Amsterdam

የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ

የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበል ማስታወቁን ተከትሎ ውሳኔው የኢሮብን ህዝብ ከሁለት የሚከፍል ነው በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዛሬ በርካታ የኢሮብ ወረዳ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ውሳኔውን እንደማይቀበለው ገልጿል። በተቃውሞው ዙሪያ የኦሮብ ተወላጅ የሆነ ግለሰብ ስቱዲዮ ጋብዘናል። የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ...

Read More »

በመከላከያ እና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ለውጦች እንደሚደረጉ ታወቀ

በመከላከያ እና ደህንነት መስሪያ ቤቶች ተጨማሪ ለውጦች እንደሚደረጉ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ነባር የመከላከያ አመራሮች እና የደህንነቱ ሹም ከስልጣን ተነስተዋል። ይህንን ተከትሎ በመከላከያ እና በደህንነቱ ተቋም የብሄር ተዋጽዖን ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን እንደሚነሱ ታውቋል። ለረጅም አመታት የደህንነት ሹም በመሆን የሰሩት የህወሃቱ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ በጄ/ል አደም ኢብራሂም እንዲተኩ ...

Read More »

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት ዛሬ ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ

በአማሮ ወረዳ ያለው ግጭት ዛሬ ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በአማሮ ወረዳ በጉጂ እና በኮሬ ማህበረሰብ መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ በመዋሉ የዜጎች ህይወት አልፏል። ከኮሬ በኩል በዳኖ ቡልቶ ቀበሌ የ49 ዓመቱ አርሶ አደር ሰንበተ ሳንኩራ እና የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ቶማስ ገመደ ከብቶቻቸዉን በማገድ ላይ እንደነበሩ ሲገደሉ፣ ከ30 በላይ የቤት እንስሶቻቸው ...

Read More »

ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ

ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ምትክ ጀነራል ሳዕረ መኮንን ጠቅላይ ኢታማዦር ሆነው ተሹመዋል። ኢሳት ከሁለት ሳምንት በፊት ምንጮቹን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና ፣ በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሰዓረ ...

Read More »

የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትሩ እንዲያናግሯቸው ጠየቁ

የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትሩ እንዲያናግሯቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የህወሃት ደህንነቶች አንድ የአብዲ ኢሌን ተቃዋሚ ለመያዝ ያደረጉት ሙከራም ሳይሳካላቸው ቀርቷል በአብዲ ኢሌ ፍጹማዊ አገዛዝ የተማመሩ ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት የተመለሱ እንዲሁም በክልሉ የሚኖሩ የአገር ሽማግሌዎች ከጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ በቤተመንግስት ዙሪያ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። የህወሃት ነባር አመራሮች ሽማግሌዎችን ...

Read More »

46 ኢትዮጵያውያን በኤደን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ

46 ኢትዮጵያውያን በኤደን ባህር ላይ ህይወታቸው አለፈ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት በምህጻረ ቃሉ -አይ ኦ ኤም እንዳስታወቀው ትናንት ረቡዕ 100 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው መርከብ በመስጠሟ፣ 37 ወንዶችና 9 ሴቶች ህይወታቸውን አጥተዋል። 16 ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። በጀልባዋ ላይ የተሳፈሩት ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ የገለጸው አይ ኦ ኤም፣ ከሶማሊያ የቦሳሶ ወደብ ተነስተው የመን ...

Read More »

ጄ/ል አለምሸት ደግፌና ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰላቸው

ጄ/ል አለምሸት ደግፌና ጄ/ል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰላቸው (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው ከ9 ዓመታት እስር በሁዋላ በቅርብ የተፈቱት ብ/ጄ/ል አሳምነው ጽጌና የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዲየር ጀኔራል አለምሸት ደግፌ፣ ወታደራዊ ማዕረጋቸው እንዲመለስላቸው መደረጉን የጠ/ሚኒስትሩ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትወተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ሁለቱም ጅኔራሎች ማእረጋቸውን እንደያዙ የጡረታ መብታቸው እንዲከበርላቸው መደረጉንም ባለስልጣኑ ገለጸዋል። ብርጋዴር ...

Read More »

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ሰጠች።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ሰጠች። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው መግለጫ ፣በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ስም- ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል አደም መሀመድ ሲ- 130 የጦር አውሮፕላንን በማበርከቱ ሂደት – አምባሳደር ሚካኤል ሬይኖር ተሳትፈዋል። ሲ-130 አውሮፕላን፣ ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ የተቀበለችውን ተልዕኮ በብቃት እንድትወጣ፣ የሰብዓዊ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው በማናቸውም አካባቢ አቅርቦቱን በፍጥነትና በሰዓቱ ለማድረስ ...

Read More »

በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡

በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በዞኑ ነዋሪ የሆኑ የቀድሞ ሚሊሻ አባላት የክልሉ መንግስት ለሰሩት ስራ ተገቢውን ድጋፍ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ የሚሊሻ አባላቱ እንደተናገሩት ከስድስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን በውትድርና ...

Read More »

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር፣ በደጋፊቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም ጠየቀ።

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር፣ በደጋፊቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም ጠየቀ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም)ማህበሩ የፋሲል ከነማ መለያ ልብስን በመልበሱ ምክንያት ወልቃይት ላይ የታሰረውን ፍቃዴ አሰፋን የአባልነት መታወቂያ አያይዞ “ለሚመለከተው ክፍል” በሚል ርዕስ በላከው ደብዳቤ፣ የክለቡ ደጋፊ የክለቡን መለያ በመልበሱ እና መታወቂያ በመያዙ ምክንያት የደረሰበትን እስርና እንግልት ነቅፏል። ፍቃዱ አሰፋ- የፋሲል ከነማ ማልያን በመልበሱ ወልቃይት ...

Read More »