ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ

ሳሞራ ዩኑስ በጄኔራል ሳዕረ መኮንን ተተኩ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ምትክ ጀነራል ሳዕረ መኮንን ጠቅላይ ኢታማዦር ሆነው ተሹመዋል።
ኢሳት ከሁለት ሳምንት በፊት ምንጮቹን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና ፣ በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄ/ል ሳሞራ የኑስን በጄ/ል ሰዓረ መኮንንለማስተካት ህወሃት ግፊት እያደረገ እንደሆነ ዘግቦ ነበር።
በዚሁ የኢሳት ዘገባ፣ ህወኃት- ጄ/ል ሳዕረ ለቦታው ብቁ መሆናቸውን እና ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶችም ይህን እንዲቀበሉ ለማድረግ ግፊት እያደረገ እንደሚገኝ፣ግፊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝም “ከማእከላዊ ስልጣን እየተገፋሁ ነው” የሚል ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርብ እንደነበር ተገልጿል።
በትግራይ ብሄርተኝነት ዙሪያ ጽንፍ አቋም አላቸው የሚባሉት ጄ/ል ሰዓረ፣ ኢታማዦር ሹም መሆናቸው፣ በኦህዴድና ብአዴን ዘንድ ቅሬታና ተቃውሞ ያስከትላል ተብሎ ይጠበቃል።