በዳውሮ ዞን የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የእና አቶ ዱባል ገበየሁን እስር ተከትሎ የዩኒቨርስቲ መምህራን እና የመንግስት ሰራተኖች እየታሰሩ ነው።

ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አቶ አባተ ኡካ፣ ከጅማ ዩኒቨርስቲ  አቶ አብረሀም ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል።

በክልሉ የሚታየው ውጥረት መንግስትን በእጅጉ እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሎአል። የአቶ ዱባለ ገበየሁ ዘመዶችና ወዳጆችም እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣  ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በአሸባሪነት ክስ እንደሚቀርብባቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ዳውሮ  መምህር የኔሰው ገብሬ ዲሞክራሲና ፍትህ በሌለበት አገር አልኖርም በማለት ራሱን በእሳት አቃጥሎ ያገደለባት  ቦታ ነው።