ፖሊስ በሲኤም ሲ የቤት ለቤት ፍተሻ አካሄደ

ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።

ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።

በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መያዙን አስታውቋል።

አልሸባብ በሶማሊ ክልል  33 የመንግስትን ወታደሮች መግደሉ ይታወሳል። ይህንን አሰቃቂ ጥቃት ተከትሎ በመንግስትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል በተደረገው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።