በጎንደር ገንፎ ቁጭ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች መታሰራቸው ተሰማ

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት ሌሊት አመፅ ቀስቅሰዋል፣ ለ3 ፖሊሶች ሞት ተጠያቂዎች ናቸው ብለው የጠረጠሩዋቸውን ሰዎች ለማወቅ በሚል ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ነዋሪዎችን አስረዋል።

በርካታ ወጣቶች አካባቢውን ለቀው መሸሻቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ነን የሚሉት ነዋሪዎች ህዝቡ እንዲታደጋቸውም ተማጽነዋል።