የእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ይግባኝ ተራዘመ

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም 6 ኪሎ ለሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ በጠየቁት መሰረት ለየካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ለውሳኔ ተቀጥሮ እንደነበር ይታወቃል።

ነገር ግን በዕለቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሐል ዳኛው ሳይገኙ ከመቅረታቸውም በላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ለመስጠት ጉዳዩ ሰፋ ያለ ጊዜ ስለሚፈልግ አይተን አልጨረስንም የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የይግባኙን የመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለ3ኛ ጊዜ ለመጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡