የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በታችኛው ኦሞ የተፈጠረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚመረምር አስታወቀ

ህዳር ፲፰(አስ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ አካል ነው የተባለው ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት በሚል በታችኛው ኦሞ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን በማፈናቀል እየፈጸመችው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጥነት እንድታቆም ጠይቆ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግም ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚኖሩ ብሄረሰቦች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና እስራት መፍጠሩን የመለከተው ኮሚሽኑ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ምእራባውያን ጉዳዩን አይተው እንዳላዩት ማለፉን አጋልጧል።

ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ስቴቨን ኮሪ  ኢትዮጵያና ተመሳሳይ ችግር የሚፈጥረው ቦትስዋና ዜጎቻቸውን ማፈናቀላቸውን ካላቆሙ የአለም ህዝብ ህገወጥ አገሮች ብሎ ይፈርጃቸዋል ብለዋል።