራዲዮ ጣቢያ” በማለት የሚጠራው ራዲዮ ፋና “ኢትዮፒካሊንክ” በሚል ርእስ በኤፍ ኤም የሚያሰራጨው ፕሮግራም ከአቶ መለስ ዜናዊ፤ ዜና ዕረፍት ዘገባ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ቁጣ ታገደ፡፡ አቶ መለስ፤ ዜና ዕረፍታቸው በይፋ በመንግስት ከተነገረ በኃላ እስከቀብር ዕለት ድረስ የጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሞች ታጥፈው የነበረ ቢሆንም የኢትዮፒካሊንክ አዘጋጆች ቅዳሜ ነሐሴ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች በአስከፊ የስቃይ ሁኔታ እንደሚገኙ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች አጋለጡ። ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ወደ ኦጋዴ ክልል በመግባት በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመቅረጽ ሲሞክሩ በታጣቂዎች ተይዘው ላለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ከታሰሩ በሁዋላ ሰሞኑን የተለቀቁት ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ እስር ቤት በእስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ...
Read More »