.የኢሳት አማርኛ ዜና

የተመራጭ እጩዎች ምዝገባ በተጠናቀቀ በሳምንቱ ዛሬም ምዝገባ እየተካሄደ ነው

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቁን አውጆ ነበር። ኢሳት ባለው የመረጃ መረብ ለማረጋጋጥ እንደቻለው በቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የተማራጮች ስም ዝርዝር አለመተላለፉን ምርጫ ቦርድ ለኢህአዴግ ከገለጸ በሁዋላ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ የኢህአዴግ አመራሮች ወደ ወረዳው በመሄድ አቶ ሀይሌ አየለ የተባሉትን የኦህዴድ ኢህአዴግ የፖለቲካ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ፖለቲካዊና ማኀበራዊ ይዘት ያላቸው መፅሔቶችና መፅሐፎች እንዳይሸጡ ታገደ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነጻነት እንደዘገበው  መጽሄቶችንና መፅሀፎችን አዙረው የሚሸጡ  ወጣቶችም ከየካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ  የያዙዋቸው መጽሀፎችና መጽሄቶች ተወርሶባቸዋል። በተለይ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 11 ልዩ  ስሙ አባጃሌ በሚባል አካባቢ ያሉ የደንብ  አስከባሪዎች እዚህ ጎንደር ውስጥ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን   መፅሔቶች፣ ጋዜጦችና መፅሐፎች  መሸጥ አትችሉም በሚል በተደጋጋሚ  ጊዜ ከአዙሪዎች እየወረሱ ቅጣት እያሉ   ያስከፍሏቸው ...

Read More »

በአዲስ አበባ ምርጫ ከ99 በመቶ በላይ በእጩነት የተመዘገቡት ኢህአዴግ ናቸው

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወኪል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች= በመዘዋወር ያጠናቀረው ዘገባ እንደሚያመለክተው በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የወረዳና የአካባቢ ምርጫ፣ ተወዳዳሪ ሆነው በእጩነት የቀረቡት 99 በመቶ የሚሆኑት የኢህአዴግ አባላት ናቸው። አብዛኞቹ ተመራጮች የመንግስት ሰራተኞችና በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ተመድበው የሚሰሩ ናቸው። በእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ እንደሚታየው ከ40 በመቶ በላይ ተመራጮች ከ3ኛ ክፍል እስከ 10ኛ ክፍል የሚሸፍን የትምህርት ...

Read More »

በሙኒክ የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብቶች ተማጓች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በተገኙበት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢ ዝግጅት ከተጠበቀው ሰው በላይ በመምጣቱ ቦታ መጥበቡን አዘጋጆች ለኢሳት ገልጸዋል። የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው አቶ አበበ መለሰ እንደተናገረው በጀርመን የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ታሪክ ይህን ያክል ህዝብ ሲሳተፍ ማየቱ የመጀመሪያው ነው። ነገ እሁድ ፌብሩዋሪ 17 ደግሞ አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት መቀመጫ ...

Read More »

በዳውሮ ዞን የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የእና አቶ ዱባል ገበየሁን እስር ተከትሎ የዩኒቨርስቲ መምህራን እና የመንግስት ሰራተኖች እየታሰሩ ነው። ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አቶ አባተ ኡካ፣ ከጅማ ዩኒቨርስቲ  አቶ አብረሀም ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። በክልሉ የሚታየው ውጥረት መንግስትን በእጅጉ እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሎአል። የአቶ ዱባለ ገበየሁ ዘመዶችና ወዳጆችም እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣  ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በአሸባሪነት ክስ እንደሚቀርብባቸው ...

Read More »

አዲስ አበባ ውስጥ መስማትና መናገር የማትችል ወጣት በፖሊስ ተደፈረች

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደብረ ብርሀን ብሎግ ስፖት በድምጽ በማስደገፍ ይፋ እንዳደረገው ዜና በአዲስ አበባ ጎዳና  ላይ መስማት የተሳናትና ዝግመት ያለባት ታዳጊ ወጣት ብቻዋን መንገድ ላይ ስትጓዝና መሄጃ ጥፍቷት ስትደናገር አንድ ግለሰብ ያገኛታል። ግለሰቡም፦ ይቺ ልጅ ትንሽ ከመሸ ጥቃት ይደርስባታል ብሎ በማሰብ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በመሆን  በ አቅራቢያው ወደሚገኝ  ፖሊስ ጣቢያ ይወስዳታል። በአደራ የተረከበው  ፖሊስ “ነገ ቤተሰቦቿ ...

Read More »

ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀው መንግስት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዛሬው ዕለት ከተካሄደው ጁምአ ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት በተያያዘ በአዲስአበባ ዛሬ ማለዳ ላይ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ ተቋርጦ እንደነበር ተሰማ፡፡ በዛሬው ዕለት ሙስሊሙ ህብረተሰብ በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራሙ እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርግ ይችላል በሚል ግምት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ ...

Read More »

የአማራ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስና ተከሰሰ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል የሚሰሩ የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች እና የኢህአዴግ አባላት ለኢሳት እንደገለጡት ከመሬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ በክልሉ የሚታየው ከፍተኛ ሙስና ሊገታ ያልቻለው የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሙስናው ዋና ተዋናይ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ሰራተኞቹ ከወራት በፊት ከፍተኛ የዜና ሽፋን ተሰጥቶት የነበረውን የሙስና ጉዳይ በማንሳት እንደገለጡት ፣ የክልሉ ባለስልጣናት ከባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ...

Read More »

የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ይግባኝ ተራዘመ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም 6 ኪሎ ለሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ በጠየቁት መሰረት ...

Read More »

በሳውዲ አረብያ የታሰሩ 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አሁንም እንደታሰሩ ነው

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት በሳውዲ አረብያ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ከዋሉት 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመፈታታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ኢትዮጵያውያኑ ሳምንታዊ የአምልኮ ጉባኤያቸውን ለማካሄድ በተሰባሰቡበት ወቅት ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት። ምንም እንኳ ፖሊስ ቃላቸውን ቢቀበልም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊመራው እንዳልቻለ ታውቋል። አንድ የእምነቱ ተከታይ እንደገለጠው፣ ኢትዮጵያውኑ ነገ  ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ  ሊሰጣቸው ይችላል ሲል ...

Read More »