‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

ህዳር ፲፰(አስ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡

ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል፡፡

ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።