ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች በ2 ወራት ውስጥ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ተስማሙ

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሰልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ቀደም ብሎ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በማክበር በ60 ቀናት ውስጥ የሽግግር መንግስት ይመሰርታሉ።

ተፋላሚ ሃይሎች ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ የኢጋድ አባል አገራት ማእቀብ እንደሚጥሉ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገልጸዋል።