.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ ለሚገኙ መሪዎቻቸው ድግፋቸውን ገለጹ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” ፍትህ ተነፍገንም ትግላችን አይቆምም” የሚል መፈክር በማንገብ  በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ፍትሃዊነት የማይታይበትን የፍርድ ሂደት አውግዘዋል። እጅግ በርካታ ህዝብ የተገኘበት  ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በፓርላማ ቀርበው የሙስሊሙን እንቅስቃሴ መቆጣጠራቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃውሞው እንደገና እየተጠናከ መምጣቱን ባለፉት 2 ሳምንታት ...

Read More »

በባህርዳር ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከተማው አስተዳደር የቤት አፍራሽ ግብረሃይል በቀበሌ 13 በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል ያላቸውን ቤቶች ለማፍረስ በተንቀሳቀሰበት  ወቅት ከነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ቤት አፍራሽ ግብረሃይሎች ነዋሪዎች ዛሬውኑ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቋቸው፣ ነዋሪዎች  ” መጪው የአመት በአል ጊዜ ነው፣  ክረምትም እየመጣ ነው፣ ...

Read More »

ሩሲያ በዩክሬን ላይ በምትወስደው የነዳጅ ማቋረጥ እርምጃ የአውሮፓ አገሮች ችግር ላይ እንደሚወድቁ አሳሰቡ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ፑቲን ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ዩክሬን ያልከፈለችውን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ ባለመክፈሉዋ ነው።የሩሲያ ታላቁ ነዳጅ ማከፋፈያ ድርጅት ጋዝ ፕሮም ዩክሬን በአስቸኳይ እዳዋን የማትከፍል ከሆነ የነዳጅ አቅርቦቷ ይቋረጥባታል። የዩክሬን የነዳጅ አቅርቦት መቋረጥ ከሲሶ በላይ የነዳጅ ፍጆታቸውን ከሩሲያ የሚያገኙት የአውሮፓ አገራት አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ። አሜሪካ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ የተቸች ሲሆን፣ የጀርመንና የፈረንሳይ ኩባንያዎች ደግሞ ጋዝ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ በቦዴዎች ላይ በሰነዘረው ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አስታወቀ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በቦዴዎችና በኮንሶች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለድርጅታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የሟቾችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር ላይ ሲሆኑ  ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርጉም ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል ሆስፒታል ...

Read More »

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆነ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በ2005 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ካገኘችው ገቢ ይበልጥ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በሐዋላ መልክ ያገኘችው ገቢ እንደሚበልጥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ የጹሑፍ መረጃ አመልክቷል። መረጃው እንደሚያሳየው በ2005 በጀት ዓመት አገሪቱ ከኤክስፖርት 3.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከውጭ ከሚልኩት ገንዘብ ደግሞ 3 ቢሊዮን 9 መቶ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ ...

Read More »

180 የሚሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶች የአለም ባንክ አገራትን ከቢዝነስ አንጻር ማወዳደሩን እንዲያቆም ጠየቁ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ባወጣው ዘገባ ደሃ አገሮች “ቢዝነስ” ለመስራት ምቹ ናቸው ተብለው ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ በማሰብ መሬታቸውን ለሃብታም አገራት ነጋዴዎች እያስረከቡ ነው። አገሮች በአሜሪካ ባለስልጣናት አይን እየተገመገሙ ” ለቢስነዝ ስራ ምቹ ናቸው አይደሉም” እየተባሉ እንደሚመደቡ የገለጸው ኦክላንድ፣ በዚህም የተነሳ የደሃ አገር መንግስታት ሀብታሞችን ለማስደሰት ሲሉ ድሆችን እየጎዱ መሬትና ሌሎች ማእድናት እንዲዘረፉ እያደረጉ ነው። ...

Read More »

የሱዳኑ መሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቀዱ

ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንቱ ትናንት ባካሄዱት ፕሬዚዳንታዊ አዋጅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራቸውን በነጻነት እንዲሰሩና እንዲሰበሰቡ እንዲሁም የመንግስትን ሚዲያ እኩል እንዲጠቀሙ ፈቅደዋል። ውሳኔው በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ውይይት ለማድረግ አዲስ ጅማሮ ነው ተብሎለታል። ፕሬዚዳንት በሽር 83 ከሚሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ድርጅትቶች ጋር በመጪው እሁድ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ የፕሬስ ነጻነት ያለምንም ገደብ እንዲከበር እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግስትን በሃይል ለማውረድ ...

Read More »

በየረር ባሬ ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ መምህራን ታሰሩ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ነዋሪ የሆኑ የየረር ጎሳ አባላት ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ ያነሱዋቸውን ጥያቄዎች ተከትሎ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 16 የጎሳው አባላት መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከወራት በፊት በክልሉ መስተዳድር ትእዛዝ ልዩ ሚሊሺያ እየተባለ የሚጠራው ሃይል በጎሳው አባላት ላይ በከፈቱት ጥቃት ከ50 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ቀደም ብሎ በኢሳት የተዘገበ ሲሆን፣ ድርጊቱ ተጣርቶ እርምጃ ...

Read More »

መንግስት የመንግስት ተሽከርካሪዎች በኮድ 4 ሰሌዳ ቁጥር ብቻ እንዲጠቀሙ መመሪያ አወጣ።

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት መመሪያውን ያወጣው በግለሰብ ታርጋዎች በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎች መበራከታቸውን በተመለከተ ዘገባው በኢሳት ከቀረበ በሁዋላ ሲሆን፣ ታዛቢዎች ግን አዲሱ መመሪያ ይስሙላ ነው ይላሉ። ኢሳት የምንጮቹን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል የመመሪያውን ቅጅ ይፋ ባያደርግም ከአፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር መ/401/653/2 የተላለፈው ሠርኩላር  የመንግስት መስሪያ ቤት ተሽከርካሪዎች ከኮድ ቁጥር 4 ...

Read More »

በሶማሊ ክልል የኮካ ኮላ ምርት እንዳይገባ ታገደ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የኢሳት ምንጭ እንደገለጸው ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ የኮካ ኮላ ምርት ወደ ክልሉ እንዳይገባ በመታገዱ ነዋሪው ህዝብ ከሶማሊላንድ እየታሸገ በኮንትሮባንድ የሚገባውን ኮካ ኮላ ለመጠቀም ተገዷል። ኢትዮጵያ በሚገኘው በኮካ ኮላ ድርጅትና በክልሉ መንግስት መካከል ልዩነት መፈጠሩም ታውቋል። ቀደም ብሎ በክልሉ የኮካ ምርትን የሚያከፋፍለው የታዋቂዋ ባለሃብት የወ/ሮ ሱራ ድርጅት ሲሆን፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ...

Read More »