በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡

በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡
(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በዞኑ ነዋሪ የሆኑ የቀድሞ ሚሊሻ አባላት የክልሉ መንግስት ለሰሩት ስራ ተገቢውን ድጋፍ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
የሚሊሻ አባላቱ እንደተናገሩት ከስድስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን በውትድርና ለመመልመል ማስታወቂያ ያወጣው አገዛዙ፤ ፈቃደኛ ወጣት በማጣቱ በሚሊሻነት ህዝብን ሲያገለግሉ የነበሩ ነዋሪዎችን በግዳጅ ወደ ማሰልጠኛ ካምፕ ወስዷል፡፡
በግዳጅ በነበሩበት ጊዜ ቆስለው አካል ጉዳተኛ ቢሆኑም፣ በሚኖሩበት አካባቢ ስራ በመስራት ራሳቸውን ለማገዝ እንዳይችሉ ፣”አካል ጉዳተኞችን ለማሰራት የሚያስችል መደብና መመሪያ የለንም” በማለት ለረዥም ዓመታት ያለስራ እንዲቆዩ መደረጋቸውን በምሬት ይገልጻሉ።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ አክለውም እንዳሉት፣ በተሰጡ ግዳጆች ላይ ከመደበኛው ወታደር በላይ መስዋዕትነት ቢከፍሉም፣ ያለምንም ድጋፍ በሜዳ ላይ መበተናቸው ኑሮን አክብዶባቸዋል፡፡