ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀረባባቸውን ክስ በፍርድ ቤት እየተከራከሩ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በፍርድ ሂደቱ ላይ ያቀረቡት መከራከሪያና ያሳዩት ጥንካሬ የመላውን ሙስሊም ማህበረሰብ ቀልብ በሳበበት በዚህ ወቅት፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለመሪዎቹ ያለውን ድጋፍ ለመግለጽና የመንግስት ህገወጥ እርምጃ ለመቃወም የፊታችን አርብ የተቃውሞ ድምጹን እንደሚያሰማ ታውቋል። የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በእስር ቤት ውስጥ እጅግ አሰቃቂ ሆነ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ዩክሬን መንግስት ለሩሲያ ደጋፊዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶስቱ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች የተነሳው አመጽ እንደቀጠ ሲሆን የዩክሬን መንግስት አመጹ ካልቆመ በ48 ሰአታት ውስጥ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል፡ ሉሃንስ፣ ዶኔትስክ እና ካርኪቭ በተባሉት የዩክሬን ግዛቶች የሚኖሩ አብዛኞቹ ሩሲያውያን ፣ ከሩሲያ ጋር መቀላቀልን ወይም ነጻ የሆነ ግዛት የመመስረት ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ ይህንንም ለማሳካት ቁልፍ የሚባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ይዘዋል። ሩሲያ በክርሚያ እንዳደረገችው ሁሉ ...
Read More »የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አወዛጋቢ አዋጅ ሥራ ላይ ዋለ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት መጨረሻ በአዲስ መልክ በአዋጅ የተቋቋመውና ዜጎች መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገደድደው ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት አዲሱን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በ1987 ዓ.ም የደህንነት የኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን በሚል ስያሜ ተቋቁሞ በስራ ላይ የነበረው ይህው ተቋም የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዲችል በሚል ባለፈው ዓመት አዲስ የማሻሻያ ረቂቅ ለፓርላማው ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ወ/ሮ አስቴር ማሞን ሾሙ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ዛሬ ፓርላማ በድንገት ተገኝተው የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩትን ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያቀረቡትን ሹመት ፓርላማው ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ የኦህዴድ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚደንት ከነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሞት በኃላ ኦህዴድ ባደረገው የሥልጣን ሽግሽግ አቶ ሙክታር ከድር ከምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ተነስተው ...
Read More »የምእራብ ጎጃም ነዋሪዎች በመብራት እጦት መማረራቸውን ገለጹ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በፍኖተ ሰላም እና አጎራባች ወረዳዎች ማለትም በቡሬ ፤ በጃቢ ጠናን ፤ ፈረስ ቤት ፤ ይልማና ዴንሳ፣ ፤ሜጫ ፣ አቸፈር እና ቋሪት የሚኖሩ ነዋሪዎች በፍኖተ ሰላም ከተማ በጃቢ አዳራሽ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ ከክልሉ መስተዳደር ጋር በተደረገ ውይይት በመብራት እጦት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን በምሬት ተናግረዋል። የመብራት ሃይል ሹሞች በሙስና ተዘፍቀዋል ያሉ ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንብረቶቻቸው ተዘረፉ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኖርዝ ዌስት ውስጥ ቡልም ኦፍ በምትባል ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተዘርፈው ተቃጥለዋል። የከተማው ነዋሪዎች ከመሰረታዊ ልማት ጋር በተያያዘ ያስነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ረብሻ መፈጠሩንና ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና ፓኪስታናውያን ኢላማ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያኑ አካባቢውን ለቀው ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል። በከተማዋ የሚታየው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉንም ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
Read More »አንድነት ፓርቲ በደሴ የተሰካ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል የተጀመረው ሁለተኛ ዙር የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴ እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓም በደሴ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው የዝግጅቱ አላማ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ችግሩን እንዲናገር፣ እንዲተነፍስ፣ የህዝቡን ችግሮች ለማወቅ እና ህዝቡ ...
Read More »የአረና ትግራይ አመራሮችና ደጋፊዎች በህወሃት ካድሬዎች ሲዋከቡ መሰንበታቸውን የድርጅቱ አመራሮች ገለጹ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓም ፓርቲው በምስራቃዊ ዞን አጽቢ ወንበርታ ወረዳ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በከፍተኛ የደህንነት አፈና ውስጥ ሆኖ መካሄዱን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚና የህዝብ ግንኑነት አባል የሆነው አቶ አብረሃ ደስታ ገልጿል። ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ቢያደርግላቸውም የህወሃት ካድሬዎች ምግብ እንዳያገኙ፣ አንዳንድ አመራሮች የያዙትን አልጋ እንዲለቁ ማድረጋቸውን በስብሰባው ዕለት መጋቢት 28 ደግሞ ህጻናቱ ...
Read More »ኢቦኒ የተባለው መጽሄት ተዘጋ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 6 አመታት በህትመት ላይ የነበረው ኢቦኒ መጽሄት የተዘጋው ከመንግስት ከፍተኛ የሆነ የግብር እዳ ከተጣለበት በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ የመጽሄቱን ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝን ጠቅሶ እንደዘገበው የመጽሄቱ አዘጋጆች ሙሉውን ግብር ቀርቶ ግማሹንም ለመክፈል ባለመቻላቸው መጽሄቱን ለመዝጋት ተገደዋል። ድርጅቱ ከወረቀት እና ከሌሎች የህትመት ወጪዎች ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር ተዳርጎ ...
Read More »በሀረር በቅርቡ ከታሰሩት መካከል አንዱ ወጣት ተገደለ
መጋቢት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀበሌ 10 ነዋሪ የሆነው ዳንኤል ጎሳ የተበላው ወጣት ሀኪም ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ በሁዋላ በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት መሞቱን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። ፖሊስ በበኩሉ ወጣቱ በራሱ ቲሸርት ታንቆ መሞቱን የገለጸ ሲሆን፣ የእስር ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን ወጣቱ ከፍተኛ ደብደባ ደርሶበት ሊሞት ተቃርቦ እንደነበር፣ ፖሊስ እጁ እንደሌለበት ለማስመሰል ቲሸርቱን አውልቆ ...
Read More »