ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ ለሚገኙ መሪዎቻቸው ድግፋቸውን ገለጹ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” ፍትህ ተነፍገንም ትግላችን አይቆምም” የሚል መፈክር በማንገብ  በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ፍትሃዊነት የማይታይበትን የፍርድ ሂደት አውግዘዋል።

እጅግ በርካታ ህዝብ የተገኘበት  ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በፓርላማ ቀርበው የሙስሊሙን እንቅስቃሴ መቆጣጠራቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጅ ተቃውሞው እንደገና እየተጠናከ መምጣቱን ባለፉት 2 ሳምንታት ከተካሄዱት ተቃውሞች ለመረዳት ተችሎአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትና በሙስሊም ጋዜጣ አዘጋጆች ላይ በእስር ቤት ውስጥ የተፈጸመው አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰት የኢትዮጵያውያንን መነጋገሪያ ሆናል።