.የኢሳት አማርኛ ዜና

ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን መዲናህ ከተባለው መጠለያቸው  ግንብ እየዘለሉ  ወደ ታይባን ዩኒቨርስቲ ካምፓስ እንደገቡ የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ብርጋዴር ፋህድ ቢን አሚር አል ጋናም እንደገለጹት 15 ኢትዮጵያውያን ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ የገቡ ሲሆን የጸጥታ ሀይሎች ኢትዮጵያውያኑን በመያዝ ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ልከዋቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በሰዎች፣  በመኪኖች ወይም ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሱ የሳውዲ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡ ...

Read More »

በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን  አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው። ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል። ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም በመገንባት ላይ የተጠመደው ክልሉ ፤ ...

Read More »

የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በታችኛው ኦሞ የተፈጠረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚመረምር አስታወቀ

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ አካል ነው የተባለው ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት በሚል በታችኛው ኦሞ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን በማፈናቀል እየፈጸመችው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጥነት እንድታቆም ጠይቆ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግም ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚኖሩ ብሄረሰቦች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና እስራት መፍጠሩን የመለከተው ኮሚሽኑ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ...

Read More »

‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

ህዳር ፲፰(አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ ምድር የእናቶችና የህጻናት ለቅሶ ቀጥሎአል።

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ከሪያድ ወደ አዲስ አበባ ትሄዳላችሁ ተብለው በመኪኖች የተሳፈሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችና ህጻናት በድንገት ጉዞዓቸው መሰረዙን ተከትሎ፣ በርካታ እናቶችና ህጻናት ለከፍተኛ የውሀ ጥም በመዳረጋቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው። እናቶች እና ህጻናት ተስፋ በቆረጠ ስሜት ያለቅሳሉ፤ ማለቃችን ነው ድረሱልን ሲሉ ይማጸናሉ። ህጻናቱና እናቶች አስፋልት ላይ ተበትነው በውሀ ጥም ማለቃቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ኢሳት በቀጥታ ከስደተኞች ...

Read More »

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው። ኢሳት የሚኒስትሩን  ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል።  በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ...

Read More »

በጅጅጋ ለብሄረሰቦች በአል ሲባል ትምህርት ቤቶችና መስሪያ ቤቶች ተዘጉ

ህዳር ፲፯(አስራ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ/ም ለ8ኛ ጊዜ  የሚከበረውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  በዓል  ጋር በተያያዘ የመንግስት ሥራ እና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ በከተማዋ በየእለቱ ቤት ለቤትና በጎዳና ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተከናወነ ነው።  በጅጅጋ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ከ3ሺ500 በላይ እንግዶችን ታስተናግዳለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እንግዶቹ ከሚያርፉባቸው ቦታዎች አንዱ የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ለአንድ ወር ትምህርት እንደማይኖር በመግለጽ ተማሪዎቹን ማሰናበቱ ታውቋል፡፡ ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ ምድር በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እና አስገድዶ መድፈር እንደቀጠለ ነው

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን። እሁድ  2  ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው እንደምትገኝ እኝሁ የአይን ምስክር ይገልጻሉ ከዚህ ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፓርላማ  ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በተቃውሞው ላይ የተገኘችው የኢሳት የደቡብ አፍሪካ ተባባሪ ዘጋቢ ዝናሽ ሀብታሙ እንደገለጸችው በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ታሰትፈዋል። ተቃውሞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ንብረት ጌታሁንም ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ተገኝቶ ስሜቱን በከፍተኛ ሁኔታ ገልጿል ብለዋል በተመሳሳይ ዜናም የአፋር ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር  እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ  በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ    10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የመንግስት 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል ብሎአል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ...

Read More »