.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኩረጃ መስፋፋት የትምህርት ጥራትን እየጎዳ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሔራዊ ፈተናዎች በተለይ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናዎች ላይ ኩረጃ በአሳሳቢ ደረጃ እየተባባሰ መምጣቱን፣ ለትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አንድ ምክንያት እየሆነ መሆኑን የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ያካሄደው ጥናት ጠቁሟል፡፡ ሰሞኑን ይፋ ሆነው ይህው ጥናት በኩረጃው ሒደት በተቀነባበረ መልኩ ሁሉም አካላት ማለትም ፈተና አስተባባሪዎች፣ፈታኞች፣ የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች፣ርዕሰመምህራን፣ መምህራን፣ ወላጆች በቀጥታ ይሳተፋሉ፡፡ ...

Read More »

በናይጀሪያ መከላከያ ሰራዊቱ ከ600 በላይ ሰዎችን መግደሉን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብኢ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ እንደገለጸው የናይጀሪያ መከላከያ ሰራዊት፣ የእስልምና መንግስት ለማቋቋም የሚታገለውን ቦኮ ሃራም የተባለውን ተዋጊ ሃይል ለመውጋት በሚል ሰበብ በከፈተው ጥቃት ከ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በሚወስደው እርምጃ በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቅ እንደሚገባው የገለጸው አምነስቲ፣ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችም በተመሳሳይ ንጹሃን ላይ የሚወስዱት እርምጃ ...

Read More »

በጉጂ እና በቦረና ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት የማቾች ቁጥር መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ባለፉት 3 ቀናት ከቦረና እና ከጉጂ ጎሳዎች ከ20 ያላነሱ ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውንና መጠኑ በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙንም ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በተለይ ትናንት ብቻ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተነሳው ግጭት ከቦረና ከ12 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከጉጂ ደግሞ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ኬንያ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሁለት አመታት ሲካሄድ የቆየው፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ዛሬ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያኑ   አላህ ሰላምን እንዲያመጣ ሲማጸኑ አርፍደዋል። የሰላም ሰዎች መሆናቸውን ነጭ ወረቀቶችን በማውለብለብ ያሳዩ ሲሆን ተቃውሞውም ያለምንም የጸጥታ ችግር ተጠናቋል። መንግስት እንቅስቃሴውን በሃይል እንደተቆጣጠረው ሲያውጅ ቢከርምም ...

Read More »

በመርአዊ ከተማ ተጨማሪ አርሶደአሮች እየታሰሩ ነው

መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ በእናሸንፋለን ቀበሌ ከአበባ እርሻና ከውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የሚታሰሩ አርሶደሮች ቁጥር መጨመሩን አካባቢው ሰዎች ገልጸዋል። በወረዳው ዋና ከተማ በመርአዊ ከተማ አሁንም የሚታሰሩ አርሶደአሮች መኖራቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ታዳጊ ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው እንዲታሰሩ መደረጉን ገልጸዋል። የመኢአድ የመርአዊ ተወካይ አቶ ስማቸው ምንችል ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ...

Read More »

ወንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ የፀጉር አቆራረጥ ስታይላቸውን እንደ ሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እንዲያደርጉ ሰሜን ኮሪያ መመሪያ አወጣች።

መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮ ፍሪ ኤሺያን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው፣መመሪያው መጀመሪያ የተላለፈው በዋና ከተማዋ በፒዮንግያንግ  ከሁለት ሳምንት በፊት ነው። በአሁኑ ወቅት በ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሙሉ አዋጁ ተግባራዊ እየሆነ መምጣቱን የዜና አውታሩ ጠቁሟል። በወጣት ፋሽን ተከታዮች  “ስታይል” ጸጉራቸውን ከተቆረጡ የሰነበቱት  ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ ይባስ ብሎ ወንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም  እንደ እርሳቸው እንዲቆረጡ ...

Read More »

በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን የተፈጠረው ግጭት

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 16፣ 2006 ዓም ከጉጂ ዞን ዋና ከተማ ስያሜ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ግጭት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች እንደሞቱ የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ግጭቱ የጉጅ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ነገሌ ቦረና ፣ ነገሌ ብቻ ተብላ እንድትጠራ የመንግስት ባለስልጣናት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተከትሎ የቦረና ተወላጆች ተቃውሞ በማስነሳታቸው መነሳቱ ታውቋል። የቦረና ተወላጆች ታሪካዊቷ የነገሌ ቦረና ...

Read More »

የጫፌ ኦሮምያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጨፌ ኦሮምያ ትናንት የጀመረውን የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ሲያጠናቀቅ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትር የሆኑትን አቶ ሙክታር ከድርን በፕሬዚዳንትነት፣ እንዲሁም አቶ ለማ መገርሳን በአፈ ጉባኤነት መርጧል። ምንም አይነት ተወዳዳሪ እጩ ባልቀረበበት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ድምጽ ሳይሰማ ፕሬዚዳንቱም አፈ ጉባኤውም ተመርጠዋል። ሌሎች የምክር ቤት አባላት አፈ ጉባኤው የፕሬዚዳንቱን ስም ጠርተው እንዲያጸድቁ ...

Read More »

የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ቀጣይ የተቃውሞ መርሃግብር

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 2 አመታት ሲካሄድ የቆየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አርብ እንደሚጀመር ታውቋል። የተቃውሞ መሪ መፈክሩ “ሰላታችንን በመስኪዳችን” የሚል እንደሆነና መስኪዶችን በመንግስት ታማኞች ለማስያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም አላማ ያደረገ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት ዛሬ ተጀምሯል። ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት ...

Read More »

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ዳግም ቃጠሎ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በማተሚያ ቤቱ የወረቀት ክምችት መጋዘን ላይ መጋቢት 13 ቀን 2006 ዓ.ም ከሰዓት በሃላ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መጋዘኑን የጎዳ ሲሆን ትናንት ጠዋት ደግሞ በዚሁ መጋዘን ላይ ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞአል፡፡ የመጀመሪያው አደጋ በማተሚያ ቤቱ የወረቀት ክምችት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ተመሳሳይ አደጋ በተመሳሳይ ቦታ ላይ በማጋጠሙ ፣በማተሚያ ቤቱ የማሽን ...

Read More »