.የኢሳት አማርኛ ዜና

የዲላ ነጋዴዎች የስራ ማቆም አድማቸውን ቀጥለዋል

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲላ የሚገኙ ነጋዴዎች ከግብር እና ከመልካም አስተዳደር ችግር ጋር በተያያዘ ላለፉት 3 ቀናት የጀመሩትን ተቃውሞ እንደቀጠሉ ሲሆን፣ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩትም አድማውን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ መተላለፉን ነጋዴዎች ገልጸዋል። የከተማው ከንቲባ አቶ ዮሴፍ ጉሙ መስተዳድሩ የሚያወጣውን መመሪያ ካልተቀበላችሁ አካባቢውን ለቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ በማለት በይፋ መናገራቸውን የሚገልጹት ነጋዴዎች፣ ጉዳዩን ለክልሉ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም ” ችግሩን እናየዋለን” የሚል መልስ ...

Read More »

ከቁጫ ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ የታሰሩ ከ300 ያላነሱ ሰዎች  ፍትህ አጥተው እየተሰቃዩ ነው

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ በቅርቡ ከተነሳው የመልካም አስተዳደር፣ የማንነትና የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፍትህ አጥተው ያለፉትን ስምንት ወራት በእስር ቤት ካሳለፉት መካከል አንደኛው ህይወታቸው አልፎአል። የ14 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ የሆኑት የ39 ዓመቱ አቶ ሻልሼ ሸዋ ኮዶ ላዴ ቀበሌ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ ፣ በእስር ቤት ውስጥ ህክማና ተነፍገው  መሞታቸውን የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ...

Read More »

ከቅማንት ብሄረሰብ ጋር በተያያዘ የታሰሩት አሁንም አልተፈቱም

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን ከቅማንት ብሄረሰብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩት 47 ሰዎች በፍትህ እጦት በእስር እየተንገላቱ መሆናቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል ፡፡ ባለፈው ወር የቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ከ13 ያላነሱ ሰዎች በግፍ ሲገደሉ  47 ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። ሰሞኑን በጎንደር ከተማ የብሄረሰብ ተወካዮችን ጠርተው  በጎንደር ሲኒማ አዳራሺ ያወያዩት የክልሉ ...

Read More »

ኢህአዴግ ምርጫውን አስታኮ ቤቶችን ለያከፋፍል ነው

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መራሹ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የእድገትን የትራንስፎርሜሽን እቅድ በአብዛኛው ዘርፎች ባያሳካም የመጪውን ዓመት ምርጫ ተከትሎ በጊዜያዊነት የሕዝቡን ድጋፍ የሚያስገኙለትን ሥራዎች ለማከናውን አቅዶ መንቀሳቀስ መጀመሩን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል በዚሁዕቅድመሠረትየመኖሪያቤትለማግኘትወደ 800ሺሕዝብየተመዘገበበትበአዲስ አበባከተማበያዝነውወርእናበነሐሴወር 40 ሺኮንዶምኒየምቤቶችንእጣለማውጣትናበዚህምድጋፍለማግኘትታቅዶአል፡፡ በተመሳሳይሁኔታእስከ ታህሳስወር 2007 ባሉትጊዜያትእንዲሁወደ 40ሺየሚሆኑተጨማሪቤቶችንለተጠቃሚዎችለማስተላለፍታቅዶእየተሰራመሆኑንምንጮቻችንጠቁመዋል፡፡ ከዚህቀደምየቤቶቹግንባታ 50 በመቶ እንኩዋን ሳይጠናቀቅ በአየር ላይ ዕጣ እንዲወጣ በማድረግ ዕድለኞች ቤታቸውን እስኪረከቡ እስከ ሁለት ዓመታት ...

Read More »

ወንጀል ፈጽማችሁዋል ተብለው ለ3 ዓመታት የታሰሩ ወጣቶች ወንጀል ሰሪው ሲያዝ ተፈቱ

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ቄራ አካባቢ የሚኖሩ አለማየሁ ተክሌ፣ ታደሰ አበራ እና ተካልኝ ወልደማርያም በ2003 ዓም ሰኔ አካባቢ ቤት አቃጠላችሁ ተብለው ለ 1 አመት ያክል ከታሰሩ በሁዋላ፣ ድርጊቱን የፈጸመው ሰው ተይዞ ጥፋት መስራቱን ቢያምንም፣ ፖሊስ “አንዴ ተፈርዷል” በሚል ፍርዱን ጨርሰው እንዲወጡ በማስደረጉ፣ ከ3 አመታት በሁዋላ ከቂሊንጦ እስር ቤት መውጣታቸውን  ገልጸዋል።

Read More »

ፖሊሶች በቡራዩ በተነሳው ተቃውሞ ተሳትፈዋል በተባሉት ላይ ሊመሰክሩ ነው

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በቡራዩ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ መርተዋል የተባሉ 7 ወጣቶች ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓም ፍርድ ቤት በቀረበቡበት ወቅት 5 ፖሊሶች እና አንድ የኢህአዴግ ባለስልጣን በእስረኞች ላይ ለመመስከር መቅረባቸው ታውቋል። በመዝገብ ቁጥር 48 ሺ 385 የተከሰሱት ፈይሳ አብዲሳ ገለታ፣ ፋይሳ ጉታ ረጋሳ፣ ታደላ ቶሎሳ ቱሉ፣ ሽሮምሳ ፋይሳ፣ ጆቲ ተመስገን፣ ከተማ ...

Read More »

የባህር ዳር ባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ መተው አረፈዱ

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓም ከንጋት ጀምረው አድማ መተው ያረፈዱት የባህር ዳር ከተማ ባጃጅ አሺከርካሪዎች ፤ መንግስት ለጥያቂያችን ምላሺ እስካልሰጠ ድርስ የስራ ማቆም አድማው ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከሶስት ሺህ በላይ ባጃጆች የሚርመሰመሱባት ባህርዳር ከጎዳናዋ የተሰወሩባት ከንጋቱ  ጀምሮ ከከተማዋ ተሰውረው ህብረተሰቡ እና መንግስት ሰራተኛው በትራንስፖርት ችግር ውስጥ ወድቆ አርፍዷል፡፡ የባጃጅ አሺከርካሪ ማህበራትሃላፊነቱን በወሰዱበት በዚህ አድማ ፣ ...

Read More »

ፖሊስ በሲኤም ሲ የቤት ለቤት ፍተሻ አካሄደ

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ። በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን ...

Read More »

ኦርኪድ 42 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ተወሰነበት

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆኑት የወ/ሮ አኪኮ ስዩም ንብረት የሆነው ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ 42 ሚሊዮን ብር ወይም 1 ሚሊዮን 700 ሺዩሮ ለ አቶ ዮናስ ካሳሁን እንዲከፍል ፍርድ ቤት መወሰኑን ሪፖርተር ዘግቧል። የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁለቱተከራካሪወገኖችእ.ኤ.አ. ጁላይ 9 ቀን 2011 ለመጀመርያጊዜከተከበረውየደቡብሱዳንየነፃነትቀንላይበተፈጸመየሥራግንኙነትጋርበተገናኘ ነው። አቶዮናስ ካሣሁን፣  የተለያዩ መሣሪያዎችንና ማሽኖች ከጀርመን በማምጣት ለኦርኪድ በማከራየት ...

Read More »

ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች በ2 ወራት ውስጥ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ተስማሙ

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሰልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ቀደም ብሎ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በማክበር በ60 ቀናት ውስጥ የሽግግር መንግስት ይመሰርታሉ። ተፋላሚ ሃይሎች ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ የኢጋድ አባል አገራት ማእቀብ እንደሚጥሉ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገልጸዋል።

Read More »