በሙኒክ የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እውቁ የሰብአዊ መብቶች ተማጓች አርቲስት ታማኝ በየነ እና ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በተገኙበት የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢ ዝግጅት ከተጠበቀው ሰው በላይ በመምጣቱ ቦታ መጥበቡን አዘጋጆች ለኢሳት ገልጸዋል።

የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው አቶ አበበ መለሰ እንደተናገረው በጀርመን የኢትዮጵያውያን ዝግጅት ታሪክ ይህን ያክል ህዝብ ሲሳተፍ ማየቱ የመጀመሪያው ነው።

ነገ እሁድ ፌብሩዋሪ 17 ደግሞ አርቲስት ታማኝ በየነ በኢሳት መቀመጫ አምስተርዳም ከተማ ተገኝቶ በሆላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያል። በዚህ ዝግጅት የሀይማኖት አባቶች እና  የሰብአዊ መብት ተማጓቾች ንግግር ያደርጋሉ።

የኢሳት የሆላንድ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረሀይል በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ  እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህ ቀደም በኖርዌይ፣ በስዊድንና በስዊዘርላንድ ደማቅ እና ውጤታማ የድጋፍ ማሳባሰብ ዝግጅት ተካሂዷል።

ተመሳሳይ ዝግጅቶች በለንደን፣ በብራሰልንስና በፍራንከፍርት እንደሚካሄዱ የአውሮፓ የኢሳት ግብረሀይል አስታውቋል።