.የኢሳት አማርኛ ዜና

አንድነት ፓርቲ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሚያዚያ 26 ባካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በስርአቱ ላይ ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል። በሰልፉ ላይ በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚሄደው የውሃ እጥረት፣ የመብራት እና የስልክ ኔት ወርክ እጥረት እንዲቀረፍ ጥሪ ቀርቧል። በቅርቡ በኦሮምያ በንጹሃን ተማሪዎች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች  ያደረሱትን ግድያ፣ ሀሳባቸውን በሚገልጹ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ላይ የደረሰውን ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ወች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠየቀ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ገምጋሚ ቡድን የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ በሚገመግምበት ወቅት መንግስት በጋዜጠኖችና በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚያደርገውን አፈና እንዲያቆም እንዲጠይቅ አሳስቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምገማውን እያካሄደ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞና ጸሃፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ሃላፊ ሌስሌ ሌፍኮው ገልጸው፣ ግምገማው ውጤታ ይሆን ዘንድ የድርጀቱ ...

Read More »

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ባለፈው ቅዳሜ በመንግሥታዊ ድርጅቶች አስተባባሪነት ሲከበር በኢትዮጽያ ስላለው የፕሬስ አፈናና ስለታሰሩ ጋዜጠኞች ጉዳይ ምንም ሳይወያይ ተበተነ፡፡

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየዓመቱ ሜይ 3 ቀን የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጽያ ለአምስተኛ ጊዜ ባለፈው ቅዳሜ በግዮን ሆቴል የተከበረ ሲሆን የስብሰባው አዘጋጅ ሆነው የተገኙት የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት እና የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡ ቀኑ የፕሬስ ነጻነት የሚታሰብበትና ጋዜጠኞች በስራዎቻቸው ዙሪያ ስለገጠማቸው ችግሮች የሚወያዩበት ቢሆንም በመንግስታዊ ድርጅቶቹ ተጠልፎ ስለፕሬስ ካውንስል ምስረታ ጉዳይ ሪፖርት ሲቀርብበት መዋሉ አሳዛኝ መሆኑን ስብሰባውን ...

Read More »

በላዛሪስትታስረውየሚገኙየሰማያዊፓርቲአባላትመደብደባቸው ታወቀ

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊፓርቲሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው ሰላማዊሰልፍቅስቀሳላይእያሉፖሊስይዟቸውላዛሪስፖሊስጣቢያየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትመደብደባቸው ታውቋል። በተለይ ‹‹አንተንየሚጠብቅፖሊስየለንምተብሎ›› ፈተናእንዳይፈተንየተደረገውዮናስከድርከፍተኛድብደባየደረሰበትሲሆንበአሁኑወቅትዮናስ  መንቀሳቀስእንደማይችልአብረውትታስረውየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትመግለጻቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በእስርላይየሚገኙሌሎችየሰማያዊፓርቲአባላትምድብደባእንደረሰባቸውየታወቀሲሆንደህንነቶችናየእስርቤቱኃላፊዎችተጨማሪድብደባእንደሚደርስባቸውእያስፈራሩዋቸውመሆኑንለነገረኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ የሰማያዊፓርቲየህዝብግንኙነትኃላፊአቶብርሃኑተክለያሬድታሳሪዎቹንለመጠየቅናሁኔታውንለማጣራትወደእስርቤትበሄደበትወቅትምእስርቤቱውስጥየሚሰራአንድፖሊስ ‹‹እኔነኝያስደበደብኩት፡፡ምንምአታመጡም፡፡ከፈለጋችሁበደንብእዩኝናክሰሱኝ፡፡አሁንከእኔጋርመነጋገርአትችሉምከግቢውጡ›› ብሎእየገፈተረእንዳስወጣቸውገልጾአል፡፡ በላዛሪስትታስረውየሚገኙትየሰማያዊፓርቲአባላትላለፉትሁለትቀናትበረሃብአድማላይመሆናቸውናበዚህምምክንያትመዳከማቸውየታወቀሲሆንፖሊስናደህንነትበዚህሁኔታላይሆነውእንኳከፍተኛድብደባእያደረሱባቸውመሆኑእንዳሳዘነውአቶብርሃኑጨምሮገልጸአል፡፡ወጣት እስረኞቹ “በመጀመሪያ መታሰራችንህገወጥሆኖእያለ 5 ሺ 500 ብርከፍላችሁውጡመባላችን አግባብ አይደለም በማለት በእስር ለመቆየት መወሰናቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Read More »

በኖርዌይኦዳከተማ የሚኖሩኢትዮጵያውያን “የምእራባውያንእርዳታበኢትዮጵያየንፁሐንዜጎችማፈኛተደርጎመዋሉንለማሳየት“ ያዘጋጁት ውይይትበተሳካሁኔታተጠናቀቀ።

ሚያዚያ ፳፯ (ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኖርዌይየፓርላማአባላትን፣ፖለቲከኞችንእንዲሁምየተለያዩየማህበረሰብክፍሎችን ባሳተፈው በዚህ ዝግጅት ፣   ገዥውስርዓትበሐገርናበሕዝብላይያደረሰውንአፈናናግድያ ፤  የዜጎችመፈናቀልንናየሰብአዊመብትጥሰቶችን  የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ  ፊልሞች ቀርበዋል። የምዕራባውያንለጋሽአገሮችድጎማ አገዛዙ ለሚያደርገው አፈና አስተዋጽኦ ማድረጉን በአቶከሊፋባርቱራእንዲሁምበወጣትሎሚታባህሩ የቀረበው ዝግጅት ያሳያል። ከተጋባዥእንግዶችመካከል ሮድ ፓርቲን በመወከል ሚ/ርቴሪያኮልቦትን፣ ሆይሬ ፓርቲን በመወከል ኒልሰን ፒተርየተገኙ ሲሆንጉዳዮንከአጋሮቻቸውጋርበመሆንለፓርላማለውይይትለማቅረብየበኩላቸውንእንደሚጥሩ ገልፀዋል። ከዚህቀደም ተመሳሳይ ዝግጅትበሰሜንኖርዌይሎዲንገንከተማተካሂዷል። በሌላ ዜና ደግሞበዲሞክራሲያዊለውጥበኢትዮጵያስታቫንገርቅርንጫፍ  የፖለቲካናየሕሊናእስረኞችንለማሰብቅዳሜሜይ 3 ቀንየተካሔደውዝግጅትበተሳካሁኔታመጠናቀቁን አበበ ደመቀ ከኖርዌይ የላከው ዘገባ ያመለክታል።

Read More »

በኦሮምያ የተነሳው ተቃውሞ አድማሱን አስፍቶ እየቀጠለ ነው

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው የኦሮምያ አካባቢ የተነሳው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ በሆነ ሁኔታ እንደቀጠለ ሲሆን ዛሬ በባኮና አካባቢዋ እንዲሁም በቡራዩ ነዋሪዎች ተደብደብው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውም ተሰምቷል። እስካሁን ድረስ ከ40 ያላነሱ ሰዎች በተለያዩ የኦሮሞያ አካባቢዎች መገደላቸውን፣ ከ300 በላይ መቁሰላቸውንና ከ1 ሺ500  በላይ የሚሆኑት ደግሞ መታሰራቸውን ከክልሉ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በባኮ የሁለተኛ ደረጃ ...

Read More »

የአንድነት ፓርቲ የመጪው እሁድ የተቃውሞ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ክፍል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ምንም እንኳ ፖሊስ ቅስቀሳውን ለማደናቀፍ የተለያዩ ጥረቶችን ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም፣ ቅስቀሳው ግን በተጠናከረ መንገድ እየቀጠለ ነው። በካዛንቺስስድስተኛፖሊስጣብያቤተመንግስቱአካባቢቅስቅሰዋል የተባሉትየአንድነትየአዲስአበባሊቀመንበርአቶዘካሪያስየማነብርሃን፣የብሄራዊምክርቤትአባልዘላለምደበበናጋዜጠኛነብዩኃይሉፖሊስ የ11 ቀናት የጊዜ ቀጥሮ ጠይቆባቸው ተፈቅዶለታል። አቶ ያሬድ በእሁዱ ሰልፍ በርካታ ህዝብ ይገኛል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል

Read More »

በቅርቡ የተቋቋመው የገለልተኛው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ ሀገር ጥሎ ተሰደደ።

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንትበፊትየኢትዮጵያጋዜጠኞችመድረክፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እናምክትሉበአፍሪካህብረትጋባዥነትበኢትዮጵያ ያለውን  አፈናበተለይ  በነፃ ሚዲያውላይያለውንጫናእና በጋዜጠኞችላይየሚደርሰውንችግርለመግለጽወደአንጎላማቅናቸው ይታወሳል። ጋዜጠኞቹ  በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ስፍራው በማቅናት ስለተጨባጩ ሀገራዊ ጉዳይሰፊማብራሪያመስጠታቸውን ተከትሎየአፍሪካህብረትየመፍትሄሀሳብማቅረቡናየሰብአዊመብትኮሚሽነሩምመልስመስጠታቸውይታወቃል፡፡ ጋዜጠኛበትረያቆብስብሰባውከተጠናቀቀበኋላወደአገሩለመመለስበሚዘጋጅበትወቅት፤የዓለምአቀፍየጋዜጠኛማህበራትንጨምሮሌሎችየዓለምአቀፍተቋማትሳይቀሩ  የኢትዮጵያ መንግስት ሊያስረው ውሳኔ እንዳሳለፈ በተጨባጭማስረጃስላቀረቡለትለመሰደድ መገደዱ ተመልክቷል። የዞንዘጠኝጦማሪዎችበታሰሩበትወቅትፖሊስየበትረያቆብንቤትበመፈተሸያገኘውንወረቀትሁሉእንደወሰደምየነገረ-ኢትዮጵያ ምንጮችገልጸዋል፡፡ ጋዜጠኛበትረያቆብአንጎላበተደረገውየአፍሪካህብረትስብሰባኮሚሽነሩንበግልበማግኘት በኢትዮጵያ ስላለው የፕሬስ ሁኔታ በስፋት ያነጋገራቸው ሲሆን፤ኮሚሽነሩምበቅርቡወደኢትዮጵያሢመጡእንዲሚያገኙትቃልገብተውለትእንደነበርተገልጻል፡፡ በአንጎላው ስብሰባ  ኢትዮጵያንናየኢትዮጵያጋዜጠኞችመድረክንወቅታዊሁኔታየሚገልጹጽሁፎችለተሰብሰብሳቢዎቹተበትነዋል፡፡ የኢትዮጵያጋዜጠኞችመድረክመቋቋምያስፈራቸውሌሎችየጋዜጠኞችማህበራትበትረያቆብን፦”ለሂውማንራይትስዎች፣ለሲፒጄ፣ለአርቲክል 19ና ለሌሎችየጋዜጠኞችማህበራትይሰራል፣ይሰልላል፣የውጪ ድርጅቶችተላላኪነው”በሚልበተደጋጋሚ ባወጧቸው መግለጫዎች ሲከሱት ቆይተዋል።

Read More »

በጎንደር ገንፎ ቁጭ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች መታሰራቸው ተሰማ

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት ሌሊት አመፅ ቀስቅሰዋል፣ ለ3 ፖሊሶች ሞት ተጠያቂዎች ናቸው ብለው የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ለማወቅ በሚል ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ነዋሪዎችን አስረዋል። በርካታ ወጣቶች አካባቢውን ለቀው መሸሻቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ነን የሚሉት ነዋሪዎች ህዝቡ እንዲታደጋቸውም ተማጽነዋል።

Read More »

ከአዲስ አበባ ካርታ ጋር በተያያዘ የሚደረገው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመስተዳድሩ  ባለስልጣናት ያወጡትን የከተማዋን አዲስ ማስተር ፕላን ተከትሎ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የጀመሩት ተቃውሞ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመዛመት ላይ ነው። በአምቦ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ በድሬዳዋ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ታስረዋል። በአዳማ የተጀመረው ተቃውሞ የረገበ ቢመስልም ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው። ዛሬ ደግሞ በአዲስ ...

Read More »