በሳውዲ አረብያ የታሰሩ 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አሁንም እንደታሰሩ ነው

የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት በሳውዲ አረብያ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ከዋሉት 43 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመፈታታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ኢትዮጵያውያኑ ሳምንታዊ የአምልኮ ጉባኤያቸውን ለማካሄድ በተሰባሰቡበት ወቅት ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት።

ምንም እንኳ ፖሊስ ቃላቸውን ቢቀበልም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊመራው እንዳልቻለ ታውቋል።

አንድ የእምነቱ ተከታይ እንደገለጠው፣ ኢትዮጵያውኑ ነገ  ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ  ሊሰጣቸው ይችላል ሲል ተናግሯል።

የሳውዲ መንግስት ሴቶችና ወንዶች በአንድ ላይ ሆነው እንዲያመልኩ ወይም በአገሪቱ የመንግስት ሀይማኖት ከሆነው እስልምና ውጭ ሌሎች ሀይማኖት እንዳይመለኩ በይፋም ባይሆን በተለያዩ መንገዶች ይከለክላል።